የፈጣሪ ህልውና

የጥንቱ ሰው በዛፍ ፣ እንደ ዘንዶ ባሉ አስፈሪና ትላልቅ አውሬዎች፣ በፀሀይ ፣ በጨረቃ ፣ በወንዝ በመሳሰሉት ያመልክ ነበረ ። ነገር ግን ከዚያ ደግሞ ሻል ሲል በጣኦታት ማምለክ ጀመረ ። ነገር ግን በጣኦታት በማሚያመልክበት ወቅት ጣኦታቱ የሚፈልገውን ሳያደርጉለት ሲቀሩ ለምሳሌ በጥንታዊ ግሪክ ጣኦታቱን ይሰድብና ያላግጥባቸውና የምንላቸውን አይሰሙም ይል ነበረ ። በጥንታዊ ቻይናም እንዲሁ ጣኦታቱ ሳያደርጉ ሲቀሩ ጣኦታቱን ከቤተ – መቅደስ አውጥቶ መንገድ ለመንገድ እየጎተተ ያላግጥባቸውና ፣ የምትፈልጉትን ምግብ አበላናችሁ ፣ በሚመች ቤተመቅደስ ውስጥ አስቀመጥናችሁ ግን ምን አላደረጋችሁልንም እያለ ይሰድባቸው ነበረ ። የኋላ ኋላ ግን ግን ቻይውያን ራሳቸው በማይታየው ታኦ «እግዝአብሄር አምልኮ » መምጣታቸው ይታወቃል ። ግሪኮችና አውሮፓውያንም እንዲሁ አንድ አምላክን የሚያመልከውን የክርስትናን ሀይማኖት መቀበላቸው ይታወቃል። የሰው ልጅ ከእርሱ የበለጠ ልእለ – ተፈጥሮ (Super-Natural) የሆነ ሀይልን ማሰብ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሲያመልክ የኖረና በዚሁ መልክ የሚቀጥልም ይመስላል ።
ለዚህም ከሚታየውና በቀላሉ ከቶ ለትችት ከሚጋለጠው ወደ ማይታየውና በቀላሉ ለትችት ወደ ማይጋለጠው እግዝአብሄር ፅንሰ – ሀሳብ ለመምጣት የሰው ልጅ በርካታ አመታት ፈጅቶበታል ።
በአለም ላይ በርካታ ተቋማት የተቋቋሙት እግዝአብሄር አለ ከሚል አመክንዮ ሎጂክ በመነሳት ነው ። መንግስታትን ለምሳሌ ብንወስድ የአሜሪካን መንግስት የገንዘብ ኖቱ ላይ በእግዝአብሄር እናምናለን የሚል ፅሁፍ ሰፍሮ እናገኘዋለን ። አንድ ሰው ፍርድ ቤት የእምነት ቃሉን ወይንም ምስክርነትን ሲሰጥ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ወይንም በቅዱስ ቁርአን ላይ አድርጎ ይምላል ። ስለዚህ እግዝአብሄር መኖር ወይንም ህልውና
ብዙዎች ለእግዝአብሄር ህልውና የዝግመተ – ለውጥን ክርክሮችን በመጥቀስ ይከራከራሉ ። በአሁኑ ወቅት ሳይንስ ከሀይማኖት አንፃር የበለጠ የመከራከሪያ ነጥቦችን ማስቆጠር የቻለበት ዘመን ነው ። ነገር ግን የሚቸኩሉ ይህንን ክርክር የሚከተሉ ሰዎች እንደሚሉት ነጥቡ የእግዝአብሄር መኖር ወይም አለመኖር ሳይሆን እግዝአብሄር የለም የሚለውን መንገድ በመከተል ከዚያ በሗላ የሚመጡትን ክርክሮችን ሁሉ ማጥፋት ይሞክራሉ ። ነገር ግን ለምሳሌ ኒቼን ብንወስድ እግዝአብሄር ሞቷል ነው ያለው እንጂ እ ግዝአብሄር የለም አላለም ።
የሰው ልጅ በዚህ አፅናፈ – አለም ብቻዬን ነኝ ወይስ ሌሎች ፍጡራን አሉ ወይ የሚለው ጥያቄ በሰዎች አእምሮ ሁልግዜም አለ ። የዩፎዎች ጉዳይ የመጣው በዚህ ነው ።
ለምሳሌ ስፒኖዛ የተባለውን ሆላንዳዊ አይሁን ብንወስድ ለእሱ እግዚአብሄር ማለት «እግዝአብሄር ማለት የተፈጥሮ ኡደት ነው » ይለዋል ። ስፒኖዛ ይህን በማስፋት ነገሮች በትክክለኛው መንገድ በሚሄዱበት ወቅት እግዝአብሄር ስራውን በትክከል እየሰራ ነው ፤ በአንፃሩ ደግሞ ነገሮች በሚበላሹበት ወቅት ደግሞ እግዝአብሄር ስራውን አቁሟል ተፈጥሮ ስራዋን እየሰራች ነው ማለት ነው ይለናል ።
ራጂኒሽን ብንወስድ ደግሞ እግዝአብሄር ማለት በራሳችሁ በውስጣችሁ ያለ ነገር ነው ይለናል ።
ነገር ግን ፍልስፍና ዋነኛ አላማው ስርአትን ማስፈን እንደመሆኑ መጠን የእግዝአብሄር ፅንሰ – ሀሳብ በአለም ላይ ስርአትን ለማስፈን ከረዱ በጣም መሰረታዊ ፅንሰ – ሀሳቦች ዋነኛው ነው ። እግዝአብሄር አሁን በምናውቀው መንገድ – የማይታይ ፣ የማይዳሰስ ሆኖ – ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የተከሰተው በሙሴ ጊዜ ነው ማለት ይቻላል ። ነገር ግን ከመፅሀፍ ቅዱስ እንደምንረዳው እግዝአብሄር ከአዳም ጊዜም ጀምሮ ነበረ ። አዳምን የፈጠረው እግዝአብሄር እንደሆነ አንረዳለን ። ከዚያም ለአብርሀም ፣ ለይስሀቅ እና ለያእቆብ በተለያዩ ጊዜያት እየተገለጠ መንገዳቸውን ያሳያቸውና ችግር ሲገጥመውንም ያፅናናውና ይመራው እንደነበረ መፅሀፍ ቅዱስ ይተርካል ።
የአብረሀም ልጆችና የልጅ ልጆች እንዲሁ በእግርዝአብሄር አማካይነት እየተመሩ ይኖሩ እንደነበር እንረዳለን ። በዚያን ወቅት በእርግጥ ብዙው አለም በጣኦታት ያመልክ ስለነበረ ፣ በአንድ አምላክ የማምለክ እድልን ያገኙት ጥንታዊያኑ አይሁድ እምነት ተከታዮች ነበሩ ። ነገር ግን ከሀዲስ ኪዳን በኋላ እና ከክርስቶስ መምጣት በኋላ ግን የተቀረውን የክርስትያን አለም እግዝብሄርን የእምነቱ ዋነኛ ምሰሶው እድርጓል ።
ሙሴንም ብንወስድ እስራኤላውያንን ከግብፅ የባርነት አገዛዝ አውጥቶ ወደ እስራኤል ሲ ያስገባቸው በመንገድ ላይ እሚበሉት ሲያጡና እሚጠጡት ውሀ ሲያጡ ፣ ከዙያ ከለምለሚቱ ግብፅ አውጥቶ እዚህ በረሀብና በውሀ ጥም ሊጨርስን ነው በማለት በሙሴ ላይ ያጉረመርሙ ነበር በዚህም ሙሴ እግዝአብሄርን ይጠይቀውና ፣ በአምላካቸው ላይ ያላቸው እምነታቸው ከበረሀ ጥምንና ረሀብን ተጋፍጠው ወደ አግራቸውም ምድር እንዲገቡ አስችሏቸዋል ። ያ እምነት በውስጣቸው ባይኖር ግን እስራኤላውያን አንደ ህዝብ እንኳን ሳይተርፉ እዛው ሲና በረሀ ውስጥ ያልቁ ነበረ ። ሙሴ ከእግዝአብሄር ጋር የተነጋገረበት የሲና ተራራ በደቡባዊ የሲና በረሀ በቀይ ባህር በኩል የሚገኝ የግብፅ ግዛት ነው ።
ማንኛውም የሀይማኖትም ሆነ የሌላ ፍልስፍና አላማው ስርአትን ማስፈንና ፣ የሰው ልጅን ስርአትና መልክ ባለው ሁኔታ እንዲኖር ማድረግ ነው ። ሚስጥሩ ያልገባቸው ግን ፣ ሳይንሳዊ ግኝቶችን ከሰው ልጅ ባህሪ ጋር ሳያጣጥሙ እንዳለ ይቀበላሉ ።
ሁለት ዋና ዋና ክርክሮች አሉ ። አንደኛው ስለ አለም አፈጣጠር የሚያትትው ሲሆን ፣ በሌላ በ ኩል ደግሞ ስለ ህሊናዊ ንቃት ያለው ክርክር ነው ። በአፈጣጠር ንድፈ – ሀሳቦችን ብንወስድ በርካታ ንድፈ – ሀሳቦች ያሉ ሲሆን በራሱ በሳይንስ ውስጥ እንኳን በርካታ ንድፈ ሀሳቦች አሉ ። በሌላ በኩል ግን አንድ አለም አቀፋዊ የሆነ አእምሮ አንድ «ዩኒቨርሳል ማይንድ»ወይንም ግንዛቤ እና መረዳት እንዳለ ግን የማያከራክር ነበው ። ኤክሀርት ቶሌ የተባለው መንፈሳዊ ሊቅ እንደሚለው ይህም አለም – አቀፋዊ ግንዛቤም አምላክ ፣ ፈጣሪ ፣ እግዝአብሄርና የተለያዩ መሰል ስሞች ያሉት ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s