ራስ ወዳድነት

ዝግመተ – ለውጥ ፣ ሙሉ ለሙሉ ሊሰራ የሚችል ነው ፣ እንሰሳት እርስ በእርሳቸው ይበላላሉ ። የራሳቸውን ዘር ይበላሉ ፣ ይሁን የምድር እንሰሳት ጅብ ይሁን አዞ ይሁን እርስ በእርስ ይበላላሉ ። ነገር ግን የሰው ልጅ እንደ እርስ በእርሱ እንሰሳት የሚበላላ አይደለም ። ዝግመተ -ለውጥን እንኳን ብንወስድ ፎር ዘጉድ ኢ ኦፍ ሰ ዘ ሶሳይቲ ነው ። በዛ ሂደት ውስጥ የተሻለ የሚወጣበትና አስፈላጊ ያልሆነው ወይም መወዳደር የማይችለው ጠፍቶ የተሻለው ስለሚተካ በዚሀ ሂደትም በማህበረሰብ ደረጃ ስናየው የተሻለ የሚወጣበት ሂደት ስለሆነ ምንም እንኳን ዝግመተ – ለውጥ በሰው ል ጅ ሞራላዊ እይታ ሲታይ ከስነ – ምግባር ውጪ ሆኖ የሚታይባቸው ነገሮች ቢኖሩም በማህበረሰብ ደረጃ ግን ተፈጥሮ ያስተካከለው ማሀበረሰቡን በዘመናት በሚጠቅም መንገድ የተቃኘ ነው ።

ለምሳሌ አዞን ብንወስድ የራሱን ከሱን ልጅ መልሶ የሚበላ ሲሆን ትንሹ አዞ ካደገ በኋላ ትላልቆቹ አዞዎች የሚኖሩበት አካባቢ መራቅና አነስተኛ በሆኑ ኩሬዎች ሄዶ እስከሚያድግ ድረስ መኖር መቻል አለበት ። ድመትም እንዲሁ ልጆቿን እንደምትበላ የሚታወቅ ነው ። ለሰው ልጅ ቅርብ ናቸው የሚባሉት እንደ ዝንጀሮ ፣ ጎሬላ የመሳሰሉት ሁሉ ባህሪያቸው አንድ አይነት ናቸው ።

ምንም እንኳን አዝጋሚ – ለውጥ ረጅም አመታትን የሚፈጅ ቢሆንም ፣ ሌላው አማራጭ ደግሞ ሌሎች እንሰሳት በረጅም የአዝጋሚ ለውጥ የሰው ልጅ ወደ ደረሰበት የእድገት ደረጃ ላይ ሊጠጉ ወይንም ሊደርሱ ይችላሉ ተብሎ ሊታሰብ ይችላሉ ። ለምሳሌ በአንድ የጦጣ ዝርያዎች ላይ የታየው እንደ ሰው ልጅ እርስ በትህትና መግባባትና የማህበራዊ ኑሮን መኖር ሲችሉ ፣ ልክ እንደ ሰው ልጅ ባህሪያትን ሲያሳዩ ፣ በረጅም አመታትም ከሰው ልጅ ጋራ የሚቀራረብ የዝግመተ ለውጥ ደረጃ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ ተብሎ በሳይንቲስቶች ተገምቷል ።

ይሁን ዝግመተ- ለውጥ በምእራባውያን በተሳሳተ መንገድ ተተርጉሟል ፡ ዝግመተ – ለውጥን (Survival of the Fittest ) አንዲሁም «dog eat dog» በሚሉ አገላለፆች ሲጠቀሙ ማየት የተለመደ ነው ።ነገር ግን ። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ የሚኖረው ለማሸነፍ ብቻ አ ይደለም ። ነገር ግን ልሂቅ ለሚባለው ህብረሰተብ ክፍል ግን ማሸነፍ የሚለው ነገር ትርጉምን ሊሰጠው ይችላል ። ለዋናው ህብረተሰብ ግን ለማሸነፍ ብቻም ሳይሆን ፣ የመኖር የሚሰጣቸው ከማሸነፍና ከመሸነፍ ሌላ በርካታ ትርጉሞች አሉት ።
የአን ራንድ ፍልስፍና እዚህ ላይ ሊጠቀስ ይችላል ። በፕሬዝደንት ክሊንተን ዘመን የተፈጠረ «እኔ ብቻ ልኑር የሚል ትውልድ» [me generation] በመባል የሚታወቀው ነው ። ነገር ግን ህልውና በተናጠል ያለ ነገር አይደለም ፤ ከዚያ ይልቅ በጋራ ያለ ነገር ነው ። ይህ የራስ ወዳድነት አስተሳሰብ በተለይም የካፒታሊዝም ስርአት ስር መስድደድ በጀመረባቸው ሀገራት ሀገራችንን ጨምሮ በመታየት ላይ ያለ ሲሆን ፣ በተለይም ልሂቅ የሚባለው የህብረተሰብ ክፍል ይህአስተሳሰብ መስረፅ መጀመሩ ይስተዋላል ።
ይሁን እንጂ አሁን ባለው ህብረተሰብ ውስጥ ለስነ – ምግባር ቦታን የማይሰጥና ጥቅምን ብቻ የ ሚስቀድም ህብረሰተብ መፈጠር መጀመሩ አሌ የሚባል አይደለም ። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ያሉ ሲሆን ፣ በአንድ በኩል የራሱ የህብረተሰቡ ንቃት መጨመር ፣ እንዲሁም ከዚህ ቀደም በርካቶች መጥተው ሌሎችን በቀላሉ በማሳሳት ወይንም በማታለል ጉዳትን አድርሰውን የራሳቸውን ጥቅም አስከብረው ሲሄዱ ህብረተሰቡ በመመልከቱ የዛን ጉዳትም ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ምንክያት ፣ ቀድሞ በቀላሉ ይወሰዱ የነበሩ ጉዳዪች አሁን ለየት ያለ ትኩረትን የሚሹ ሆነዋል ። ሌላው ደግሞ አሁን ያለው ህብረተሰን እንደ ቀድሞው ሳይሆን ፍላጎቱም ሆነ አኗኗሩ ከቀድሞው ህብረተሰቦች ለየትና ወጣ ያለ መሆኑ ነው ። አሁን ያለው ህብረተሰብ ስለ ገንዘብ ፣ ስለ ጥቅሞቹና መብቶቹ እንዲሁም ስለመሳሰሉት ጉዳዮች ያለው ግንዛቤ ጨምሯል ። ይህ በአንድ በኩል ጥሩ ሲሆን ንቃቱ መጨመሩ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አግባብ ባልሆነ መንገድ ሲተረጎምና ስራ ላይ ሲውል ይታያል ። ይበልጥ ተገልሎ መኖር የጀመረ ማህበረሰብም እየተፈጠረ ሲሆን ይህም ለብቻው የመኖርና ከሌሎች ጋር ያለመቀላቀል ልማድ እንዲሁ ከቀድሞው ማህበረሰቦች እንዲለይ ያደርገዋል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s