የሚበልጡትን ሰዎች ከጎኑ ለማሰለፍ ዝግጁ መሆን

የአንድ መሪ ችሎታ ከሚለካባቸው ችሎታዎች አንዱ በዙሪያው በሚያሰልፋቸው ሰዎች ብቃት ነው ። አቅም ያላቸውን በዙሪያው ማሰባሰብ የሚችል መሪ ይደነቃል ብቃት ብቻ ሳይሆን ከሱ የሚበልጡ ሰዎችንም ጭምር በዙሪያው ማሰለፍ የሚችል መሪ ብልህ መሆኑን ያሳያል ። አንዳንድ ግዜ መሪዎች ከእነሱ የሚበልጧቸውንና ከነሱ ጎልተው ሊታዩ የሚችሉ ሰዎችን በዙሪያቸው ለማሰለፍ አይፈልጉም ይህም በሌሎች መበለጥን ዋጥ የማድረግ ችሎታን ይጠይቃል ።ብዙውን ጊዜ በሌሎች እንጋረዳለን ብለው የሚሰጉ ሰዎች ፣ የሚበልጧቸውን ማሰለፍ ያመነታሉ ።

ይህም ብዙውን ግዜ አንድ መሪ ከእርሱ ጋር ተመጣጣኝ ወይንም ከተቻለ የበለጡ ሰዎችን ማሰለፍ መቻል ፣ ለመምራት የሚያስችለውን አንድ የልእለ – አእምሮ ቡድንን እንዲፈጥር ያስችለዋል ። ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ባለሙያዎቸን ማሰለፍ  ለመሪው እጅግ አስፈላጊ ሲሆን ፣ እርሱ ብቻውን ሊወጣ የማይችለውን ፣ በሌሎች አቅሙና ልምዱ ባላቸው ሰዎች እገዛ እንዲወጣ ያደርገዋል ። ለምሳሌ ማይክሮሶፍት ኩባንያን በመመስረት ስኬታማ የሆነው ቢል ጌትስ ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን ሰዎች በዙሪያው በማሰለፍ ይታወቃል ። በአሜሪካም እንዲሁ አንድ ፓርቲ ተመርጦ ወደ ቤተመንግስት በሚገባበት ወቅት በሚችለው አቅም ከፍተኛ ልምድንና ብቃትን ያላቸውን ሰዎችን በአማካሪነትና የተለያዩ ሀላፊነቶችን በመስጠትስራውን እንደሚጀምር ይታወቃል ።

ነገር ግን ይህን ማድረግ ካልቻለ የእርሱን ፍላጎት በማንበብ እሱ መስማት የሚፈልገውን ብቻ በሚነግሩት ደካማ የሆኑና ጥቅም ፈላጊ የሆኑ ሰዎች ይከቡታል ። ይህም ወይ ጠንካራ ሰዎች ከጎኑ አይኖሩም ፣ ወይም እርሱ እሚፈልገውን ደካማ ፍላጎትን የሚያሟሉ ሰዎች ብቻ ባጠገቡ እንዲገኙ ያደርጋል ።

ይህ ብቻም ሳይሆን ብቃት ያላቸው ሰዎች በመሪው ዙሪያ መኖራቸው በመሪው ላይ ሊኖር የሚችለውን የስራ ጫናን ይቀንስለታል ። ሁሉንም ነገር ራሱ ከሚሰራው ይልቅ በሌሎች ሰዎች ቢታገዝ እርሱ ከዛ የበለጠትኩረትን ወደ ሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ማድረግ ያስችለዋል ። በተለይም ሀሳብን በማመንጨትና በመፈፀም በኩል የለሌሎች ሰዎች እገዛ ለመሪው የስራ መቃናት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ።ይህም ብቻ ሳይሆን መሪዎች በስራ ጫናና ሸክም ምክንያት ህመም ላይ እንደሚወድቁም ይታወቃል እንደ ልብ ድካም ፣ ስትሮክ ፣ ማርጀት ፣ መሸበት የመሳሰሉት ህመሞችንና አካላዊ ለውጦችን በብዛት አእምሯዊ የሆነ ከባድ የስራ ሸክም ባለባቸው ሰዎች ላይ በብዛት እንደሚከሰቱ ይታወቃል ። መሪ እንደማንኛውም ሰው ጤናው ይታወካል ፣ በአለማችንም ላይ በርካታ መሪዎች በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸውን ያጡ ወይንም ለከባድ ህመም የተጋለጡ በርካታ መሪዎች አሉ ፤ በአብዛኛው ምክንያቱም መሪዎች ካለባቸው የስራ ጫናና የጭንቀት ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው ። በተገቢው ሁኔታ የእረፍት ጊዜውን የሚጠቀም መሪ የእረፍት ጊዜውን ከማይጠቀም መሪ ይልቅ ጤነኛ እና ረጅም አመታትን በተሻለ የመኖርና የመስራት እድል ይኖረዋል ።

ዊድሮው ዊልሰን ወይት ሀውስ ውስጥ እያለ ሁለት ጊዜ ስትሮክ የመታው ሲሆን ፣ ኮንግሬሱ ሁለት ጊዜ የጣለው ሲሆን ፣ የናዚዎች መሪ የነበረው አዶልፍ ሂትለርም ናዚዎች እየተሸነፉ በነበረበት የመጨረሻው ዘመን በተደጋጋሚ ስትሮክ እንደመታውና ፣ ከቀኑ ውስጥ ለረጅም ሰአታት በእንቅልፍ ያሳልፍ እንደነበረ የታሪክ ባለሙያዎች የመዘገቡት ነው ። የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችንም እንዲሁ ከዋይት ሀውስ ሲወጡ ሸብተው እንደሚወጡ ይታወቃል ። ለምሳሌ ማእድን ማውጣትን ብንወስድ ለአደጋ እንዲሁም ለጤንነት አደገኛ ከሆኑ ስራዎች አንዱ ነው ። በእርግጥ መሪነት እዛ ደረጃ ላይ ባይደርስም በአለም ላይ ለጤንነት እንዲሁም ለአደጋ የሚያጋልጡ ስራዎች እንዳሉ ሁሉ መሪነት ለጤንነት አደገኛ ከሆኑ ስራዎች እንደ አንዱ ሊመደብ ይችላል፣ በተለይም ውጥረትና ጭንቀት የሚበዛባቸው የስራ ድባቦችና ሁኔታዎች ለመሪዎችም ሆነ በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች ጭንቀትንና ስጋትን ይፈጥራሉ ። 

ነገር ግን ይህ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት የተለመደ ነገር አይደለም ። በመሪዎችና በምሁራኖችና በሳይንቲስቶች መሀከል መቀራረብና አብሮ የመስራት ነገር ብዙም አይታይም ፣ ነገር ግን መሪዎች የባለሙያዎችን ምክር እንደ ግብአት ቢጠቀሙበት ለውሳኔያቸው ይበልጥ ጠቃሚ ሆኖ ያገኙታል ። በባለሙያዎች በኩልም የመሪዎቹን ደረጃ ጠብቀው መልካም ግንኙነትን ለመፍጠር ጥረትን ማድረግ ይጠበቃል ።በእርግትአንድ ትልቅ የስልጣን ደረጃ ላይ ያለ ሰውን ማገልገል የራሱ የሆነ ጥበብን ይጠይቃል ። ያ መሪ ቢሳሳት እንኳን በቀጥታ ይህን አድርገሀል ላይባል ይችላል ።  

በአብዛኛው በሀገራችንም ሆነ በብዙ የአፍሪካ ሀገራት ቲንክ ታንኮች (አዳዲስ ሀሳቦችን አመንጪ የሀሳብ ሙዳየ ተቋማት ፣ የሙያተኞች አምባ) በብዛት የሉም ። ይህ በምእራቡ አለም የተለመደ ስለሆነ መሪዎች በቀላሉ ከብዙ ቲንክ ታንኮች ሀሳቦችን የመውሰድ እድል አላቸው ፣ መሪዎች የመምራት ስራቸውን ያቀልላቸዋል ። እነኒኚህ ተቋማት በምርምርና በጥናት በበርካታ ጉዳዮች ላይ ስለሚመራመሩ ፣ የምርምራቸውንም ውጤት በህትመት ስለሚያሰራጩት በብዙ ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ ያደርጋሉ ።

ቻይናውያን ሰፊ የአመራር ልምድ ያላቸው ሲሆኑ የመተካካት ባህላቸው እድሜን እያስቆጠረ የመጣና ሲሆን መተካካቱም በመንግስት ስልጣን ላይ ብቻ ሳይሆን በፓርቲውስጥም እስካሉት ከፍተኛ የአስፈፃሚዎች ድረስ ነው ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማካይ በየአስር አመቱ የፓርቲው ከፍተኛ ስራ 9 ከሚሆኑት ውስጥ 7 ወይም 8 የሚሆኑት ይተካሉ ስለዚህ ይህ በፓርቲው ውስጥም ሆነ በመንግስት ውስጥ የሚደረገው የአመራር ለውጥ ከዋናዎቹ መሪዎች ጀምሮ ነው ።

አንድ መሪ በተለይ ግቡን ለማሳካት ስታራቴጂዎችንና ታክቲኮችን ማወቅ አለበት ። አንድ መሪ ስትራቴጂንና (Strategy) እና ታክቲክን (Tactic) ለይቶ ማወቅ ሲኖርበት ፣ ስትራቴጂ ማለት የመሪው ዋነኛው የረጅም ጊዜ ግቡ ወይም በረጅም ጊዜ እደርስበታለሁ ብሎ የሚያስበው ሲሆን ፣ በአንፃሩ ግን ታክቲክ ማለት ስትራቴጂውን እሚያስፈፅምበት የአጭር ጊዜ ብልሀቶችና መንገዶች ናቸው ። ስለዚህ የታክቲኮች ስኬታማነት ተሰባስቦ የስትራቴጂን ውጤማነትን ያረጋግጣል ። የታክቲኮች መውደቅም የስትራቴጂውን አለመሳካት ሲያመለክት ።

ይሁን እንጂ (the End Justifies the Means) የሚል አቋም ያላቸውና አንድ መሪ ስትራቴጂውን ለማሳካት ማንኛውንም ነገር ማድረግ አለበት ብለው የሚያምኑ አሉ ። መጨረሻ ግቡ ትክክል እስከሆነ ድረስ ፣ መሪው ግቡን ለማሳካት ማንኛውንም ነገር ወንጀል ሊሆን የሚችልንና ሌሎች ሰዎችን ሊጎዳ የሚችል ነገርን ጨምሮ መፈፀምና አላማውን ማሳካት አለበት ብለው የሚያምኑ ናቸው ። ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ እጅግ አደገኛ ሲሆን ሊያስከትል የሚችለው ቀውስ ከባድ በመሆኑ ከፍተኛ የማመዛዘን ችሎታን ይጠይቃል ።ታራቁ ስትራቴጂ ወይም ዋነኛው ግብ የሚባልም አለ ። tere is also what we call Grand Strategy

የአጭር ጊዜ የታክቲክ አዋቂ መሆንና የረጅም ጊዜ የስትራቴጂ ቀያሽ መሆን በጣም የተለያዩ መሆናቸውን መረዳት ያስፈልጋል ። ብዙ ጊዜ የአጭር ጊዜ ታክቲኮች ረጅም መንገዶችን የማያስኬዱ ሲሆኑ ለአጭር ጊዜ ጥቅምን ሊያስገኙ ቢችሉም በረጅም ጊዜ ግን ጉዳታቸው አመዛኝ ነው ። የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ግን የረጅም ጊዜ ግብን ወይም ስኬትን አልሞ የሚጓዝ ሲሆን በሂደትም አንድ መሪን ከመንገዱ ከሚያጋጥሙ ከብዙ አላስፈላጊ ችግሮች የሚጠብቅ ነው ነው ። የአጭር ጊዜ ታክቲክ ከረጅም ጊዜ ስትራቴጂው ያፈነገጠ መሆን የለበትም ። ብዙውን ጊዜ የአጭር ጊዜ ታክቲክን ብቻ የሚጠቀሙ ሰዎች  ረጅም ርቀት መሄዳቸው አጠራጣሪ ነው ። መሄድ ከቻሉም ብዙ ዋጋ በሚያስከፍል መንገድ ሊሆን ይችላል ። ይህም በተደጋጋሚ በብዙ መስኮች በታሪክ የታየ አጋጣሚ ነው ።

ለአጭር ጊዜ እሚጠቅም ነገርን ማስፈንና ለረጅም ጊዜ ዘላቂ የሆነ ነገርን ማስፈን በጣም የተለያዩ ነገሮች ሲሆኑ እሚጠይቁት ጥረትና እሚኬድባቸው ጎዳናም የተለያየ ነው ። ብዙ ጊዜ ምእራባውያን የረጅም  ጊዜውን በማየት ነው እሚንቀሳቀሱት ።

በነገራችን ላይ ምእራባውያንም በአንድ ወቅት የአጭር ጊዜ ታክቲክን እንደ ትክክለኛ አማራጭ የሚወስዱበት ጊዜ የነበረ ሲሆን ይህንንም አፍሪካን በቅኝ ግዛት ሲይዙና ከዚያም በኋላም ቢሆን ምንም እንኳን ሀገራቱ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ወጡ ቢባልም ብዙዎች ሀገራት ግን እውነተኛ ነፃነት አልነበራቸውም  በተለይም የኢኮኖሚ ነፃነታቸው በምእራባውያን እጅ ሆኖ ለዘመናት ሲቆይ ፣ ነገር ግን የቀድሞ ታዳጊ ሀገራት በመባል ይታወቁ የነበሩት እነኚህ ሀገራት በምጣኔ – ሀብታቸው እያደጉ ሲሄዱና ፣ በአንፃሩ ግን ምእተራባውያን የምጣኔ – ሀብት የበላይነታቸውን እያጡ ሲመጡ እነኚህ ታዳጊ ሀገራት ነፃነታቸውን ማስመለስ መጀመራቸው ይታወቃል ተጠቅመውበታል።ሆኖም ግን አሁን ጉዳቱን በአመዛኙ ሰለተረዱት እየተውት መጥተዋል።

አንድ ነገር እየተደረገ ካለበት ጊዜ ይልቅ ካለፈ በኋላ ይበልጥ ጥሩነቱ ወይንም መጥፎነቱ መሆኑ ጎልቶ ይታያል ።መጥፎ ስራ ጊዜ እያለፈ በሄደ ቁጥር መጥፎነቱ ይበልጥ እየጎላ ይሄዳል ሲሄድ በአንፃሩ ደግሞ ጥሩ ስራ ከሆነ ደግሞ ጊዜ ጥሩነትን ይበልጥ እያጎላው ይሄዳል ። ለዚህም በርካታ መጥፎ ስራዎች መጥፎነታቸው ተደጋግሞ የሚነሳና በርካታ አመታትም ካለፉም በኋላም ቢሆን መጪውም ትውልድ ጭምር የሚያፍርባቸው ሲሆኑ ፣ ጥሩዎቹም ዘመን ባለፈ ቁጥር ጥሩነታቸው እየጎላና ህብረተሰቡ የሚኮራባቸው ነው ።

ወጣት ችግርም ሲመጣ መስዋእትነትንየሚከፍለው እሱ ስለሆነ ያገሩ ጉዳይ ከሌሎቹ የትውልዱ አካላት በበለጠ ሊያሳስበው ይችላል ። በሀገራችን በ1950ዎቹና 60ዎቹ ብዙ ጊዜ የነበረው ትውልድ ይደነቃል ። ሆኖም ሁሉም ትውልድ የየራሱ የሆኑ ታሪካዊ ግዴታዎችና ሀላፊነቶች አሉበት እንደየዘመኑና ወቅቱም ይለዋወጣሉ ።በአንድ ወቅት የነበረ ችግር በሌላ ጊዜ ላይኖር ይችላል፣ ወቅቱ የሚጠይቀው ፈተናም እንደዛው ለየቅል ነው ። ሁኔታዎች ስለሚቀያየሩ የሚፈልጉትም መፍትሄ እንደዛዉ ይለያያል።

ይሁን እንጂ በመሪነት ውስጥ እሚመከረው ከሶስቱም ትውልዶች የተለዩ ትውልዶች ሰዎች መኖር አለባቸው ። ከወጣትም፣ ከመካከለኛው እድሜም ፣ እንዲሁም የረጅም ዘመን ልምድ ካላቸው የተውጣጣ እንዲሆን ነው ።ለምሳሌ የረጅም ዘመን ልምድ ያላቸው ሰዎች ከሌሉ ለወጣቶቹ ተሞክሮን እሚያስተላልፍላቸው አይኖርም ፣ መሀል ላይ ያለውም ባይኖር በእድሜ ከበለፀጉት በቅርብ ሊረከብ የሚችል አይኖርም ። የረጅም ዘመን ልምድ ያላቸው ሰዎች ብቻ ቢኖሩ ከአዲሱ ለውጥ ጋር ለመጓዝ አስቸጋሪ ይሆናል ። ስለዚህ ትውልድ ሰንሰለት ነው እንደሚባለው ሁሉ በመሪነት ውስጥም እንደዛው ሰንሰለቱን ጠብቆ እየተተካካ መሄድ አለበት ።

(Ernest and Young) የተባለው በስራ ቦታ ላይ ስብጥር ለስኬት አስፈላጊ መሆኑ በጥናቶቹ አመልክቷል ። እኩልነትን ከማረጋገጥ የፖለቲካ ተቀባይነትን «Politically Correct» ከመሆን አንፃር ብቻ ሳይሆን ለስራዎች ውጤታማነት ከተለያየ ዘር ፣ ፆታ ፣ ሀይማኖት ፣የትምህርት ደረጃ ወዘተ በስራ ቦታዎች ላይ ስብጥር መኖሩ መልካም መሆኑ ታውቋል ።

የጾታ ስብጥርን ብንወስድ ብዙዎች የእስያውያን ሴቶች ጠቅላይ ሚኒስትርና ከዛም በላይ ደረጃ ድረሰዋል ። ቻይናን ብንወስድ በርካታ የንግዱ አለም መሪዎች ሴቶች ናቸው ። በትላልቅ ኩባንያዎች ላይ ትልቅ ደረጃ ላይ ያሉ በርካታ ሴቶች ሲኖሩ እንደ ፊሊፒንስ ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ሲሪላንካ በመሳሰሉት የእስያ ሀገራት የሴቶች ተሰሚነትም ሆነ በአመራር ያላቸው ቦታ ሰፊ ነው ። ምንም እንኳን በምእራቡ አለም በርካቶቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች ሴቶች ቢሆኑም በምእራቡ አለም ግን በአንፃራዊነት ከእስያውያን ጋር ሲተያይ ትላልቅ ቦታ ላይ በብዛት አይታዩም፣ ይህ ያሳሰበው የአውሮፓ ህብረት ሴቶች በኮርፖሬሽኖች ውስጥ እንዲቀጠሩ አስደገዳጅ ህግጋትን ለማውጣት ተገዷል ። በምእራባውያን በፋይናንሱ ዘርፍ ከከፍተኛ ውድድርን በሚጠይቀው ዘርፍ ምንም እንኳን ወደ ከፍተኛው ደረጃ ቢወጡም ብዙም እንደማይቆዩና ለቀው እንደሚሄዱ ታውቋል ።

ከአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤቶች ሂላሪ ክሊንተን ቤተ-መንግስት ውስጥ የራሷን ህግጋትን ለማውጣት በመሞከሯ እኛ የመረጥነው ክሊንተንን ነው እሷን አይደለም በማለት ተቃውሞ ገጥሟት እንደነበረ ይታወቃል ። ቀዳማዊ እመቤቶች የመቀስቀስ ስራን ነው እንጂ የሚሰሩት ቀጥታ በህዝብ የተመረጡ ስላልሆኑ ፖሊሲ ማውጣት አይችሉም ። ፖሊሲ አውጪ ለመሆን ከሞከሩ ከህዝብ ሊመጣ የሚችለው ተቃውሞ ባክላሽ የከፋ ነው የሚሆነው ።

ለምሳሌ ከጥንቶቹ መሪዎች የእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤጥ ስኬታማ እንደነበረች ሲነገር የሩስያ ንግስት የነበረችው ንግስት ታላቋ ካትሪንም እንዲሁ ስኬታማ እንደነበረች ይነገርላታል ። በእኛም ሀገር እቴጌ ጣይቱ ስኬታማ እንደበሩ በታሪክ የሚታወቅና የበርካታ ሴቶችም ምሳሌ መሆናቸው ይታወቃል ። በታሪክ ሀገራችን የመጀመሪያዋን ሴት ንግስት የሰየመች መሆኗም ይነገርላታል ።

አንድ መሪ ራሱን ከሀገርና ከህዝብ እንዲሁም ከሚመራው ተቋም በላይ አድርጎ መውሰድ የለበትም ። ከዛ ይልቅ ግን እሱ የሚወስናቸውና የሚያደርጋቸው ነገሮች የሌሎች ሰዎችን ህይወትና ህልውና በጥሩም በመጥፎም ሊነኩ እንደሚችሉ በሚገባ በመረዳት በሙሉ የሀላፊነት ስሜት ስራውን መስራት አለበት ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s