የህዝብ ብዛትና የምጣኔ ሀብት እድገት

የህዝብ ብዛትን ከምጣኔ – ሀብት እድገት ጋር አገናዝቦ ለመጀመሪያ ጊዜ የገለፀው የምጣኔ ሀብት አዋቂ እንግሊዛዊው ቶማስ ማልተስ (1789)ነው ።እንደእርሱ አባባል ህዝብ ብዛት በጂኦሜትሪክ ፕሮግሬሽን ሲያድግ የምግብ ምርት ግን በአርትሜቲክ መጠን ነው የሚጨምረው የሚል ነው ። የማልተስ ምልከታው ትክክል ቢሆንም እሱ የተነበያቸው አስከፊ ትንበያዎች ግን አልተከሰቱም ። ለምሳሌ የቴክኖሎጂ እድገትን እርሱ ከግምት ውስጥ ያላስገባ ሲሆን በቴክኖሎጂ እድገት አማካይነት ግን የምግብ ምርትን መጨመር ተችሏል ፣ አሁንም ድረስ በግብርናው ዘርፍ አዳዲስ ግኝቶች እየተገኙ እንደሆነ ይታወቃል ።የአለም ህዝብ ቁጥር ማደግ ደግሞ በይበልጥ ለምግብ ዋጋ መናር አስተዋፅኦን አድርጓል ።

ካርል ማርክስ ማልተስን ስራ ከሌላ የተቀዳ ነው ብሎ የሚያጣጥለው የሚል ሲሆን ፣ ማልተስ ስለምግብ ስርጭትን ጉዳይ ከግምት ውስጥ አላስገባም፣ ይሁን እንጂ በአለም ላይ ምንም እንኳን በቂ ምግብ ቢኖርም የስርጭት ችግር መኖር ግን ረሀብን ሊያስከትል እንደሚችል አማርታ ሴን የተባለው የምጣኔ – ሀብት አዋቂ ያስገነዘበው ጉዳይ ነው ። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት ያለው ምግብን በተመለከተ እጥረት ሳይሆን የስርጭት ችግር ነው ያለው የሚለው ሀሳብ በአማርታ ሴን የመነጨ ሀሳብ ነው ።

ሌላው ደግሞ ሆላንዳዊት ቦስሬፍ የምትባል እንዲሁ በተቃራኒው ፤ የህዝብ ብዛት ምጣኔ ሀብት እድገትን ሊያስከትል እንደሚችል ንድፈ – ሀሳቧን አቅርባለች ።ይሁን እንጂ አሁን በአለም ላይ ከሚታየው የምግብ ዋጋ መወደድና የምግብ ምርት እድገት ከአለም ህዝብ ብዛት አንፃርና ከአየር ንብረት ለውጥ አንፃር እየቀነሰ ከመምጣት አንፃር የማልተስ ሀሳብ ሊሰራ ይችል ይሆናል የሚያስብሉ አንዳንድ ፍንጮች አሉ።

የምእራባውያን ሀገራት ህዝብ እያረጀ መምጣትና እያረጀ ያለውንም ህዝብ በበቂ የሚተካ ወጣት አለመኖር የምእራባውያን ፖሊሲ አውጪዎችን በእጅጉ እያሳሰበ ይገኛል ። ለምሳሌ ሩስያ የህዝብ ብዛቷ እያነሰ መምጣቱን የብሄራዊ ደህንነት አደጋ ነው ብላ ያወጀች ሲሆን ፣ ሴቶች ልጆችን እንዲወልዱና እንዳያስወርዱ በማበረታታት ላይ ነች ። የህዝብ ቁጥሯ አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየቀሰነ ስለመጣ ። የሚያንሳትንም የሰው ሀይል በአቅራቢያዋ ካሉ ከሀገራት የምታስገባ ሲሆን ፣ በተለይም የጉልበት ስራን የሚሰሩ ሰራተኞችን ይሄም አናደንዳንድ የዘረኝነትን ስሜት በተለይም በወጣቱ ዘንድ እየፈጠረባት ነው ።
የህዝብ ብዛት ከምጣኔሀብት እድገት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው ነገር ነው። አውሮፓውያን ሩስያን ጨምሮ የህዝብ ብዛታቸው እየቀነሰ ወይንም ባለበት የቆመ ሀገራት የወደፊት ኢኮኖሚ እድገታቸውም ባለበት የመቆም ወይንም የመገታት እድል ያጋጥመዋል ። በአንፃሩ ደግሞ የህዝባቸው ቁጥር እየጨመረ ያለ ሀገራት የተፋጠነ የምጣኔ ሀብት እድገት ይኖራቸዋል።በተለምዶ የሚታሰበው የህዝብ ብዛት የኢኮኖሚ እድገትን ያጓትታል የሚል ቢሆንም በሁለቱ መሀከል ቀጥተኛም ሆነ የተገላቢጦሽ ግንኙነት ሊኖር ይችላል ። የህዝብ ብዛት እድገቱ ከተወሰነ ደረጃ አይለፍ እንጂ የህዝብ ብዛት የምጣኔ – ሀብት እድገትን ሊያፋጥን ይችላል ። በእርግጥ ከተወሰነ ደረጃም ሲያልፍ የምጣኔ – ሀብት እድገትን መጎተትም ይጀምራል ።

ለምሳሌ አንዱ የአውሮፓ አህጉር ያለው የምጣኔ ሀብት አቅም እየቀነሰ ያለበት ምክንያት የአውሮፓ ህዝብ ቁጥር መቀነስና በተለይም ወጣት የሆነው የሰራተኛው ህዝብ ቁጥር መመናመን ነው። ነባሩን ህዝብ ቁጥር የሚተካ ወጣት መኖር አለበት ነገር ግን የሚተካ ወጣት ከሌለ ስራ ሰርቶ ለመንግስት ግብርን የሚከፍል ሰራተኛ ሀይል የሆነ ትውልድ እየተመናመነ ይመጣል።አንድ ህዝብ ቢያንስ ራሱን መተካት መቻል ሲኖርበት ፣ ሊተካ ከሚችለው በታች ከሆነ የወጣት ቁጥር መመናመንን ያስከትላል – ይህም ሰራተኛና አምራች ፣እንዲሁም የተመረቱ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ተጠቃሚ ወይም ሸማች ሀይል እንዲቀንስ ያደርጋል ።ለምሳሌ ጃፓን የህዝብ ቁጥሯ አሁን ባለው እጅግ አነስተኛ የሆነ ራሱን የመተካት ከቀጠለ በአንድ ሺ አመት ውስጥ የጃፓናውያን ዘር እንደሚጠፋ ተተንብያል ። ለምሳሌ በዚህቹ በጃፓን ሀገር የቤት እንሰሰሳት ቁጥር ከአስር አመት ለክ ልጆች ቁጥር በልጦ ተገኝቷል ።

የአውሮፓውያን የህዝብ ቁጥጥር ለብዙ አስርት አመታት በመቀጠሉ ምክንያት አሁን ለሚታየው የህዝብ ቁጥራቸው መሳሳትና የአዛውንቶች ከተረቀው ህዝብ አንፃር ለመብዛቱ አንድ ምክንያት ሆኗል፤ በዚሁ በስነ – ህዝብ ምክንያትም ወጥመድ ውስጥ ገብተዋል ። በአንድ በኩል ከትናንሽ ስራዎች ጀምሮ እሚሰራላቸውን ርካሽ ጉልበት ከውጪ በተለይም ቀረብ ካሉት ሀገራት ማስገባት ሲኖርባቸው ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እነኚህ ወደ ሀገራቸው የገቡ ሰዎች ዜግነትን ጨምሮ – ሙሉ መብትን ይፈልጋሉ ።ይህም ሀገራችንን ውሎ አድሮ በመጤዎች እንዲያዝብን ያደርጋል በሚል ሙሉ መብትን ለማጎናፀፍ ሲያንገራግሩ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እያረጀ ላለው ህዝባቸው ስራ ሰርቶ ጡረታ እሚከፍል ፣ የጤና እንክብካቤን የሚያደርግ የሰው ሀይልም መኖር አለበት ስለዚህ ተጨማሪ የሰው ሀይልን ከውጪ እንዲገባ መፍቀድ እንደሚያስፈልጋቸው ግልፅ ነው ።

ነገር ግን አውሮፓውያን እድሜው እየገፋ እና እያረጀ ያለ ህዝባቸውን እንክብካቤ ለማድረግና ፣ የተሟላ በሆነው የመሰረተ ልማት አውታር ተጠቅሞ የምጣኔ – ሀብት እድገቱን ማስቀጠል እንዳለባቸውም ስለሚረዱ ለቀቅ ያለየስደተኛ ህግን በማውጣት በተለይም ወጣትና ፣ የተማሩ ሰዎችን ከመላው አለም እየተቀበሉ እንደሚያስገቡ የታወቀ ነው ።ይህ ብቻ ሳይሆን አለማችንን የስነ – ህዝብ ስርጭትና ስብጥርን ብንመለከት፣ በአሁኑ ወቅት በተለይም በምእራቡ አለም ከመላው አለም የተሰባሰበቡ ሰዎች ከተለያየ የአለማችን ክፍሎች እየመሄዱና እየኖሩ ሲገኙ ፣ አሜሪካንን ብንወስድ ከጥቂት አመታት በኋላ በአገሯ በህዝብ ብዛት ዋነኛ የሚሆኑት ሂስፓኒክ ወይንም የላቲን አሜሪካ ዝርያ ያላቸው ዜጎች እንደሚሆኑ የተለያዩ ጥናቶች እየጠቆሙ ሲሆን ። ቁጥራቸው በርካታ የሆኑትን ስፓኒኮችን ድምፅ ለማግኘት የአሜሪካ ምርጫዎች ሲቃረቡም በተለይም የአሜሪካ የፕሬዝዳንትነቱ ተወዳዳሪዎች ሂስፓኒኮችን ለማማለል ሲጥሩ ማየት የተለመደ ሆኗል ። የሷም ህዝብ እያረጀ ቢሆንም በአንፃሩ ግን ወጣቶችን ወደ ሀገሯ በማስገባቷና በዲቪ እና ያስገባችውን ወጣት ህዝብ ከፍ ያለ የህዝብ የውልደት መጠን ያለው ስለሆነ ፣ በመሳሰሉት እንደ አውሮፓውያን በስነ – ህዘብ ጉዳይ በጣም አትቸገርም ።

በአንፃሩ የእስያ ሀገራት እያደጉ ያሉበት አንዱ ምክንያት ህዝባቸው ቁጥር ግዙፍ መሆኑ ነው ። የህዝብ ቁጥራቸው ከፍተኛ መሆኑ የሀገር ውስጥ ፍላጎትንና ገበያን ፣እንዲሁም ርካሽ ጉልበትን አስገኝቶላቸዋል ። ለምሳሌ በቻይና በከተማ አንድ ልጅ ፣ በገጠር ደግሞ ሁለት ልጅ ብቻ የመውለድ ፖሊሲ ምክንያት ወላጆች የፅንሱን ፆታ በመመርመር ሴት ከሆነች በማስወረድ ፣ ወንድ ከሆነ እንዲወለድ በማድረጋቸው ምክንያት በብዙ አመታት የሴቶች ቁጥር ከወንዶቹ ቁጥር ጋር መሳ ለመሳ ሊሆን አልቻለም ። ይህም የስነ – ህዝብ ስር ስብጥሩን በማዛባቱ ምክንያት ቻይናውያን ወንዶች ሚስት ትዳር ፍለጋ ከሀገራቸው ውጪ ወደ እንደ ፊሊፒን ላሉ ጎረቤት ሀገራት ለማማተር ተገደዋል ።

በዚህ ምክንያት የቻይና ወንዶች ትዳር መመስረት በሚፈልጉበት ወቅት እንደ ፊሊፒንስ ካሉ ውጪ ሀገራት ሚስቶችን እስከማግባት እየደረሱ ነው። ዋናው የቻይና ህብረተሰብ በፍጥነት እያረጀ ሲሆን ፣ ባለስልጣኖች የስነ- ህዝብ ፖሊሲውን ለመመርመር ተገደዋል። ቻይናውያን መጀመሪያ አካባቢ ህዝብ ብዛታቸውን እንደ ችግር ያዩት የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት ግን ሰፊ ሀገር ውስጥ አቅምን የፈጠረላቸው መሆኑን ተረድተዋል።

በተመሳሳይም ምንም እንኳን ህንድ የቻይና አይነት የአንድ ልጅ ብቻ የመውለድ ፖሊሲ ባይኖራትም ህንድም የፅንሱን ፆታ አስቀድሞ በማየት ፅንሱ የሴት ከሆነ እንዳይወለድ ማድረግ ስለጀመሩ ህንድንም የቻይና አይነት ሁኔታ ያሰጋታል። በነገራችን ላይ ከተወሰኑ አስርት አመታት በኋላ የህንድ ኢኮኖሚ የቻይናን የሚበልጥበት ደረጃ የሚደርስበት ምክንያት በዚሁ በህዝብ እድገት እና የስነ – ህዝብ ጉዳይ ሆኖ እናገኘዋለን።የህንድ ህዝብ በፍጥነት ስለሚያድግ በርካታ ወጣት ሲኖራት በአንፃሩ ግን ቻይና በእድሜ የገፋው ህዝቧ ቁጥር እየጨመረና ሰራተኛና ወጣት የሆነው የህዝብ ቁጥሯ አንፃራዊ በሆነ መልኩ እየቀነሰ ይመጣል።

ስለዚህ ሰራተኛና የወጣት ህዝብ ቁጥር መቀነስና በእድሜ የገፋ ህዝብ ቁጥር መጨመር ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ መቀዝቀዝ አንድ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በእድሜ የገፋ ህዝብ ሲጨምረ ለጡረታና ለህክምና የሚወጣው ወጪ ከፍተኛ ሲሆን ያንን ሰርቶ ሊከፍል የሚችል ወጣት ትውልድ መኖር አለበት ።

የህዝብ ቁጥር ቁጥጥር ተፈጥሯዊ የሆነውን ስነ – ህዝብ ምጣኔውን ማለትም የእድሜና የፆታውን አንፃራዊ ድርሻ የሚያዛባ መሆን የለበትም ።ይሁን አንጂ የህዝብ ቁጥርን ለመቀነስ የሚደረግ ነገር ተፈጥሯዊ አካሄድን በጣም መጫን የለበትም ። ለምሳሌ በሩሲያ ከሁለተኛው የአለም ጦርነትና በስታሊን ጭፍጨፋና በሁለተኛው የአለም ጦርነት ምክንያትየወንዶች ቁጥር በመናመኑ ምክንያት የፆታ ድርሻውን ለማስተካከል ረጅም ጊዜን ፈጅቷል ። ስለዚህ የሩሲያ ሴቶች የውጪ ሀገር ባል እስከ ማፈላለግ ደርሰዋል ።

የህዝብ ብዛት ሁለት ፈተናዎችንም ሆነ እድሎችንም ይዞ የሚመጣ ነገር ነው። በአንድ በኩል እያደገ ያለ ህዝብ በተለይም በወጣቶች የተሞላ በበቂ የሚገኝ ሰራተኛ ህዝብን ሲያስገኝ ለተመረቱ ምርቶችን ሊገዛ የሚችል ሰፊ የሀገር ውስጥ የገበያ እድሎችን ሲፈጥር በሌላ በኩል ደግሞ ደካማ አቅም ላለው ሀገር በቂ መሰረተ ልማቶች በሌሉበት እንደ ሆስፒታል፣ትምህርት ቤት ፣ ትራንስፖርት ፣ መኖሪያ ቤት የመሳሰሉትና በሌሎችም የህዝብ አገልግሎቶች ተቋማት ላይ ጫናን ያሳድራል ።

ሰፊ የህዝብ ቁጥር የገበያ እድሎችን ከመፍጠር ሌላ በሀገር ውስጥ መንግስት ላይ ጫናን ያሳድራል ። መንግስታቸው የመልካም አስተዳደርን እንዲያሰፍን ፣ ዲሞክራሲ እንዲጠናከር እንዲሁም የተሻለ የኢኮኖሚ እድሎች እንዲኖሩና መንግስት ልማቱን እንዲያፋጥን ግፊትምን የማሳደር አቅም ይኖረዋል።ብዛት ያለው ህዝብ ብዛት ከሌለው ህዝብ ይልቅ በራሱ መንግስትም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ተደማጭነት አለው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s