መሪ ይወለዳል ወይስ ይፈጠራል ?

በመሪነት ውስጥ የዘርፉን ባለሙያዎች ከሚያከራክሩ ጉዳዮች አንዱ ይሄ ጉዳይ ነው ። አንዳንዶች መሪ ይወለዳል ማለትም በተፈጥሮ መሪ ሆኖ ይፈጠራል ይላሉ ፣ ሌሎች ደግሞ መሪ ይፈጠራል ፣ ከሁኔታዎች ሁኔታው ራሱ ይፈጥረዋል ፣ ለምሳሌ ጦርነት ቢፈጠር ጦርነት የራሱን መሪዎችን ይፈጥራል ።ከዚህ በተፃራሪው ደግሞ መሪ ይወለዳል ማለትም በተፈጥሮ ታድሎ የተወለዱ ብቻ ናቸው ስኬታማ መሪዎች ሆነው ብቅ የሚሉት የሚሉ አሉ ። አንድ ሰው ለመሪነት ታጭቶ ነው እሚወለደው ፣ ለመሪነት የተወለደ ካልሆነ ብቃት ያለው መሪ ሊሆን አይችልም የሚል አስተያየት ያላቸው አሉ ። ነገር ግን ሁለቱም የየራሳቸው እውነታ እንዳላቸው ልብ ማለት ይቻላል ።

የቀድሞዎቹን ነገስታቶችን ብንወስድ ከመለኮት ተቀብተው ነው ሲወለዱም ጀመሮ ተብሎ ሲታሰብ ነገስታትና ልጆቻቸው ለንግስና የተቀቡና የተመረጡ ናቸው ብለው ሲገዙ ከነሱ ውጪም ማንም መግዛት እንደማይችል ሲያስተምሩና ህዝቡንም ይህን ተቀብሎ ለሺዎች አመታት በዚህ አይነት መንገድ ሲገዙ ኖረዋል ። ከህዝቡ ራቅ ብለውም ፍትሀ – ነገስትንና ሌሎችን ለአስተዳደራዊ ስራዎች የሚጠቅሟቸውን ትምህርቶችን እንዲማሩ ይደረጉ ነበር ።ለምሳሌ ከሀገራችን ታሪክ ብንነሳ በዘመነ መሳፍንት ምንም እንኳን የጦር አበጋዞች የወታደራዊ ድልን ሊያገኙ ቢችሉም ከላይ ስላልተቀቡ ግን የነገስታት ዘሮችን እያነገሱእነሱ ቀጥሎ ያለውን ማእረግ በወቅቱ እንደ ጠቅለላይ ሚኒስትርነት የሚቆጠረውን – የራስ ቢትወደድነት ማእረግን ጨብጠው አገር ያስተዳድሩ እንደነበረ ያለፈው የታሪካችን አንድ አካል ነው ። ይህም ህጋዊ ተቀባይነትን ለማግኘት ማለትም ከላይ መቀባትን ብሎም በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት የተዘየደ የፖለቲካ መላ መሆኑ ነው ።

ጦርነት ታላላቅ መሪዎችን ይወልዳል ። የአለማችን ታላላቅ መሪዎች የምንላቸው በጦርነት ውስጥ የተወለዱ ናቸው ። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ብንወስድ ሩዝቬልት ፣ ቸርችልና ደጎልን ብንወስድ የጦርነት ወቅት መሪዎች የነበሩ ናቸው ። እንደ ናፖሌዎን ቦናፓርቴ ያሉትንም ብንወስድ በርካታ ጦርነቶችን በማካሄድና ድልን በመቀዳጀት ሀያል ነገስታት ለመሆን የበቁ ናቸው ። ከኩባንያ መሪዎችን ብንወስድ ለምሳሌ ክራይስለር የተባለውን የመኪና አምራች መሪ የነበረው ሌክ ዋሌች ፣ እንዲሁም የጄኔራል ኤሌክትሪክ ኩባንያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ኩባንያዎቹ በችግር ውስጥ በነሩበት ወቅት ከችግር ያወጡ ናቸው ።

 

 

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s