ዲሞክራሲና ልማት / ምርጫ

ዲሞክራሲ የረጅም ጊዜ ሂደት «ፐሮሰስ» መሆኑ በርካታ የዘርፉ አዋቂዎች የሚገልፁት ጉዳይ ነው ። ዲሞክራሲ ባለባቸው ሀገራትም እንኳን ነን የዲሞክራሲ ግንባታው ሂደት ቀጣይ መሆኑ ይታወቃል ። ዲሞክራሲ ዳብሮባታል በምትባለው ሀገረ አሜሪካ ሳይቀር የዲሞክራሲ ግንባታው በሂደት ላይ መሆኑ ይገለፃል ። በአሜሪካን ሀገር የመጀመሪያው አፍሪካ – አሜሪካዊ ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠ ሲሆን ፣ እስካሁንም ድረስ በአሜሪካን ሀገር ሴት ፕሬዝዳንት ሆና ተመርጣ አታውቅም ። ነገር ግን ከተወሰኑ አመታት በኋላ ሴት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆና ብትመረጥ አስገራሚ አይሆንም ። በዲሞክራሲ አለም ውስጥ በወቅቱ ከሆነው ሁነት በላይ የሂደቱ መዘርጋት ይበልጥ ቁልፍ ጉዳይ ነው ። ዋናው ስርአቱ ፣ ህጎቹና አሰራሮቹ እስካሉ ድረስ ፣ እየዋለ እያደረ የሚፈለገውንም ውጤት መስጠት ይጀምራል ። ሌሎች አናሳ የሆኑ በስልጣን መድረኩ ተሳትፈው የማያውቁ ማሳተፍም አንዱ የዲሞክራሲው ግንባታ ሂደት ተቀጣይ ሂደት አካል ነው ።
ዋናው ሂደቱ ነው ሲባል ሂደቱ እስከተዘረጋ ድረስ የዛሬን አይደለም ማየት ያለብን ፣ የዲሞክራሲያዊ ሂደቱ እስካለ ድረስ ፣ ወደፊት በርካታ ፓርቲዎች ወደ ስልጣን ተመርጠው ይመጣሉ ። የትኛውም ወገን ከዲክራሲያዊ ምርጫ ውጪ በሌላ በምንም አይነት መንገድ ስልጣንን መያዝ የሌለበት ሲሆን ለሂደቱም ሙሉ ለሙሉ ተገዢ መሆን አለበት ።
በአለም ላይ በጣም እሚደነቁት መሪዎች ለብዙ አመታት ስልጣን ላይ የቆዩ ወይም ጭራሽ ላይ ስልጣን ላይ ወተው እማያውቁ ሊሆኑ ይችላሉ ። በመሆኑም መሪዎች በአጭር ጊዜ ስልጣን ላይ በመቆየት ሊያስገኙ ከሚችሉት ጥቅም ይልቅ የዲሞክራሲ ስርአትንና ሂደቱን መገንባትየበለጠ ጥቅም ያስገኛል ። በዚህ መስክ ምንም እንኳን ሁለቱም ሀገራቸውን ከቅኝ ዘገዛ አገዛዝና ከአፓርታይድ ያላቀቁ ቢሆንም ሙጋቤን ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ መቆየታቸውና ስልጣናቸውን ላለመልቀቅ ያደረጉት ትግል ተወዳጅነትን ሲያሳጣቸው ፣ በአንፃሩ ማንዴላ ግን ትግሉ ስኬትን ከተጎናፀፈ በኋላ ግን ብዙም በስልጣን ለመቆየት አልፈለጉም ፣ ይህም ተወዳጅነታውን ጨመረው እንጂ አልቀነሰውም ።
የዲሞክራሲ ስርአት አንዱ ሌላው ጠቀሜታው በባሰለስልጣናት መካከል እርስ በእርስ ኢንተርዶዲፔንደንት ስለሚሆኑ በባለስልጣናት መሀከል አላስፈላጊ ውድድርን ያስቀራል ። ሌላውም ባለስልጣን መራጮችና ደጋፊዎች ስለሚኖሩትእነኛን ደጋፊዎች ላለማጣት ሲባል ፣እና ስልጣኑ በአንድ ባለስልጣን እጅ ስለማይገባ እርስ በእርስ መደጋገፍና ተባብሮ መስራት እድልን ይፈጥራል ። ጥምር መንግስትም ከሆነ እንደዛውየጥምር መንግስቱ አባላት እርስ በእርስ በመግባባት ይሰራሉ።
አንዱ ለታዳጊ ሀገራት የዲሞክራሲ እድገት መቀጨጭ የሚነሳው ጉዳይ የአገራቱ ድህነት ሲሆን ፣ በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችና መሪዎቹን ጨምሮ ስልጣናቸውን ካጡ ኑሯቸውንም ያጣሉ የሚል ሲሆን ይህም በተወሰነ ደረጃ እውነትነት አለው ።በአውሮፓና በአሜሪካ ሀገራት ግን ፖለቲከኞች በምርጫ ስልጣናቸውን ቢያጡ ወይም የስራ ዘመናቸውን ቢጨርሱበተለያዩ ኩባንያዎችና ድርጅቶች ውስጥ የመግባት ፣ የመቀጠር እድል ስለሚኖራቸው ስልጣን ከለቀቁ በኋላ የግል ህይወታቸው ሲያሳስባቸው አይታይም ። አፍሪካ ውስጥ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ግን መሪዎቹም ሆነ ሌሎቹ የፖለቲካ መሪዎች ስልጣናቸው ሲሰናበቱ የሚገቡባቸው ተቋማት አለመኖር ፣ ከስልጣን ሲሰናበቱ ስራቸውን ብቻ ሳይሆን ኑሯቸውንም ጭምር የሚያጡ መሆናቸው ከስልጣን ላለመልቀቅ የሙጥኝ የሚሉበት አንዱ ምክንያት ይሄው ነው የሚል ሀሳብ እሚያቀርቡ ሰዎች አሉ ።
በተጨማሪም የህግ ስርአታቸው ለበርካታ አመታት የዳበረ ስለሆነ አንዱ ባለስልጣን ስልጣን ላይ እያለም ቢሆን ከህግ ውጪ የሚያደርገው ነገር ስለማይኖር ፣ ላድርግም ቢል ህጉ ራሱ ስለሚከለክለው በስልጣን አላአግባብ መጠቀምና ፣ የመሳሰሉት ወንጀሎች የመፈፀማቸው እድል ጠባብ ስለሚሆን መ ሪዎች በዚህ በኩል የሚፈሩት ነገር አነስተኛ ነው ።
ሌላው ደግሞ የውጪ ሀይላትም ቢሆኑ ያ ሀገር መንግስት የነሱን ፖሊሲ እስከደገፈና እስካልተቃወማቸው እና ጥቅማቸውን እስካልተፃረረ በስተቀረ ፣ የዛ አገር ህዝብ ውስጣዊ ግፊት ካላደረገ በውጪ ሀይሎች ድጋፍ ዲሞክራሲ በየትኛውም ሀገር እንደማይመጣ በተደጋጋሚ ታይቷል ። የራሱ የህዝቡ ከውስጥ የሚነሳ ግፊት የበለጠ ውጤት አለው ። ለምሳሌ በሩስያ በ2011 ከተደረገው ምርጫ በኋላ በምርጫው ላይ ባለው ቅሬታ ህዝቡ ወጥቶ ሰልፍ በማድረግ ትክክለኛ ምርጫ እንዲደረግ ጠይቋል ።
ሌላው በምእራቡ አለምም ጭምር እየታየ ያለ ገሀድ ፣ የተራጩ ህዝብ ስለምርጫው ያለው ግንዛቤ ማደግ በራሱ በምርጫ ሰሞን የሚካሄደው የከረረ ውድድርና ፉክክር ማየት በቂ ነው ። ቀድሞ በቀላሉ ይመረጡ የነበሩ መ ሪዎች አሁን ደግሞ ዳግመኛ ለመመረጥ ከባድ ፉከክክርን ማድረግ ግድ ሆኖባቸዋል ። ለምሳሌ ኦባማ ዳግመኛ ለመመረጥ ያደረጉት ከባድ ውድድር አለምን ጉድ ያሰኘና ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው መፅሄት «savage» በማለት ጠርቶታል ።
የአምባገነን ስርአት በሌላ የአምባገነን ስርአት የመተካት ከፍ ያለ እድል ሲኖረው የዲሞክራሲ ስርአት ወደ አምባገነን ስርአት የመመለስ እድሉ ግን አነስተኛ ነው ። ስለዚህ በእርግጥ አዲስ ስርአትን ማቆም አስቸጋሪና አደገኛም መሆኑ ይታወቃል ። መተካት
የህዝቡ ንቃትም የራሱ የሆነ አስተዋፅኦ አለው ። ዲሞክራሲ ባለበትም ሆነ በሌለበት ሀገር ላይ ህዝቡ የነቃ ከሆነ ቀድሞ መብቱን ማስከበርና ነገሮች በማይመለስ ደረጃ ከመበላሸታቸው በፊት ለማስተካከል እንዲረዳ ያደርጋል ። ነገር ግን ህዝቡ ለረጅም ጊዜ ዝም ካለ ብዙ ነገሮች በማይመለስ ሁኔታ የመበላሸት እድላቸው ሰፊ ሲሆን ፣ ህዝቡ በሚነቃበት ወቅት አንዳንድ ችግሮች ከመበላሸታቸው የተነነሳ ፣ ስርአቱን እንደ አሰዲደስ እስከመጀመር እና ነገሮች በቀላሉ በማይመለስበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ያደርጋል ። ለምሳሌ የአረቡን አመፅ ብንወስድ ፣ የአረብ ሀገራት ህዝብ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ምንም አይነት ተቃውሞንም ሆነ ድምፁን ያላሰማ ሲሆን አሁን ከበርካታ አመታት በኋላ ሲያምፅ በርካታ ነገሮች በማይመለሱበት ደረጃ ከመበላሸታቸው የተነሳ የስርአት መፍረሶችና እንደ አዲስ መጀመርን አስከትሏል ። በተመሳሳይም በአሜሪካን አገር የታየው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎችና አመፆች ፣ በለበርካታ አስርት አመታት ኮርፖሬሽኖች፣ እንዲሁም ድጋፍ አሰባሳቢዎች ከጀርባ ሆነው ፖለቲካውን ሲመሩ እንደቆዩ የሚታወቅ ሲሆን ህዝቡ በሚነቃበት ወቅት ግን በርካታ ነገሮች ተበላሽተውና በቀላሉ የማይስተካከሉበት ደረጃ ላይ ደርሰው ደረጃ ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s