መሰረታዊ የምጣኔ ሀብት ህግጋት

ምንም አንኳን በምጣኔ – ሀብት ውስጥ ህግጋት ቢኖሩም ፣እንደ ተፈጥሮሳይንስ ዝንፍ ሳይሉ በማንኛውም ሁኔታ የሚሰሩ አይደሉም ። መሰረታዊ የሆነው የምጣኔ ሀብት ህግ የአቅርቦትና የፍላጎት ህግ ሲሆን ይኀውም በመጀመሪያ ሴይ በተባለ ፈረንሳዊ የተገኘውና የሴይ ሀግ በመባል የሚታወቀው የሴይ ህግ ነው። ይህም በአቅርቦትና በፍላጎት መሀከል ያለውን የሚተነትን ሲሆን የብሉይ ዘመን ምጣኔ ሀብት አስተሳሰብ መሰረት ነው ። የእርሱ ህግ የሚለው አቅርቦት የራሱን ፍላጎት ይፈጥራል (Supply Creats its Own Demand) የሚል ነው ።

ይህም ማለት አቅርቦት እስካለ ድረስ ፍላጎትም ይኖራል ማለት ሲሆን በሌላ አነጋገር የፍላጎት ችግር አይኖርም ማለት ነው ።ስለዚህ በአገር ኢኮኖሚ ደረጃ ስናስበው የአንድ አገር ኢኮኖሚ እንደፈለገው ቢያመርት የገበያ ወይንም የገዢ ችግር አይኖርበትም ማለት ነው ።ይህ አስተሳሰብ የብሉይ (Classical Economics) እጅግ መሰረታዊ የሆነ ፍልስፍና ሲሆን ለብዙ አመታት ያለጥያቄ ተቀባይነትን አግኝቶ ኖሯል ። በተለይም እስከ 1930ዎቹ የአለም ምጣኔ – ሀብት ዝቅጠት ( The Great Depression ) ድረስ የብሉይ አስተሳሰሰብ ገዢ መሰረታዊ ሀሳብ ሆኖ ቆይቷል ። ከ1930ዎቹ ቀውስ በኋላ ግን በኬነስ አማካይነት የኬነዢያን አስተሳሰብ የበላይነቱን ተጋርቶታል ።

ይሁን እንጂ ጉዳዩ ቀላል አይደለም ፣ እንደውም እንደማርክሲስቶች አባባል የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣም መሰረታዊ የካፒታሊዝም ስርአት ውስጣዊ ቅራኔ ነው ። በአቅርቦትና በፍላጎት መሀከል መጣጣም አለመኖር በአለም ላይ ለታዩት በርካታ የምጣኔ – ሀብት መቀዛቀዞችና መዝቀጦች ዋነኛ ምክንያት ነው ።ምንም እንኳን ልል የሆነ የመንግስት ፖሊሲ ፣ የመዋእለ – ንዋይ አፍሳሾችና ፣ የባንኮች መስገብገብና (Speculation) ባህሪ ችግሩን የማባባበስ ባህሪ ቢኖረውም ጉዳዩ ግን የካፒታሊዝም ስርአት የፈጠረው ችግር ነው የሚል ክርክር በማርክሲስቶች በኩል ይቀርባል ።

ይሁን እንጂ የሴይ ህግ የምጣኔ – ሀብት ዋና ንድፈ – ሀሳባዊ መሰረት ሆኖ አሁንም ድረስ የሚያገልግል ነው ። በምጣኔ – ሀብት ውስጥ ምንም እንኳን ከእውነተኛው አለም የራቁ ቢሆንም በጣም ንድፈ – ሀሳባዊ የሆኑ ሀሳቦችን መጠቀም የተመለደ ነው ። በኬነስ በ1936 ዓ.ም በታተመው መፅሀፍ ከመፈተኑ ውጪ ለክፍለ ዘመናት ያለጥያቄ ተቀባይነትን አግኝቶ ቆይቷል ። የሴይን ህግ በመከተልም አልፍሬድ ማርሻል የተባለው ታላቁ እንግሊዛዊ የምጣኔ – ሀብት ሊቅ የአቅርቦትናንና የፍላጎትን ህግ መሰረት እና ሂሳባዊ ስሌቶችን በመጠቀም የአቅርቦትንና የፍላጎትን ሂሳባዊ ቀመርና የግራፍ አመልክቷል።

የዚህ አስተሳሰብ መሰረት መናድ የጀመረው የታላቁ የአለም ኢኮኖሚ መዝቀጥ (The Great Depression) እ.ኤ.አ.በ1930ዎቹ በተከሰተበት ወቅት ሲሆን ያንን ታላቅና ግዙፍ የሆነ አለም አቀፋዊ የሆነ የምጣኔ ሀብት ችግር በአለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የስራ አጥነትን ፣ የፋብሪካዎች መዘጋትን ፣ ገንዘብ ግሽበትንና ብሎም ለሁለተኛው የአለም ጦርነት አንዱ መነሻ ሊሆን በቅቷል ። በዚህ ወቅት ጆን ሚያራንድ ኬነስ የተባለው እንግሊዛዊ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ቀደምት ከነበረው የብሉይ የምጣኔ ሀብት አስተሳሰብን በመቀየርና ሌላ መስመርን በመቀየስ መፍትሄውን ለማግኘት በቅቷል ።

የኬነስ አስተሳሰብ ቀደምት የነበረውን አቅርቦት የራሱን ፍላጎት ይፈጥራል የሚለውን የሴይን አስተሳሰብ አቅርቦት ቢኖርም ግን የግድ ግን ፍላጎትን ይፈጥራል ማለት እንዳልሆነ ታይቷል ስለሆነም ኬነስ ያቀረበው ሀሳብ መንግስት ጣልቃ ገብቶ ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ፍላጎትን ማሳደግ አለበት የሚል ነው ።

ካርል ማርክስም አንዱ የካፒታሊዝም ስርአት ችግር ያመረተውን ያህል ገበያ አይኖረውም የሚል ሲሆን ፣ ከፍተኛ አቅርቦት ቢኖርም ፍላጎት ግን የአቅርቦት ያክልን ስለማያድግ የምጣኔ – ሀብት ችግሮች ይከሰታሉ ፣ ይህምምንን ኬነስ በመረዳት የኬነስ አስተሳሰብ ኢኮኖሚ ችግር ውስጥ በሚገባበት ወቅት ኢኮኖሚዎችን ፍላጎት ማነቃቃት ፍቱንና ትክክለኛ መፍትሄ መሆኑ በተደጋጋሚ የታየ ሲሆን ዋናው ጥያቄ ግን መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ የሚገባው በምን አይነት ሁኔታ መሆን አለበት የሚለውና እስከምን ድረስ ነው መግባት ያለበት የሚለው ነገር ግን ምንግዜም ቢሆን አወዛጋቢ ነው ።ለምሳሌ እ.ኤአ. እ.ኤ.አ በ2008 በአሜሪካን ሀገር በተፈጠረው የገንዘብ ቀውስና የኢኮኖሚ ዝቅጠት ውስጥ መግባት ምክንያት ሁለቱንም የአሜሪካ ዋና ዋና ፓርቲዎች ማለትም ሪፐብሊካኖችም ሆኑ ዲሞክራቶች ኢኮኖሚውን ማነቃቃት እንዳለት ሲስማሙ መጠኑና በምን አይነት ሁኔታ ማነቃቂያው መፈፀም አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ግን ሰፊ ልዩነት አላቸው ።

ሀገሪቱ በእዳ ውስጥ እየተዘፈቀች በነበረበት ወቅት እ.ኤ.አ .ከ2008በፊት ዘመን አንዳንዶች አሜሪካ እየተዘፈቀችበት የነበረው እዳ ያስገርማቸው የነበረ ሲሆን ፣ ይሄን ያህል እዳ ለመሸከም እና የበጀት ጉድለትን ለማሳየት የሚያስችላት ልዩ የሚያደርጋት ወይም የተለየ ነገር አላት ወይ ብለው እስከመጠየቅ ደርሰው የነበረ ሲሆን ፤ ነገር ግን ከጥቂት አመታት በኋላ የኦባማ አስተዳደር ወደ ስልጣን ከመጣ ከሁለት አመት በኋላ ግን የእዳ ጣሪያውን ከፍ ለማድረግ በኮንግሬሱ በአስተዳደሩ መሀከል የታየው እሰጥ አገባ ግን ለመጀመሪያ ጊዜ የችግሩን ጥልቀትና ስፋት ህዝቡ እንዲረዳው አስችሎታል ።

ነገር ግን ይሄው እዳ ውሎ አድሮ የመንግስት ተቋማትን እንዲዘጉ እስከማሳሰብ ድረስ ደርሷል ፣ አንዳንድ ክፍለ ሀገራትና ከተሞችም ከእዳ ብዛት የተነሳ የኪሳራ መክሰራቸውን እስከማወጅ መክሰራቸውን እስከማሳወቅ (File for Bankruptcy) ድረስ ደርሰዋል ። ይህም ካርል ማርክስ ይህን በውስጣዊ ተቃርኖዎች የተሞላው የካፒታሊዝም ስርአት የራሱን መቃብር ይቆፍራል ይለዋል ።በግብር በሚሰበሰብ ገንዘብ የባንክ ብድርንና ወለድን መክፈል እጅግ ፈታኝና በረጅም ጊዜ ሀብታም ለሆነ ሀገርም ቢሆን ፈታኝ እየሆነ እንደሚሄድ የታወቀ ሀቅ ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s