የስበት ህግ

ይህ ህግ ጥንታዊ በግብፅ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በድንጋይ ላይ ፅፈው ቀርፀውት የከተቡት ህግ ለ ዘመናት ሲደበቅ የኖረ ህግ ነው ። ኤመራልድ ታብሌት የተባለው ጥንታዊ ፅሁፍ ይህንን የሚያመለክት ነው ። አሁን በዘመናችንም ሮሆልድ የተባለች አውስትራሊያዊት ይህንን ሚስጥር የተለያዩ በምእራቡ አለም የሚገኙ ፈላስፋዎችን ፣ የኳንተም ፊዚክስ ሊቃውንትና ፣ የመሳሰሉትን ባለሙያዎችን ቃለ – መጠይቅ በማድረግ ቁልጭ ባለ መንገድ ለአለም ግልፅ አድርጋዋለች ። መፅሀፏም ለራስ እገዛ (ሰልፍ ህልፕ) ከተፃፊ ሀያ ታላላቅ መፅሀፍት አንዱ ሆኖ በታሪክ ሰፍሯል ። ይህ ህግ በብዙ የሀይማኖት መፅሀፍት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ ቃላት በተደጋጋሚ ተፅፏል ።

አብርሆትን የተጎናፀፉ ጥቂት ልሂቃን (ኢንላይትድ ኤሊት) ብቻ የሚያውቁትና ለስኬቶቻቸው ለዘመናት ሲጠቀሙ የነበረ ህግ እንደመሆኑ ጥንታዊ ሰዎች ቢያውቁትም ለሌሎች ግን ሆን ተብሎ ለብዙሀን እንዳይታወቅ ሲባል ለክፍለ ዘመናት እንዲደበቅ የተደረገ ህግ ነው ።ይሁን እንጂ ህጉ በመገለፁና መፅሀፍት በመፃፋቸው የሰው ልጅ አኗኗር በአንድ ጊዜ ይሻሻላል ማለት አይደለም ።ትምህር ቱን መቀበልና ፣ በየቀኑ ተግባራዊ ማድረግ ፣ ልምምድ ማድረግና በዘመናት ውስጥ ልምድን እያዳበሩ መ ሄድ ለአንድ ሰው ስኬትን ለመጎናፀፍ አስፈላጊ ነው ።

ይሁን እንጂ በአጠቃላይ ሳይንሳዊ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት የሰው ልጅ ከእርሱ እጅግ የገዘፈና ሀያል የሆነ አለም አካል ነው ። ነገር ግን እስካሁን ድረስ በዚህ ስርአተ – ፀሀይም ሆነ በአፅናፈ – አለሙ ውስጥ ከተፈጠሩት ፍጥረታት ሁሉ ማሰብ የሚችለውና ህሊናዊ ንቃት ያለው ፍጡር የሰው ልጅ ብቻ ነው ። ስለሆነም ራሱን ከተቀረው አለም ጋር አስማምቶ ማኖር ይችላል ። የሰው ልጅ እንደ ዘርም ጭምር እነኚህን የአፅናፈ – አለሙ ህግጋት ሊረዳቸውና ለህልውናው ሲል ሊጠብቃቸው የሚገቡ ናቸው ፣ እንጂ ሊቀይራቸው የሚችላቸው አይደሉም ። ሳይንቲስቶች እንደሚነግሩን እነኚህ ህግጋት የተፈጠሩት ጊዜ ከተፈጠረ ጀምሮ ነው ተብሎ ይታመናል ። ይህ ማለት የሰው ልጅ ራሱ ከመፈጠሩና ፕላኔቶችና ፀሀይም ጭምር ከመፈጠራቸው ጀምሮ እነኚህ ህግጋት ነበሩ ወደ ፊት ከሰው ልጅ ህልውና በኋላም ይኖራሉ ።

አንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ህዝቦችም ከትክክለኛው መንገድ በሚወጡበት ወቅት በራሳቸው ላይ መከራን እንደሚያመጡ በበርካታ የአለማችን ታላላቅ ቅዱሳን መፅሀፍት ላይ ተፅፏል ። ለዚህም በታሪክ በርካታ ኒቢያቶች ፣ ትንቢት ተናጋሪዎች ተፈጥረው የበኩላቸውን መልእክት አስተላልፈዋል ፣ ህዝቦችና ነገስታት ከመንገዳቸው በሚወጡበት ወቅት በራሳቸው ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ መከራንና በብዙ ትውልዶችም ጭምር በቀላሉ የማይስተካከል መከራና ፍዳ ውስጥ ሲገቡ ታይተዋል ። በአብዛኛው ግን እነኚህ ነቢያቶች የመገደል ፣ ከአገር የመባረር እጣ ሲጥማቸውና ፣ የሚያስተላልፉትን መልእክት በየዘመኑ የነበሩ ህዝቦችም ሆነ ገዢዎች ነገሬ ብለው መስማትም መገዛት አይፈልጉም ነበረ ። ነቢዩ ኤርሚያስ በዛን ወቅት የአይሁዳውያን ንጉሰ አፈንግጦ በባሊሎን ንጉስ ላይ ሲያምፅ ለሀገሩ ለእስራኤልም ሆነ ለእስራኤላውያን ከባድ መከራን እንደሚያመጣ አስጠንቅቆት የነበረ ቢሆንም ፣ በተቃራኒው ንጉሱ በአንድ ቤት ውስጥ እስረኛ አድርጎ ዘግቶበታል ። የተፈራውም አልቀረም እስራኤል ተወራ ዜጎቿ በባቢሎን ሲበተኑ ቤት ንብረታቸውን ተፈናቅለው በጎዳና ተዳዳሪ ደረጃ በመውረድ በባቢሎን ከተሞች ለመንከራተት ተዳርገዋል ለመኖር ተገደዋል ። ንጉሱም የባቢሎን ንጉስ አይኖቹ እያየ ልጆቹን ከፊቱ እንደገደለበትና አይኑን አጥፍቶ ወደ ባቢሎን ይዞት እንደሄደና በዛውም በእስረኝነት የተቀረውን የሕይወት ዘመኑን እንዳሳለፈ መፅሀፍ ቅዱስ ይተርካል ።

አንድ ሰው እነኒህምን ህግጋት ቢጥስስ ምን ይሆናል ? ቢባል ህልውናው አደጋ ውስጥ ይገባል ። ህም ይህም በዩኒቨርስ ውስጥ ያሉትን ሁሉ ይመለከታል ። ለምሳሌ ፀሀይና ፕላኔቶች እርስ በእርሳቸው ይጋጫሉ ወዘተ ……..

እነኚህን ህግጋትን የጣሱ መንግስታት ፣ ነገስታት ፣ ሀገራትንና ህዝቦችም ጭምር ዋጋውን ይከፍላሉ ። መዝሙረ ዳዊት ላይ «ከመንገዱ ያፈነገጡ ነደው ይጠፋሉ» እንደሚለው ብዙውን ጊዜ በራሳችን ላይ መከራን የምናመጣው እኛው ራሳችን ነን ። አንድ ሰው በርካታ ተንኮሎችን ቢቀምር እነኛ ተንኮሎች ወደ ፈጠራቸው ወደ ሰውየው ወደራሱ ይመጣሉ ፣ ወይንም ማንም ምንም ውጤት የማይገኝበት የዜሮ ድምር ጨዋታ ነው የሚሆነው ።

በነገራችን ላይ ሀይማኖቶች ብቻ ሳይሆኑ አለማችንን የለወጡ በርካታ ፍልስፍናዎችም መሰረታቸው ይሄው የስበት ህግ ሆኖ እናገኘዋለን ። ምንም እንኳን ሶሻሊዝም በአንብዛኛው የአለማችን ክፍል የከሰመ ፍልስፍና ቢሆንም «ቲዎሪ (ንድፈ – ሀሳብ) በሰፊው ህዝብ ዘንድ ሲሰርፅ ፣ ቁስ አካል ይሆናል » ይላል ። ይህም ሀሳብ በህብረተሰቡ ህሊና ውስጥ ከሰረፀ ወደ ተግባር እንደሚለወጥ የሚያመለከትና ህብረተሰቡ ለዚያ እንዲተጋ የሚያሳስብ ነው ።

አንድ ሰው በዚህ ምድር ላይ የሚኖረው ስኬት በአስተሳሰብ ደረጃው ላይ የተመሰረተ ነው ።ቡድሀ «አንድ ሰው የሚሆነው የሚያስበውን ነገር ነው» ከፍተኛ የማሰብ ደረጃና ግንዛቤው ያላቸው ሰዎች ፣ በየተሰማሩበት የሚደርሱበት ደረጃም እንደዛው ከፍተኛ የሚሆን ሲሆን ፣ የአስተሳሰብ ደረጃቸው ከፍተኛ ያልሆነ ግን ብዙም የላቀ ስሌትን ሲጎናፀፉ አይታይም ። ይህም በአለም ላይ ለምናው የሀብት መዛባት ፣ የፍትህ መዛባት ፣ የጥቂቶች የአብዛኛውን የአለምን ሀብት መያዝን ፣ ጥቂቶች በስልጣን መንበሽበሽን ሲያስከትከል ለብዙሀኑ ግን አገልጋይነትንና ተመልካችነትን ብቻ ሲያጎናፅፍ ታይቷል ። በሰዎች መሀከል እኩልነት ለምንድነው እማይሰፍነው ለሚለው ዘመናትን ላስቆጠረ ጥያቄ ይህ ህግ ምላሽን ይሰጣል ።

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከአቅማቸው በላይ ትልቅ ነገርን ሲይዙ እናያለን ። ለምሳሌ ከአቅማቸው በላይ ሀብትን ፣ ስልጣንን ፣ እንዲሁም ጊዜያዊ ዝናን ሊጎናፀፉ ይችላሉ ። ነገር ግን ሰዎች ለዛ ነገር ትክክለኛው ያ ነገር የሚገባቸው ነገር ካልሆነ ያ የያዙት ነገር ዘላቂ ሆኖ ከእነሱ ጋር አይቆይም ። አንድ ሰውም ሆኑ አገራት የሚደርሱባቸው ደረጃዎች በሰው የአስተሳሰብ ደረጃ ላይ የተመሰረተ ነው ። ለምሳሌ ሰውየው ስልጣን ቢሆን ያለውና ስልጣኑን እንዴት በትክክል መጠቀም እንዳለበት እማያውቅ ከሆነ ስልጣኑን ሲያጣው መቼም ቢሆን መልሶ አያገኘውም ፣ አንድ ሰውም ሀብታም ቢሆንና ፣ ያንን ሀብቱን እንዴት መጠበቅና መጠቀም እና ማብዛት እንዳለበት እማያውቅ ከሆነ ሀብቱን አጥቶ ይደኀያል ፣ ተመል ሶም ሀብታም አይሆንም ፤ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ሎተሪ ይወጣላቸውና በአንድ ጊዜ ሀብታም ይሆናሉ ፣ ሀብት ያለውን የስበትን ህግ የማያውቁ ከሆነ ግን ተመልሰው ወደ ድህነት አዘቅት ይገባሉ ። አንዳንድ ስፖርተኞችና አትሌቶችም እንዲሁ የተሳካ ውድድርን በማደርጉበት ወቅት እንዲሁ በአንድ ጊዜ እጅግ ሀብታም ይሆኑና ነገር ግን የሽልማት ገንዘቡ ሲያልቅ ተመልሰው ደሀ ይሆናሉ ። በማንኛውንም ነበገር አንድ ሰው እማይገባውን ነገር ከያዘ ፣ በእድልም ይሁን በአጋጣሚ ሊሳካለት ቢችልም ፣ ስለዛ ነገር ት ክክለኛው እውቀትና ብልሀቱ ከሌለው ያንን ነገር መልሶ ያጣዋል ።

አንድን ነገር በጣም ስንፈልገው የማግኘት እድላችን ይቀንሳል ። ምክንያቱም ለዛ ነገር ከፍተኛ ፍላጎትን ስናነሳ ለዛ ነገር የምንለቀው ፍሪኩዌንሲ ወይም ሞገድ ከፍተኛ ይሆንና ፣ ሌሎችም በዛ ነገር ላይ ያላቸው ፍላጎት እንዲሁ ይጨምራል ፣ በዛ ነገር ላይ ያለው ውድድር እንደዛው ያይላል ። ያንን ነገር የማግኘት እድላችን እየጠበበ ይመጣል ።

በእንግሊዝኛው ፈረንጆች አንድን እጅግ ባለፀጋ የሆነ ሰውን ሲገልፁ «ማግኔት» የሚል ቃልን ይ ጠቀማሉ ። ይህም ሀብትን እንደ ማግኔት ይሰበስባል ከሚል የመነጨ ነው ። ለምሳሌ በ2012ዓ.ም .የወጣ የታክስ መረጃ ፍትሀዊነት «Tax Justice» የተሰኘ ጥናት እንዳመለከተው የአለማችን ቱጃሮች መንግስታት ማይደርሱበት ሁኔታ ከ21 እስከ 31 ትሪሊየን ዶላር እንደሸሸጉ አጋልጠዋል ይህ ገንዘብ የአሜሪካንና የጆፓንን አጠቃላይ አመታዊ ገቢን የሚያክል መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አስገራሚ አድርጎታል ። ይህን ግብር የማይከፈልበትና ሩቅ በሆነ (ኦፍ ሲ ሾር) በሚባሉ ባንኪ እንዲሁም ሚስጥርን በከፍተኛ ደረጃ በሚጠብቁና ፣ ግብርን በማያስከፍሉ የባንክ አግልግሎት በሚሰጥባቸው እንደ ስዊዘርላንድ በመሳሰሉ ሀገራት የተሸሸገ ገንዘብ መጠን ነው ። ይህም ግለሰቦች ከመንግስታት የበለጠ የአለማችንን ሀብት በእጃቸው ማድረጋቸውን የሚያሳይ ነው ።

ለአንድ ነገር የምንፈጥረው ጉጉት ፣ የጋለ ምኞት እንዲሁም ያንን ነገር ከማግኘት የምናደርው ጥረት ለዛ ነገር የሰጠነውን ደረጃ (ፍሪኩዌንሲ) ያሳያል ። ደረጃው ከፍ ባለ ቁጥር የዛ ነገር ውጤትም እንዲሁ ከፍ እያለ ይሄዳል ። ለምሳሌ ከባድ እልህ ውስጥ ስንገባ ፣ ከባድ ንዴት ሲሰማን ለዛ ነገር የምንሰጠውን ደረጃ እያሳደገው ነው የምንሄደው ፣ በውጤቱንም ለዛ ነገር ጋር ያለን ትስስር እንዲጨምርና ፣ ሌሎች ሰዎችም በዛ ነገረት ውስጥ ስሜታዊ ሆነው እንዲዘፈቁ ያደርጋል ። ኢሞሽናል ኢንቮልቭመንታቸው ይጨምራል ፣ ይህም የሚካሄደው ትግል የከረረና እና በርካታ ያልተጠበቁ ሀይሎች በዚህ ጉዳይ ላይ እጃቸውን እንዲከቱ ያደርጋል ። ይህም በየቀኑ በአለም ላይ የምንሰማቸው የፖለቲካ ትግሎች ፣ ሀገሮች በቀላሉ ሊፈታ በሚችል ነገር ውስጥ ባልፈተፈለገና ጎጂ በሆነ ሁኔታ እንዲዘፈቁ የሚያደርግና ፣ የሀገራትን ሰላም የሚያናጋ ፣ እንዲሁም ለአለም ሰላም አደጋን የሚደቅን ሁኔታ እንዲፈጠር ያደርጋል ።

ሌላው ከስበት ህግ ዋናው ደግሞ ድርጊት የራሱን ተመጣጣኝ የድርጊት ምላሽ ይፈጥራል ።ይህም የኒውተን ህግ ሲሆን «Action Creates its own Reaction» ይህም በታሪክ የሚጠቀሰው የጥንቲ ታንዊ አሶርያውያን ሲሆኑ ፣ በሀያልነታቸው ዘመን እጅግ ጨካኝና አሮጋንት የነበረ ኢማየር የነበረ ሲሆን በርካታ ጠላቶችን በማፍራቷ ይህች ሀገራ በዙሪያዋ ይገኙ የነበሩት ህዝቦት ድምጥማጧን በማጥፋት ወደ አሸዋ ፍርስራሽነት ለውጠዋታል ። ነነዌ የተሰኘችው ይህችው የአሶርያውያን ከተማ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ታሪኳ ተተርኳል ። ልክ እነሱ በሌሎች ላይ ያደረጉትን ፣ ሌሎችም መልሰው በእነሱ ላይ አደረጉባችው። በነገራችን ላይ ባቢሎያን አሶርያውያን ምንም እንኳን ተራ በተራ ሀያላን የነበሩ ቢሆንም ሁለቱም ሊንኮታኮቱና ሊጠፉን በቅተዋል ።

ይህ ህግ ለእከሌ ተብሎ የሚመጣ አይደለም ። ለአበበ ፣ ለከበደ ወይንም ለአንድ ሀገር ወይንም ሌላ ሀገር ተብሎ የወጣ አይደለም ። ኢምፐርሰናል ነው በነገራችን ላይ የስበት ህግ የሰው ልጅ በዚህ ምድር ከላይ ከመፈጠሩ በፊትም የነበረ ነው ። ሳይንሱ እንደሚነግረን የሰው ልጅ እንደውም በዚህች ምድር ላይ የቆየበት ዘመን አጭር ነው ማለት ይቻላል ፣ ስለሆነም ህግጋቱ የሰውን ልጅ ብቻ ሳይሆን የተቀሩትን ፍጥረታትን መላውን አፅናፈ – አለምን የሚገዛ ነው ።

ኤክሀርት ቶሌ እንደሚለው የዚህ «Vibration / Frequency» እርግብግቦሽ ከሴቶች ይልቅ በወንድ ላይ ጎልቶ የሚታይ ይመስላል ይላል ። ነገር ግን ህይወትን የምትሰጥና የምትነሳ የሴት ፆታ ብቻ ናት ፣ በቀድሞ ዘመን እንደ ፈጣሪ እምትታየው የሴት ፆታ የነበረችውም ለዚህ ሳይሆን አይቀርም ። በጥንታዊ ስልጣኔዎች እንደ ፈጣሪ አድርገው የሚያመልኩት ሴት አማልክቶችን የነበረውም ለዚህ ነው ። ይሁን እንጂ የወንዱ ወደ አፅናፈ – አለም የሚለቀው እርግብግቦሽ በአንፃሩ በበለጠ ሀይል የተሞላ ሲሆን በዚህም ወንዱ ከሴቷ ይልቅ የተሳካለት ሆኖ ይታያል ። ይህም ሀብትን ፣ ስልጣንን እና ሌሎችን ቁሳዊም ሆነ በአለም ላይ የገዘፉ ስብእናዎችን በማሳረፍ ወንዱ በበለጠ ጎላ ብሎ ይታያል ፣ ይሁን እንጂ ቶሌ ።

ህጎቹን መረዳት ለማንም ሰው ቀላል ነው ነገር ግን ፣ አንድ ሰው ምንም እንኳን ህግጋቱን ቢያውቃቸውም ፣ ይጠቅመኛል ብሎ የሚያደርገው ወይንም ጥሩ ነገር ነው ብሎ ያደረገው ነገር መጥፎ ቢሆንም ውጤትን ቢያመጣ አይታወቅም ፤ ለደግ ብሎ ያደገረው በመጥፎ ውጤትን አስከትሎ ቢጠናቀቅስ ? ። ስለዚህ አንድ ሰው የሚያደርገው ነገር ውጤቱ ለጥሩ ብሎ ካደረገው መጥፎ ውጤትን ቢያመጣ እንዴት ነው የሚያውቀው ፣ ይህን ማወቅ ነው ለብዙ ሰዎች ፈታኝ የሆነው ጉዳይ ።

አንዳንድ የአለማችን ታላላቅ ሰዎች ምንም እንኳን ያለውን በስልጣን ላይ ያለው ሀይል መገዳደራቸውን እያወቁ ነገር ግን ለሰው ልጅ ህልውና ሲሉ መስዋእትነትን በመክፈል በራሳቸው ላይ ስቃይን ፣ ሞትንና እስራትን ያመጣል ። ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የሚሆነው ለክርስቶስን ብንወስድ ምንም እንኳን አስተምህሮዎቹን በወቅቱ ስልጣን ላይ የነበሩት ነገስታት ፣ እንዲሁም ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን እንደሚቃወሙትና እንደሚያጠፉት ያውቅ የነበረ ቢሆንም የሰውም ዘር ነፃ ለማውጣት ግን ተጋፍጧል ። ነገር ግን ይህ ነገር የሚሆነው ፣ ግላዊ ለሆነ ጥቅም ሳይሆን ፣ ለመላው የሰው ዘር ጠቃሚ ለሆነ አላማ ነው ። ሌሎቹም እንደ ጋንዲ ፣ ማርቲን ሉተር ፣ ማንዴላ የመሳሰሉ ታላላቅ ሰዎች የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታን የሚፈታተነውን ሀሳባቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት ከባድ ተዋቃውሞን ፣ ጥላቻን ፣ እስራትን ብሎም ህይወታቸውን እስከማጣት ደርሰዋል ። ይህም ወደ ለሌሎች በጎ ኑሮን መኖር ሲሉ ፣ በራሳቸው ላይ አሉታዊ ድርጊቶችን ስበዋል ።

እንጂ በግላዊ ህይወታችን የዚህ አይነት ራሳቸውን መጥፎ ነገርን መሳብን ጉዳትን ያስከትልብናል ። የህይወታችንን መመሰቃቀል ፣ መጠላት ፣ መገለል የመሳሰሉት ችግሮችን ያመጣል ። «መከራን የሚዘሩ መከራን ያጭዳሉ» ይላል መፅሀፈ እዮብ ። ሌላው አፍራሽ ከሆኑት ስሜቶች አንዱ የፍርሀት ስሜት ነው ። ፍርሀት ራሳችንን መከላከል እንዳንችልና ፣ አሉታዊ የሆኑ ነገሮች ወደ ራሳችን በሚመጡበት ወቅት ተጋላጭ እንድንሆን እንዲሁም ወደ ማንፈልገው ነገር ውስጥ እንድንዘፈቅ የሚያደርገን ነገር ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s