መሪነትና ኢንተርፐርነርሽፕ (Leadership & Entrepreneurship)

ጥሩ መሪዎች ጥሩ (Enterperuner) ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ ። ኢንተርፐርነሮች አዳዲስ ነገሮችን የሚፈጥሩ ወይንም የነበረውን አሻሽለው የሚያቀርቡ ሰዎች ናቸው ። ነገር ግን የሁለቱ ችሎታ አንድ ላይ አብሮ በሚገኝበት ጊዜ ማለትም የመሪነትም (Enterperuner) ችሎታ ለአንድ መሪ ስራ መሳካት አስተዋጽኦን ያደርጋል ።

መሪነት የግለሰብ ብቻ ሳይሆን የህብረተሰብም ጭምር ነው ። ህዝቡ በተለይ በሀገር ጉዳይና ሰፊ ማህበራዊ ተሳትፎን በሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ ቀዳሚ መሪ ሊሆን ይችላል። ግለሰብ መሪዎችም ያስፈልጋሉ ። በርካታ ግለሰብ መሪዎች ሀገራቸውን፣ የሚመሩትን የንግድ ተቋም ፣ ወዘተ ወደ ተሻለ ቦታ በመምራት የሚታወቁ ሰዎች አሉ ። በመሆኑም የግለሰብ መሪዎች ሚና በበጎም በመጥፎም ቀላል አለመሆኑን መዘንጋት የለብንም ።

አንድ መሪ ለሌሎች ሰዎችን ችግር የሚረዳና ግላዊ የሆነው ህይወታቸውንም ጭምር የተሳካ እንዲሆን የሚጥር መሆን አለበት ።

በአሁኑ ወቅት በርካታ ስራ ፈጣሪዎች (Enterperuners) ኢኮኖሚያቸው እያደጉ ባሉ ሀገራት ውስጥ እየወጡ ይገኛሉ ። ለዚህም አይነተኛ ምሳሌዋ ቻይና ስትሆን እያደገ ባለው ግዙፍ ኢኮኖሚዋ በርካታ የአዳዲስ ስራ ፈጣሪዎች እየወጡ ይገኛሉ ። ስራ ፈጣሪዎች እያገደ ባለ ምጣኔ – ሀብት ውስጥ በቀላሉ ድልን የማግኘት እድል ሲኖራቸው ፣ እድገታቸውን በጨረሱና እየተጓተተ ባሉ የምእራብ ሀገራት ግን አዳዲስ ስራ ፈጣሪዎች የነበረውን ገበያ ድርሻ ነው እሚቀራመቱት ፣ ምክንያቱም  ሀብቱ እያያደገ ባለመሆኑ አዳዲስም ሆነ ነባር ኩባንያዎች በነበረው የገበያ ድርሻ ላይ በመወዳደር ፣ የተካረረ የገበያ ውድድር በማድረግ አንዱ አንዱን ከገበያ የማስወጣት ወይም እስከ መዋዋጥ ደረጃ የደረሰ የገበያ ውድድር ያደርጋሉ ። አዲስ የገበያ እድል ጠባብ ስለሆነ በነበረው ገበያ ላይ የገበያ ድርሻቸውን ለማሳደግ የጠነከረ ውድድርን ለማድረግ ይገደዳሉ ።

መሪነትንና የስራ ፈጠራ ጥበብ «ኢንተርፐርነርሺፕ» በጣም የተለያዩ ሲሆኑ ኢንተርፐርነርሽፕን ብንወስድ አንድ ኩባንያ በራሱ አንድ ነገርን መፍጠር ቢያቅትው እንኳን ፣ ከሌሎች መማር ይችላል ። በምእራቡ አለም ፣ ትላልቅ የሆኑ ኩባንያዎች ፣ ትናንሽና አዳዲስ የሆኑ ኩባንያዎችን በመግዛት አዳዲስ ሀሳቦችን መውሰድ ሲችሉ ፤ ለተለያዩ ዩንቨርስቲዎች ምርምር የገንዘብ ድጋፍን በማድረግም እንዲሁ ፣ አዳዲስ ሀሳቦችን ማግኘትና ፈጠራዎችን ማመንጨት ይችላሉ ። ኢንተርፐርነርሽፕ ከገበያ ሊገዛ የሚችልም ነገር ሲሆን ፤ አንድ ኩባንያ የአዳዲስ ሀሳቦች ቢያልቁበት ፣ አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦችን ሊያመነጩ ከሚችሉ የምርምር ተቋማት ወይም ግለሰቦች ሊያገኝ ሲችል ፤ ይህ የሚያሳየው አንድ ድርጅት የሚያስፈልጉትን በገበያው ውስጥ ለመወዳደር የሚያስችሉትን አዳዲስ ሀሳቦችን ማግኘት ቢያቅተው በተለየ መንገድ ሊያገኝ እንደሚችል ነው ። ትላልቅ ኩባንያዎች ከትናንሽ የተለያዩ የፈጠራ ሀሳቦችን (Patents)፣ የባለቤትነት መብቶችን (Copywrite) በግዢ ማግኘት ይችላሉ ። ይህ በተለይም በኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ዘርፍ በግልፅ የሚታይ ሲሆን ግዙፎቹ የኢንፎርሜሽን ኩባንያዎች አዲስ የተፈጠሩ ጀማሪ (Start Ups) ኩባንያዎችን በመግዛት ወደ ራሳቸው በመቀላቀል ወይንም እራሳቸውን እንደቻሉ እንዲቀጥሉ በማድረግ ራሳቸው ሊፈጥሯቸው የማይችሏቸውን  ሀሳቦችን ከውጪ በቀላሉ የሚያገኙበትና ወደ ራሳቸው የሚያዋህዱበት ስልት ነው ።

ይህ ብቻ ሳይሆን የስራ ፈጠራ ጥበብ ባለሙያዎች (Enterperuners) ከነሱ ጋር ተመሳሳይ አላማ ያላቸውን ባለሙያዎችን ማሰባሰብ ይችላሉ ። ይህም በአለም ላይ ያተሱ ታላላቅ ኢንተርፐርነሮች የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶችን የፈጠሩት ሁሉን ነገር ብቻቸውን ሰርተው እንዳልሆነ ይታወቃል ። ዋናው የስራ ፈጠራ ጥበብ አላማው ሀብትን ወይንም እሴትን መፍጠር እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ ለሰው ልጅ ኑሮ የተሻለ መደላድልን መፍጠር ነው ፣ ከእሱ ጋር ተመጣጣኝ እውቀትን ወይንም የበለጠ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች በማሰባሰብ አላማውን ማሳካት ነው ። 

ኩባንያዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት የውጭ አማካሪዎችንም ሊቀጥሩ ይችላሉ ። ነገር ግን አማካሪዎች ኩባንያውን ወይንም ድርጅቱን በቋሚነት የሚመሩ ሳይሆኑ ለአጭር ጊዜ ተቀጥረው ምክራቸውን ለግሰው የሚሄዱ ስለሆኑ የራሱን የድርጅቱን አመራር ሊተኩ አይችሉም ። ይህ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውም የአማካሪዎቹ ብቃት እንዳለ ሆኖ ምክራቸውም አስተዳደሩ ሙሉ ለሙሉ ተረድቶ ተግባር ላይውል የሚችልበት እድልም እንዳለ ሆኖ ማለት ሙሉ በሙሉ ተግባር ላይ ሊውል መቻሉም ሊያጠራጥር ይችላል ።

በአንፃሩ ግን መሪነት ከስራ ፈጠራ ጥበብ «ኢንተርፐርነርሽፕ» የበለጠ የሰዎች ባህሪን የመረዳት ችሎታን ይጠይቃል ፣ ምክንያቱን አንድ ነገርን ከመፍጠር ወይም አንድ መሪነት የበለጠ ውስብስብና ብዙ ነገሮችን ማገናዘብንና መረዳትን ስለሚጠይቅ ነው ። ይህ የሚያሳየን መሪነት በጣም እጅግ አስፈላጊና እንደ ኢንተርነርሽፕ ከውጭ ሊገኝ የማይችል ፣ እንዲሁም አማካሪዎችን በመቅጠርም ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለመቅረፍ የሚቻል አይደለም ስለዚህ አንድ ድርጅት መሪዎች ይህንን መረዳት ሲኖርባቸው ፣ የራሳቸውን የመሪነት ብቃትን ማሳደግ በምንም የማይተካ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን መረዳት ያሻል ። በአንፃሩ ግን ኢንተርፐርነሮች አንድ ስራን ፈጥረው ለአስተዳደር ሰዎች በማስረከብ ያ ነገር ትርፍን እንዲያመጣና ቀጣይ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ ።ብዙዎቹ ኢንተርፕርነሮችም በፈጠሯቸውና ከትንሽ አንስተው በገነቧቸው ኩባንያዎች ውስጥ ብዙም የማይቆዩ ሲሆን ፣ ነገር ግን የአስተዳደር ሰዎች ግን እነኛን በኢንተርፐርነሮቹ ሀሳብ የተፈጠሩትን ድርጅቶች በማስቀጠል ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲቀጥል ማስቻል ስራቸው ነው ። ለምሳሌ የማይክሮሶፍቱን ቢል ጌትስን ብንወስድ ፣ እንዲሁ የአፕል መስራችን ስቲቭ ጆብስን ብንወስድ በጀመሯቸው ኩባንያዎች ውስጥ ለረጅም ጊዜ አልቆዩም ፣ ነገር ግን ጀምረውት ለአጭር ጊዜ ቆዩ እንጂ ሌሎች አስተዳዳሪዎች (Managers) ናቸው እነኚህን ድርጅቶችን ማስቀጠል የቻሉት ። ስለሆነም የድርጅቶቹ ፈጣሪዎች ኢንተርፐርነሮች ሲሆኑ ፣ ድርጅቱን እለት በእለት የሚያስተዳድሩት የአስተዳደር ሰዎች ናቸው ።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የመሪነትን ጥበብንና ፣ ኢንተርፐርነርሽፕን ችሎታ አቀናጅተው የያዙ ሰዎች አሉ ፤ እነኚህም ሰዎች ቁጥራቸው ብዙም አይደለም ። ለምሳሌ የአፕል ሶፍትዌርና ኮምፒውተር መስራችና ባለቤት ስቲቭ ጆብስ ፣ እና ቢል ጌትስ የመሳሰሉ ሁለቱንም አጣምረው የያዙ ናቸው ፣ የስራ ፈጠራ ጥበብ ባለሙያ «ኢንተርፐርነር» ነበረ ፤ እንዲሁም የድርጅቱ መሪዎችም ነበሩ ። ነገር ግን በዚህ አይነት ችሎታ የተፈጠሩ ሰዎች ቁጥራቸው እምብዛም አይደለም ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s