የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ድብቁ ታሪክ ክፍል ሁለት

via የቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ድብቁ ታሪክ ክፍል ሁለት

Advertisements

Liberalisation in Ethiopian Ethio Telecom,ethiopian airlines ,DR Abey ,inflation in ethiopa

ጸሃፊው ስሜነህ ተረፈ
ኢ -ሜይል smofed@gmail.com ወይም
smofed@hotmail.com
ከፈረሱ ጋሪው የቀደመው የልማት ድርጅቶን ወደ ግል የማዛወርየ‹‹ሊበራሊዝም››ሂደት
በአሁኑ ሰአት ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዋና ዋና የሆኑትን የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ ወደ ግል ለማዛወር መወሰኑ ከዚህ ቀደም ገዢው ፓርቲ ያራምድ ከነበረው የተለየ አቋም ሲሆን እነኚህ የልማት ድርጅቶች ወደ ግል አይዛወሩም በሚል በነሱ አትምጡብኝ የኒኦ ሊበራል ሃይሎች አመለካከት ነው ይሄንን አንቀበልም ሲል የቆየ ቢሆንም አሁን ግን ብዙዎቹን ምእራባውያኑን ጭምር ያስገረመ የፖሊሲ ለውጥን አድርጓል፡፡ የፖሊሲ ለውጡ ያልተጠበቀ ሲሆን የዘገየና ትንሽ(Too little, Too Late)ፈረንጆቹ እንደሚሉት ነው፤ ከዚህ በተጨማሪ ግን የዚህን ያህል ግዙፍ የፖሊሲ ለውጥን ለማድረግ ከመነሳት በፊት ኩባንያዎቹን ለማስተላለፍና ለውጡን መምራት በህዝብ ዘንድ ተአማኒ በሆነ ሁኔታ ሽግግር እንዲደረግ አስፈላጊ የሆኑት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት ነበረባቸው ፡፡
በማንኛውም ሃገር እንደሚደረገው ሁሉ አንድን ተቋም ወደ ግል ለማዛወር እንዲሁም አክስዮኖችን ለህዝብ ለመሸጥ አስቀድሞ የሚያስፈልጉ መዘጋጀት ያለባቸው መደላድል የሚሆኑየገበያ መሰረተ ልማቶች፤ደጋፊ የህግ ማእቅፎችና ተቋማት የሚያስፈልጉ ሲሆን ለምሳሌ ስለ አክስዮን ድርጅቶች የሚደነግገውናከ60 አመት በፊት የወጣው የንግድ ህግ ይሻሻላል ቢባልም ተሻሽሎ አልወጣም ፤ ከዚህ ቀደም ትላልቆቹ የመንግስት ድርጅቶች የቢራ ፋብሪካዎቹን ጨምሮ በዝግ ጨረታ ላሸነፉት የውጭ ኩባንያዎች የተሸጡ ሲሆን ይፋዊ የሆነ የአክስዮን ገበያ ባለመኖሩ ምክንያትእስካሁን ድረስ መንግስት ትላልቆቹን ድርጅቶቹን የመግዛት እድልን ያገኙት የውጭ ባለሃብቶችና እንደ ሚድሮክ ያሉት ናቸው ፡፡እነኚህ ድርጅቶች አክስዮኖቻቸው ለህዝብ ይሸጣሉ ቢባልም በየትኛው የአክስዮን መገበያያ መድረክ እንደሆነ ግልፅ አይደለም ፤ በተደጋጋሚ የንግዱ ህብረተሰብ የአክስዮን ገበያ እንዲከፈት ውትወታ ቢያደርግም በመንግስት በኩል ግን መቆጣጠር አንችልም ፤ ሃገሪቱ ለዚህ ዝግጁ አይደለችም ….ወዘተ በሚሉ ምክንያቶች ፈቃደኝነት አልታየም ፤ ኢትዮጲያ የአክስዮን ገበያ ከሌላቸው በዓለም ላይ ካሉ 40 አገራት ትልቋ መሆኗ የዓለም ሚዲያዎች የዘገቡት ጉዳይ ነው ፤የአሁኑን የመንግስት ድርጅቶችን ለህዝብ አክስዮን እሸጣለሁ የሚለው አቋም በመጀመሪያ የአክስዮን ገበያና ግልፅ የሆኑ የአክስዮን ኩባንያ ድንጋጌዎችና ፤ የንግድ ህግጋት በሌሉበት አክስዮኖቹ እንዴት እንደሚሸጡ ግልፅ ማድረግ ይጠበቃል ፡፡
በመግለጫው ላይ እንደተጠቀሰው ወደ ግል በሚዛወሩበት ሙስናን ለመከላከልጥንቃቄን እንደሚደረግ አመልክቷል፡፡በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት አባል በሆኑበት ሃገራትና በአሁኗ ራሺያ በቦሪስ የልሲን ዘመን የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል በሚያዛውሩበት ወቅት ከፍተኛ ሙስና በመፈፀሙ ዋና ዋና የሚባሉ ድርጅቶች በግለሰቦች እጅ ገብተው አሁን ቱጃር ኦሊጋርክ የሚባሉት የሃገሪቱን የሀብት ሃብት ምንጭ የሆኑትን ኩባንያዎች በርካሽ ዋጋ በእጃቸው ሊያስገቡ በቅተዋል በዚህም ሩስያና ፤ እንደ ኡክሬን ያሉ ሃገራት በሃብታሙና በደሃው መሀከል ሰፊ የሆነ የሃብት ልዩነት ከሚታይባቸው የዓለም ሃገራት ተርታ ተሰልፈዋል ፤ ብዙዎቹ የአሁኑ የሩስያና ኡክሬይን ቢሊየነሮችም በዚህ መንገድ ሃብትን ያካበቱና ፖለቲካውንና ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር በቻሉ ሰዎች ስለሆነ ዲሞክራሲን ለማስፈንም እንቅፋት ሆኗል ፤ የአሁኑ የሩስያ ፕሬዝደንት ፑቲንም በእነኚህ ዲታ ኦሊጋርኮች ጋር በመሻረክና የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብት በመከፋፈል ሃገሪቱን እየገዙ እንዳለ ይታወቃል፤እነኚህ ባለሃብቶችም ሃገራቸውን ስለማያምኑ ኑሯቸውን በአውሮፓና እንግሊዝ ሲያደርጉ የሃገራቸውን ሃብትም ወደ ውጭ በማሸሽ ኪሳራን ተከትሎም የተዛባ የሃብት ክፍፍል አስከትለዋል፤ እንዲሁም በቻይናም የመንግስትን ኩባንያዎችን እንደ ሩስያ አይሁን እንጂ የኮሚኒስት ፓርቲው አባላትና ዘመዶች ሊከፋፈሏቸው በቅተዋል፡፡
ውሳኔው በገዢው ፓርቲ የተወሰነ ሲሆን ነገር ግን ይህ ቁልፍ ውሳኔ እንደመሆኑ መጠን መወሰን የነበረበት በፓርቲ መዋቅር ነው ወይንስ አስፈጻሚ በሆነው በሚኒስትሮች ም/ቤትና በህግ አውጪው መፅደቅ ነው የነበረበት የሚለው አነጋጋሪ ነው ፤ ጉዳዩ ወደ ፓርላማ ሄዶ ህግ ሆኖ በሚቀየርበት ወቅት ፓርላማው የገዢውን ፓርቲ ውሳኔ ማፅደቅ ይጠበቅበታል ማለት ነው ፡፡ትላልቅና ወሳኝ የሆኑ የኢኮኖሚ አውታር የሆኑ ድርጅቶችን ፤ወደ ግል የማዛወር ሂደት በጥንቃቄ መተግበር ሲኖርበት ከላይ የተጠቀሱትንና የሌሎችን ሃገራትን ልምድን ማስተዋል ያሻል፤ይዛወራሉ ከሚባሉት መሃከል ቴሌን ብንወስድ ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ከመደረጉ በፊት ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ክፍት ተደርጎ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ሃብትን እንዲፈጥሩበትና የመወዳደር ብቃታቸውን ለማሳደግ ቅድሚያ እድል ማግኘት የሚገባቸው ሲሆን እነሱ ሲጠነክሩ ለውጭዎች ክፍት መደረግ የነበረበት ቢሆንም ለረጅም አመታት ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ጭምር ክፍት አይደረግም በሚል ግትር አቋም በመንግስት ሞኖፖሊ ለአመታት ተይዞ ቆይቷል፤ የአየር መንግዱም ዘርፍ ከአነስተኛ አውሮፕላንና ከአምቡላንስና ሄሊኮፕተር በስተቀር ለትላልቅ የግል አየር መንገዶች ፈቃድ የማይሰጥ ሲሆን መጀመሪያ ዘርፉን ክፍት በማድረግ የሃገር ውስጥ ትላልቅ አውሮፕላኖችን ለሚያንቀሳቅሱ ክፍት መደረግ ነበረበት ፡፡ አሁን ክፍት ይደረጋሉ የሚባሉት ዘርፎች በሙሉ የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ያለ ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ቢፈቀድ ስንት ቴሌና ስንት ትላልቅ የግል አየር መንገዶች ሊኖሩ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል፡፡
የፋይናንሱን ዘርፍ ብንመለከት የግል ኢንሹራንሶችና ባንኮች መጀመሪያ ለሃገር ውስጥ ተወዳዳሪዎች ክፍት የተደረገ ሲሆን አንዳንዶቹ ተቋማት ከፍተኛ ካፒታልን እስከመፍጠር ደርሰዋል አሁን የዚህ ዘርፍ ችግር ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ክፍት መሆኑና ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት አለመደረጉና ለረጅም ግዜ ዝግ ሆኖ መቆየቱ ደግሞ በዘርፉ በቂ ውድድር እንዳይኖርና የውጭ ምንዛሬን ለማፍራት በራሱ እየፈጠረ ያለው ችግር አለ፡፡ ነገር ግን አሁን ክፍት ይደረጋሉ የተባሉት ዘርፎች ቅደምተከተሉ መሆን ያለበት መጀመሪያ ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች እንዲሳተፉ ህጎችን ማውጣት የነበረበት ሲሆን በመቀጠልም በሃገር ውስጥ ካፒታልን ከፈጠሩና ከውጭ ባለሃብቶች ጋር መወዳደር የሚያስችል አቅምን በሚፈጥሩበት ወቅት የውጭዎቹ እንዲገቡ ይደረጋል፤ ነገር ግን የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ግን ለውጭም ለሃገር ውስጥም እኩል ክፍት ማድረጉ የተለየ ያደርገዋል ፡፡በኢትዮጲያ የመንግስት ድርጅቶችን ወደ ግል የማዛወር ሂደት ግልፅነት የጎደለውና ለሙስና የተጋለጠ ሲሆን ፤ ብዙዎቹ ትላልቆቹ ለውጭ ባለሃብት የተላለፉ ሲሆን ህብረተሰቡ ከደመወዝተኝነት ውጪ ሌላ ሃብትና ንብረትን እንዳያፈራ ሲያደርገው ከእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ የባለቤትነት ድርሻ መብት ለመግዛት ምንም እድልን ሳያገኝ የቀረ ሲሆን የአሁኑ ለየት የሚያደርገው ግን ለህዝቡም ድርሻን እሸጣለሁ ማለቱ ነው ይህ መልካም ሲሆን ህዝቡም ተሳታፊ መሆኑ ለግልፅነት አጋዥ ነው፡፡
የገንዘብና / ኢኮኖሚ / ትብብር ሚ/ሩ 59 ቢሊየን ብር በላይ የ2011 ዓ.ም. በጀት ጉደለት ማሳየቱንና ይህንንም ለመሙላት በሃገር ውስጥ የገንዘብ ህትመት ይሸፈናል ማለታው መጪው ግዜ የባሰ የዋጋ ግሽበት የሚታይበትና የዜጎች ኑሮ የበለጠ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገባ አመላካች ነው፡፡ የበጀት ጉድለቱን ለመሙላት አሁን ካለው አሳሳቢ ከሆነውና አሁንም እየናረ ካለው የዋጋ ግሽበት አንጻር እንደ ከዚህ ቀደም ተጨማሪ ገንዘብን ወደ ኢኮኖሚው ቢለቀቅ የሚፈጥረውን ተጨማሪ ግሽበትን መቋቋም ስለማይቻል እነኚህን ድርጅቶችን መሸጥ አማራጭ የሌለው ሆኖ ተገኝቷል
እንደ ቻይና ያሉ ሃገራትም በተነሳው ብጥብጥና የፖለቲካ አለመረጋጋት ሳቢያ ወደዚህ የሚልኩትን ኢንቨስትመንታቸውን ያዝ ማድረጋቸውም ተሰምቷል ፤ ከውጭ ይገኝ የነበረው ብድር የመቀነስ አዝማሚያን አሳይቷል – በመሸጥ ካልሆነ በቀር እንደ ከዚህ ቀደሙ በብድርም ሆነ በእርዳታ በቀላሉ ከውጪ ገንዘብ ማግኘት እንደማይቻል መገመት ይቻላል ፤ስለሆነም መንግስት ካለበት የእዳ ጫናና ከከፍተኛ የበጀት ጉድለት ለማቃለል የእነዚህን ድርጅቶችን ሽያጭ እንዳሰበው መገመት ይቻላል ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኢኮኖሚውን ለውጭ ባለሃብቶች ‹‹ሊበራላይዝ›› ክፍት አድርግ የሚለውን የምእራባውያንን ግፊት መልስ ለመስጠትና የፖሊሲ ማሻሻያን በማድረግ ሊመጣ የሚችልን እርዳታንና ብድር ለማግኘት ሊሆን ይችላል ፡፡ ሃገሪቱ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል እንዳትሆን አንድ እንቅፋት ሆኖ የቆየው ይሄው ክፍት አይደረጉም የሚባሉት ዘርፎች ጉዳይ ነው ፤ ይሁንና ወደ ግል ይዛወሩ በተለይም ለሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ይተላለፉ መባሉ መልካም ቢሆንም ያለውን የሃብት ልዩነትን እንዳያሰፋውና ለማስተካከል በሚያስቸግር ሁኔታ ሃብት በጥቂቶች እጅ መከማቸትን እንዳይፈጥር ጥንቃቄን ማድረግ ያሻል፡፡የልማት ድርጅቶቹ ለረጅም አመታት ሞኖፖሊ በመሆን ባለሃብት አይገባባቸውም መባላቸው በሃገሪቱ እድገት ላይ የራሱን አሉታዊ ተፅእኖን ፈጥሮ ቆይቷል ፤ ቴሌና አየር መንገድ ድርጅቶች በጣም አትራፊ ስለሆኑ እንደ ኢትዮጲያ አየር መንገድ ያለው በውጭ ምንዛሬ ስለሆነ በተለይም የውጭ ባለሃብቶቹ ትርፋቸውን ወደ ውጭ ማውጣትም ይችላልበዚህም ምክንያት የውጭ ባለሃብቶችን ለመሳብ ያስችላል ፤ ነገር ግን ከቴሌ በተለየ ሁኔታ አየር መንገዱ አትራፊና የብሄራዊ መለያ እንደመሆኑ መጠን እርሱን ወደ ግል ማዛወሩ የተቻኮለ ውሳኔ ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ እነኚህ የልማት ድርጅቶች በሙስናና ውጤታማ ያልሆነን አገልግሎት በመስጠት የሚታወቁ ናቸው እንደ ቴሌ ፤ (Shipping Lines) ሺፒንግ ላይንስ ያሉት መንግስታዊ ሞኖፖሊዎች ሲሆን ተወዳዳሪ ኩባንያዎች ቢኖሩ የዋጋና የጥራት ልዩነት ሊመጣ የሚችል ሲሆን ለዚህ የገበያ ውድድር መልካም እድልን ይፈጥራል ፤ከእነኚህ ኩባንያዎች ግልጽ የሆነ የሂሳብ አያያዝ የሚጠይቅ ሲሆን የሂሳብ ሪፖርቶችንም በየሩብ አመቱ በግልፅ ማተምን ይጠይቃል፡፡ ከዚህ ቀደም ለኢትዮያ ዋነኛ አበዳሪ የሆነችው ቻይና የንግድ መርክብ ድርጅት ውስጥ ድርሻ ይሰጠኝ ብላ ጠይቃ የነበረ ሲሆን ለውጭ ባለሃብቶች ክፍት ሲደረግ ቻይናና ሌሎች የሩቅ ምስራቅ አበዳሪዎች ኢኮኖሚውን ለመቆጣጠር የሚስችላቸውን ድርሻ ሊይዙ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ፡፡ መንግስት አብዛኛውን ድርሻ አሁንም ቢሆን እኔ እይዛለሁ ቢልም በሂደት ግን አንዴ መሸጥ ከጀመረ እየሸጠ መውጣቱ የማይቀርና የግል ባለሃብቶቹ ድርሻ እያየለ መምጣቱ አይቀርም ስለዚህ ቋሚ የሆነ የአክስዮን ግብይት በማቋቋም ማንኛውም ሰው ባለው አቅም አክስዮኖችን የመግዛት እድልን ማግኘት አለበት፡፡
የወጪ ንግድ ገቢ የሃገሪቱን ምንዛሬ ፍላጎትን ማሟላት ባቃተው ወቅት ድርጅቶቹን የተወሰነውን ድርሻ መሸጥ እንደ አንድ የገቢ ምንጭ ሆኖ ሊያገለግል ቢችልም በዘላቂነት ግን በሽያጩ ከሚገኘው ገቢ አስተማማኝ ገቢን የሚያስገኝ አቅምን መፍጠር ዋነኛ ተግባር መሆን አለበት፡፡የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለውጡ በዚህ መገታት የሌለበት ሲሆን የሃገሪቱን ሃብት ለረጅም ዘመናት አስረው የያዙና ትርፋማ ያልሆኑ ዘርፎች ለውድድር ክፍት በማድረግ በተሻለ ሁኔታ በግል ባለሃብቶች እንዲተዳደር መደረግ አለበት ፡፡

Ethiopian Justice system

ፀሃፊው በስሜነህ ተረፈ
የፍትህ ስርአቱ ትኩረትን ይሻል
መልካም አስተዳር ለማስፈን ዋነኛ መሳሪያ ከሆኑት ተቋማት መሃከል ፍርድ ቤቶች ዋነኞቹ ቢሆኑም ነገር ግን ህብረተሰቡ በሚጠበቅባቸው ደረጃ ላይ አለመሆናቸው የፍትህ አሰጣጡ ያለበትን ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ አድርሶታል ፤ ፍርድ ቤቶች ተገቢውን ፍትህ ለመስጠት ዝግጁ አለመሆናቸው በአሁኑ ሰአት በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚታየው የስነ ምግባር ውድቀት አሳሳቢ ደረጃ ላይ Continue reading

EPRDF justice system

የፍትህ ስርአቱ አሳሳቢ ፈተናዎች
ምንም አንኳን አዲሱ ጠ / ሚር ወደ ስልጣን ሲመጡ ብዙዎች ተደስተው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ትኩረት ይሻ የነበረውንና በአሳሳቢ ሙስናና የስነ ምግባር ብልሹነት ተዘፍቆ ያለውን የፍትህ ስርአቱን የበታች አመራሮች ሳይቀይሩ ባሉበት እንዲቀጥሉ ማድረጋቸው አዲሱ ጠ / ሚር ስለ መልካም አስተዳደር ለማስፈን የት ቦታ ማተኮር እንዳለባቸው ትኩረት እንዳላደረጉ ማየት ይቻላል ፡፡

ለቀድሞው ጠ / ሚር መልካም አስተዳደር አለመስፈን ዋነኛ ችግር ፈጣሪ የነበሩት ፍ/ቤቶች ሆነው ሳለ ነገር ግን ይህንን