መንፈሳዊነትና ዕምነት

 

የአለም የመንፈሳዊነት ማእከል ተደርጋ የምትወሰደው ሀገር ህንድ ስትሆን በአሁኑ ወቅት በህንድና በመላው አለም መንፈሳዊነት የቢሊየን ዶላር ስራ ወይም ቢዝነስ ለመሆን በቅቷል ። በርካታ ምእራባውያን በተለይ እንደ ቱሪስት በመሆን ህንድን የሚጎበኙ ሲሆን መንፈሳዊ ማእከላትን ለመጎብኘት ፣ የጉሩዎቻቸው ጋር ለመገናኘት ፣ በርካታ ቱሪስቶች በየአመቱ ወደ ህንድ ጎርፋሉ ።

በአለም ላይ አሉ የተባሉ መንፈሳውያን ፣ ዮጋ ሊቃውንቶች (Yogists) ከህንድ የሚፈልቁ ሲሆን መንፈሳዊነት ህንድን አልፎ አልፎም የአካባቢው ሀገራት ልዩ መታወቂያ ሆኖ ቆይቷል ። መንፈሳዊነት ከዕምነት በእጅጉ የተለየ ነው ። እምነት ከመንፈሳዊነት የበለጠ ሰፊ ሲሆን ፣ አንድ እምነት ያለው ሰው መንፈሳዊም ሊሆን ይችላል ።

የመንፈሳዊነት መሰረቱ ስጋ ነው ። መንፈሳዊነት ብቻውን በአየር ላይ የተንጠለጠለ ሳይሆን በስጋ ላይ የተመሰረተ ነው ። ዋና ዋና ከሆኑት የህንድ ሀይማኖቶች አንዱ የሆነው የሲክ እምነትን ብንወስድ አንድ ሰው መንፈሳዊ ደህንነቱን መከላከል የሚችለው ፣ አካላዊ ደህንነቱን መከላከል የሚችለው ብለው ስለሚያምኑ ተከታዮቻቸውን በተለያዩ አካልን ከጥቃት የመከላከል ስልቶችና  በጦርነት ጥበብ ያሰለጥናሉ ። በዚህም ሲኮች ህንድ ውስጥ የሚፈሩና ማንም የማይደፍራቸው ናቸው ። ብዙዎችንም እምነቶችን ብንወስድ ፣ እንዲሁ ምድራዊ ስኬትን ለመንፈሳዊ ስኬት እንደ ቅድመ – ሁኔታ የሚያስቀምጡ ናቸው ፤ በጣም ስኬታማ የሆኑ ሀይማኖቶች ፣ ምድራዊ የሆኑት ናቸው ። አይሁዳውያንንም ብንወስድ ሙሴ ለወገኖቹ ባስተላለፈው መልክእክት አበዳሪ እንጂ ተበዳሪ እንዳይሆኑ  ፣ በመዝሙረ ዳዊትም ላይ እንዲሁ እስራኤላውያን የአህዛንብን ርስት እንደሚወርሱ ይገልፃል ።

መንፈሳዊነት በኳምተም ፊዚክስ ግኝት መገኘት እየዳበረ ያለ አመለካከት ሆኗል በዘመናችን ። የቀድሞው የቁስ – አካላዊ ፍልስፍና መንፈሳዊነትን የማይቀበል ሲሆን ፣ ለምሳሌ ማርክሲዝምን ብንወስድ አንዱ ማርክሲስቶች ታላቅ የፍልስፍና ጥያቄ ነው ብለው የሚያምኑት ቀድሞ የተፈጠረው መንፈስ /  ሀሳብ  ነው ወይንስ ቁስ – አካል ነው ? የሚል ሲሆን ማርክሲዝም መንፈስን ወይንም የሀሳብን መቅደም የማይቀበል ፍልስፍና ስለሆነ አሁንም ድረስ እንደ ስር ነቀል / ራዲካል አብዮተኛ ፍልስፍና ተደርጎ ይቆጠራል ። ነገር ግን ማርክስ የሶሻሊዝምን ፍልስፍና ሲፈጥር የዝግመተ – ለውጥ ሀሳብ በዳርዊን  አማካይነት ሲቀመር ፣ በወቅቱ ግን እንኳን የአንስታይን አንፃራዊነት ቀርቶ ኳንተም ፊዚክስ የተሰኘው የፊዚክስ ግኝነት እንኳን አልተገም ። ኳንተም ፊዚክስ ከአንስታይን አንፃራዊነት ግኝት በኋላ በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተገኘ መሆኑ ይታወቃል ። ቁስ አካላውያን መንፈስ ቁስ አካልን አልቀደምም ብቻ ብለው ሳይሆን የሚያምኑት ፣ ጨርሶ የመንፈስንም ህልውናን ጭምር አይቀበሉም ።

በእርግጥ አንድ ሀይማኖት ምድራዊ ስኬትን እማያጎናፅፍ ከሆነ ተቀባይነትን አግኝቶ መቀጠሉ አጠራጣሪ ሲሆን ፣ በተለይም በምእራቡ አለም በአሁኑ ወቅት በርካታ ሀይማኖቶች በዚህ  መስመር የተቃኙ ሲሆኑ ፣ ሌሎቹ ሀይማኖቶችም በዚሁ መንገድ እራሳቸውን እያስኬዱ ይገኛሉ ። ይሁን እንጂ ለምድራዉ ስኬት ብቻ የቆመ ሀይማኖት ብዙም ፣ ከዛ ይልቅ ግን ሁለቱንም መንፈሳዊነቱንም ምርድራዊውንም ሁለቱንም አብሮ ማስኬድ ከቻለ የበለጠ ተቀባይነቱ ይጨምራል ።    

አንዳንድ ጊዜ ሀይማኖትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግጭቶች የመጨረሻ አሸናፊ የማይኖራቸው ሲሆን ፣ የሰዎችን ሰላም ከመበጥበጥና ፣ በአለም ላይ ትርምስን ከመፍጠር ውጪ የሚፈይዱት ነገር የለም ። በአለም ላይ በርካታ ሀይማኖቶች ያሉ ሲሆን ሁሉም የየራሳቸው ልዩነትም ሆነ አንድነት አላቸው ። አክብሮትን ማግኘትና እሚገባኝን ቦታ አላገኘሁም ብሎ እማሚያስብ ከሆነም ብጥብጦች ስሆን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ራሱን ማስተዋወቅና በመግለፅ ተገቢውን ቦታውን ማግኘት ይችላል ። የግድ ወደ አመፃ ድርጊት መሄድ የለበትም ። ብዙዎቹ የአለማችን ሀይማኖቶች መጨረሻ ላይ የአለም ህዝቦች አንድ እ ንድ እንደሚሆኑ ይተነብያሉ ፣ ለምሳሌ የክርስትናን ሀይማኖት ብንወስድ «በጨረሻው ዘመን አራዊት ከአንድ ወ ንዝ ውሀን ይጠጣሉ» የሚሉ ሲሆን አውሬ የተባሉት እርስ በእርሳቸው የማይስማሙትና ለመጠፋፋት የሚፈላለጉት የአለማችን ሀይማኖቶችን ማለቱ ነው ፣ በባሁ ሀኢ እምነትም እንዲሁ ይህን ክስተት ይተነብያል ። 

በመሰረቱ ሐይማኖቶች መንግስታትን አይቃወሙም ፣ ለዚህም ምክንያቱ ሀይማኖቶች የረጅም ጊዜውን የሚመለከቱ ሲሆን መንግስትታ ግን ከሀይማኖቶች አንፃር ኦድሜያቸው አጭርና ከሀይማኖቶች ጋር የማይወዳደር ነው ። መንግስታት አላፊ የሆኑ ነገሮች ሲሆኑ ፣ በአንፃሬ  ግን ሀይማኖቶች ምንም አይን መንግስት ቢመጣ በዛ መንግስት ውስጥ ህልውናቸውን ማቆየት የሚችሉ ናቸው ። ለምሳሌ ሀዲስ ኪዳንን ብንወስድ ክርስቶስ የቄሳርን ለቄሳር ፣ የእግዝአብሄርን ለእግዝአብሄር እርሱም ሆኑ ተከታዮቹ ያለው በፖለቲካ ውስጥ ለመግባት ፍላጎት የሌለው መሆኑን ለመግለፅና ነው ። ሀይማኖቶችንም በረጅም ጊዜ ህልውናቸውን ማቆየት የሚችሉት ፖለቲካ ውስጥ እስካልገቡና በፖለቲካ ትግል ውስጥ ራሳቸውን እስካልዘፈቁ ድረስ ብቻ ነው ። ከአንዱ የፖለቲካ አቋም ጋር ቢወግኑ ግን ያ የፖለቲካ ሀይል በሚሸነፍበት  ወቅት አብረው መሸነፍና የመጥፋት አደጋ ይጋረጥባቸዋል ።

ለምሳሌ የክርስትናን ሀይማኒትን ብንወስድ ፣ ከመንግስት ጋር ሊያጣሉትና ሊፈትኑት የቀረቡትን «የቄሳርን ለቄሳር፣ የእግዝአብሄርን ለእግዝአብሄር » በማለት ግልፅና የማያሻማ መልስን ሰጥቷቸዋል ። አይሁዳውያንንም ብንወስድ ለብዙ ክፍለ ዘመናት በውጪ ወራሪዎች ተረግጠው ቢገዙም ፣ ቤተ – መቅደሶቻቸው በወራሪዎች ቢፈራርሱባቸውም ፣ ንዋየ ቅዱሳን ቢዘረፉና ወደ ውጪ ሀገራት ቢጋዙም በባርነት ቢሸጡም እንዲሁም ብዙ ስቃይን ቢያዩም ሀይማኖታቸውን ግን ለሺዎች አመታት ጠብቀው መዝለቅ ችለዋል ። ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ናቡከደነፆር የተሰኘው የባቢሎን ንገስ በአይሁዳውያን ላይ ያደረሰው ውድመት በታሪክ ከደረሳቸው ግዙፍ ከሆኑ ውድመቶች እንደ ዋናው ተደርጎ ይቆጠራል ። በእነኚህ ሁሉ ጊዜያት ግን ሀይማኖታቸውን መጠብቅ ችለዋል ፣  ቡድሂስቶችንም ብንወስድ ፖለቲካ ውስጥ  የማይገቡ ናቸው ።

ብዙዎቹም ሀይማኖቶች ተከታዮቻቸው መንግስታትን መታዘዝ እንዳለባቸው ለተከታዮቻቸው ያስተምራሉ ። መንግስታትም ቢሆኑ ሀይማኖትን ለመገዳደር አይደፍሩም – የስልጣን መሰረታቸውን የሚፈታተን ሁኔታ ከራሳቸው ከሀይማኖቶቹ እስካልመጣባቸው ድረስ ። ተግባራዊ የሆነ መንግስትም ሀይማኖትን በመነካካት አላስፈላጊ ተቃውሞን መፍጠርን አይፈልግም ። በጣም አክራሪ ርእዮተ – አለምን ያነገቡ ወይንም ራሳቸው አክራሪ እምነትን ያነገቡ ካልሆኑ በስተቀር መንግስታትም ሆኑ የፖለቲካ ሀይሎች ሀይማኖትን የሚጋፉ አይደሉም ። አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት ለምሳሌ ታሊባን በአፍጋኒስታን በተቆጣጠረበት ወቅት የባእድ አምልኮ ማምለኪያዎች ናቸው ያላቸውን ጥንታዊ የቡድሂዝም ሀውልቶችን በዩኔስኮና ከአለም ጭምር እንዳያፈርስ ልመና ቢቀርብለትም ፍርስራቸውን አውጥቷቸዋል ። አንዳንድ የኮሚኒስት መንግስታትም ሀይማኖትን ሲያፍኑና ባለበት ለመግታት ሲታገሉ ተስተውለዋል ። በቅርቢም ማሊን  የተቆጣጠሩ የትዋሬግ አማፅያን ፣ ምንም እንኳን አለም አቀፋዊ ተቃውሞ ቢገጥማቸውም ፣ እንዲሁ እስልምናን አይወክሉም ያላቸውን ፣ ነገር ግን ታሪካዊ የሆኑ ቤተ – መቅደሶችንና ሀውልቶችን አፈራርሰዋል ።  

የአዲሱ ዘመን አስተሳሰብ ባለቤቶች (New Agers) ማለትም በመባል የሚታወቁት ከተለያዩ ሀይማኖቶች የተወሰዱ የተለያዩ ፍልስፍናዎች ላይ የተመሰረቱ ሲሆን የቀጣዮቹ ክፍለ ዘመናት የፍልስፍና እንዲሁም የሀይማኖቶች መሰረታዊ አስተምህሮ መሰረት ሊሆን ይችላል ተብሎ እሚታመንበት ነው ።

ብዙ ጊዜ ታላላቅ ሀይማኖቶች ከእውቀት ይልቅ እምነትን ሲያስቀድሙ ፣ በአንፃሩ ግን ፈላስፋዎች ሀይማኖትን በፍልስፍና ሊመረምሩ ይለፈልጋሉ ። ይህንንም የሀይማኖት መሪዎች እንደሚቃወሙትም ይታወቃል ። ሀይማኖቶች የሀይማኖቶቻቸው አስተምህሮ በፍልስፍና መንገድ እንዲታይ አይፈቅዱም ፣ ምክንያቱም ፍልስፍና ማለት መመራመርን የሚያካትት ስለሆነ ማንም የእምነቱ ሚስጥር ለምርምር እንዲቀርብ ስለማይፈልግ ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s