የሚተማመኑበት (Dependable) መሆን

      እንኳን ግለሰብ መሪዎችን ትተን ፣ በአለማችን ላይ ከትላልቆቹ ኩባንያዎች ፣ መንግስታት ፣ ባንኮች እና መሰል ተቋማት ስራቸውን መስራት የሚችሉት መልካም ስማቸውን እስጠበቁ ድረስ ነው ። ተቋማትም ህልውናቸው የተመሰረተው ከዚህ እምነት ላይ ነወው ። ተአማኒ መሆን ለአንድ መሪ የስራ ስኬት እጅግ አስፈላጊ ነው ። አንድ መሪ በተከታዮቹም ሆነ በተቀረው ወገን ሌሎች ሰዎች የሚተማመኑበት መሆን መቻል ይኖርበታል ። አንድ መሪ የሚመራውን ተቋምንም ሆነ የራሱን መልካም ስምና ዝናን መጠበቅ አለበት ።

መልካም ስምናንና ዝናን (Reputation) ለመገንባት አመታትን የሚፈጅ ነገር ሲሆን በአንፃሩ አንዴ ካመለጠ ግን መልሶ ለመገንባት የበለጠ ጊዜን ይወስዳል ፤ የጠፋውንም ስም ለመገንባት ፈፅሞ ላይመለስም ይችል ይሆናል ፣ በቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ መስክ እየወጡ ያሉ ጥናቶች  እንደሚጠቁሙት በበርካታ ማህበረሰቦች ውስጥ (Ethical) በስነ – ምግባር የስነ –  ባህሪ ውድቀትን በስፋት መረዳት ችለዋል ፤ ነገር እየሳሳ እንደመጣ በበርካታ በዘርፉ ጥናት ያጠኑ አጥኚዎች መስክረዋል ። ይህም እጅግ አሳሳቢ ሲሆን መተማመንን ፣ መልካም ስምን በመጠበቅ ፋንታ በሌላው ማላከክን ፣ ከተጠበቀው በታች አገልግሎትን ወይንም ሸቀጥን ማቅረብን ፣ ወይንም ለምሳሌ የባጀት ፍላጎትን አጋኖ ማቅረብን የመሳሉት ሲሆኑ በተለይም የበታች ሰራተኞች የበላይ መሪዎቻቸው የዚህን አይነት ባህሪን በሚያሳዩበት ወቅት ወደ ተቀረው ሰራተኞች እንደሚስፋፉና የመሪዎቹንም ሆነ የድርጅቶቹን መልካም ስም እንደሚሸረሽር ተመራማሪዎቹ በጥናታቸው ተረድተዋል ።

በተለይ በአሁኑ ወቅት የትላል ኩባንያ ሀላፊዎች ፣ እንደዚሁም እምነታቸውን መጠበቅ ይገባቸው የነበሩ በርካታ ሰዎች እምነታቸውን ሲጥሱና ፣ በዛም ተጠያቂ ሲደረጉ ማየትና መስማት የተለመደ ሆኗል ። ለምሳሌ የምእራቡ አለም የገንዘብ ተቋማት ተአማኒነታቸው በመሸርሸሩ ኀላፊዎቻቸው ሲጠየቁ መመልከት የተለመደ ነው ። ይህም በተቋማቱ ህልውና ላይ ጥቁር ጠባሳን የተወና በህዝብ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ነው ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s