መልካም አስተዳደርና ድርቅ

የአማርታ ሴን የተባለው የምጣኔ – ሀብት ባለሙያ ከታሪክ የተወሰኑ ምልከታዎችና መረጃዎችን በውሰድ በመልካም አስተዳደርና በረሀብ መሀከል ቀጥተኛ ዝምድና እንዳለ አስቀምጧል ። በርቀት ያሉ ገዢዎች ታሪክ እንግሊዝ ህንድን ስታስተዳድር ፣ እንዲሁም አየርላንድን ስታስተዳድር ፣ እንዲሁም ደርግ የኢትዮጲያ መሪ በነበረበት ጊዜና ምሳሌዎችን በመውሰድ ድርቅን ሳይሆን ረሀብንና ዲሞክራሲን አለመኖር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው አመልክቷል ።በተመሳሳይም በሀገራችንም ፕሮፌሰር መስፍን ይህንኑ ፅንሰ – ሀሳብ ኢትዮጲያ ውስጥ ና ባደረጓቸው ጥተናቶች ተገንዝበዋለቸዋል ። የአፍሪካ ቀንድ መፅሀፍን ጥቀስ
በነገራችን ላይ ድርቅ በየትም ሀገር የሚከለሰት ነው ። በአለም ላይ በግብርና ምርታቸው በሚታወቁት ሰፊና ለእርሻስራ አመቺ የሆነ ሰፊ መሬት ባላቸው ፣ የግብርና ምርቶችን ለአለም ገበያ በሚያቀርቡ እንደ አውስትራሊያ፣ አሜሪካ ፣ ካናዳና ፣ ቻይና በመሳሰሉ አገራት ሲከሰት እንደ ሩሲያ ባሉ የአለም ታላላቅ የስንዴ አምራች የሆኑ ሀገራትም የደን ቃጠሎ ፣ በሰብሉ የበረዶ የመመታት አደጋዎች ያጋጥማቸዋል ። ይሁን እንጂ ድርቅም ሆነ ሌላ የተፈጥሮ አደጋ ቢከሰት በእነሱ አገር ረሀብ አይከሰትም ፣ አቅሙም ስላላቸው ፣እነኚህን አደጋዎች ያለምንም ችግር መቋቋም ይችላሉ ። ደሀ በሆኑና እንዲሁም ውስጣዊ ዲሞክራሲ የሰፈነበትና ፣ ተጠያቂነት ያለበት አስተዳደር በሌለባቸው ሀገራት ግን ድርቅም ሆነ ሌላ የተፈጥሮ አደጋ ወደ አስከፊ ረሀብና ቸነፈር ደረጃ ይሸጋገራል ።
ካርል ማርክስ በዳዝ ካፒታል መፅሀፉ እንደጠቀሰው ቅኝ ገዢ እንግሊዞች ሆነ ብለው ከገበያው ሩዝን ገዝተው የተወሰነ ጊዜ አቆይተው በወድ ዋጋ ይሸጡ እንደነበረ ማርክስም በዳዝ ካፒታል መፅሀፉ ዘግቦታል ።
በነገራችን ላይ የሴን ሀሳብ አሁንም ቢሆን መልካም አስተዳደር በሌለባቸው ሀገራት ላይ ይሰራል ። አልሻባብ በሶማሊያ ያለውን ሁኔታ የዝናብ እጥረት ነው እንጂ ረሀብ አይደለም ያለ ሲሆን ይህም በዛች ሀገርም ቀላል የማይባል ቀውስ መከተሉም ይታወሳል ። ቀድሞም ቢሆን አለም አቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶችን ወደ ሀገሩ ገብተው እንዳይንቀሳቀሱ አግዶ የነበረ ሲሆን በዚህ አስከፊ ረሀብም እንዲንቀሳቀሱ በሙሉ ልቡ ሳይፈቅድ ቀርቷል ። ይሁን እንጂ ሁኔታውን ተከታተሉ አለም አቀፍ ድርጅቶች እንዳስታወቁት ግን በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ ባለፉት 60 አመታት ውስጥ ተከስቶ የማይታይ ነው ብለውታል ። ነገር ግን ይህ ውሳኔው በሱማሊያ ህዝብ ዘንድ ህዝባዊ ድጋፉን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሸረሸርና ከጥቂት ወራት በኋላም ለከፍተኛ ሽንፈት ዳርጎታል።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s