የቡድሀ መንፈስ

በዚህች ምድር ተፈጥረው ከተራመዱ እጅግ ጥቂት ታላላቅ ሰዎች ቡድሀ አንዱ እንደሆነ በርካታ የቡድሀን የህይወት ታሪክ በመረመሩ ሰዎች የተመሰከረ ነው ። በሰሜናዊ ህንድ አሁን ኔፓል ተብላ በምትታወቀው አገር ውስጥ ያለች የአንድ ግዛት ንጉስ ልጅ የነበረው ልኡሉ ቡድሀ ብዙዎች ሊያደርጉ የማይደፍሩትን ፣ ያን ሁሉ ምድራዊ ስልጣኑን ፣ ሀብቱን ትቶ መመነኑና ለሰው ልጅ መንፈሳዊ መገለጥ የደረሰበትን ለሌሎች ብርሀን መሆኑ በታሪክ አስደናቂ ድርጊት ሆኖ ይኖራል ። ቡድሀ የደረሰበት የአብርሆት ንቃት «Enlightenment» ደረጃ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ የሚመጣው የሰው ልጅ በቀላሉ እንደማይደርስበት የታወቀ ነው ።

ለሰዎች ድርጊት ከፍተኛ ርህራሄና እዝነት «Compassion» የነበረው ቡድሀ የሰዎችን ድርጊት በሚገባ የሚረዳና ፣ ሰዎች ጥፋትንም ጭምር ለምን እንደፈፀሙ በእነሱ ቦታ ሆኖ የሚረዳ ሰው ነበረ ። ቡድሀ ከዛሬ 2500 አመት በፊት ያስረተማረው ትምሀርት እርሱ ከሞተ ከጥቂት ክፍለ ዘመናት በኋላ ሀይማኖት ሆኖ በደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት እስከ ሲሪላንካና ታይላንድ ፣ ቬትናም ፣ በርማ ድረስ ሊሰራጭ የበቃ ነው ፣ ወደ ሩቅ ምስራቅም ህንድን አልፎ ቻይናን አዳርሶ ኮርያን አቋርጦ ጃፓን ድረስ በዜን ቡድሂዝም እምነት የተገለጠ ነው ።

አንዳንዶች የንጉስ ልጅ መሆኑና በማህበረሱ ውስጥ የታወቀ መሆኑ አስተሳቡንና አስተምህሮውን በቀላሉ እንዲያሰራጭ እና ተቀባይነትን ለማግኘት ረድቶታል ይላሉ ። በካስት ስርአት በምትመራው ፣ እንዲሁም ከጥንት ጀምሮ የአለም የመንፈሳዊነት ማእከል ተደርጋ የምትወሰደውና ፣ ለመንፈሳዊ መምህሮቿ የምትሰጠው ከፍተኛ ክብርና ግርማ በምትሰጠው ህንድ ምንም እንኳን የሂንዱ እምነትን ቢተችም በህይወቱ ላይ የደረሰበት ነገር አልነበረም ።

እንደማንም አዲስ ነገርን በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ለማስፋፋት እንደተነሳ ሰው ግን ከማህበረሱ ተቀባይነትን አለማግኘትንና ፣ በመንደሮች ውስጥ ሊያስተምር በሚገባበት ወቅት በድንጋት መመታት ፣ እንዲሁም ሌሎች በህይወቱ ላይ አደጋዎችም ጭምር አጋጥመውታል ። ቡድሀ በሂንዱ ሀይማኖት ላይ ያቀረባቸው ትችቶች የሂንዱ እምነት ራሱን እንዲያሻሽል ረድቷል ተብሎ ይገመታል ።

አንዳንድ ታዛቢዎች ቡድሂዝም በምእራቡ አለም በአሁኑ ወቅት ተቀባይነትን ማግኘቱ ያስገርማቸዋል ። ከጥቂት አስርት አመታት ወዲህ ሰላማዊ የሆነው የቡድሂዝም እምነት በምእራብ ሀገራት በመስፋፋት ላይ ነው ። በነገራችን ላይ ቡድሂዝም ብቻ ሳይሆን የባሀኢ እምነትም በአሁኑ ወቅት በምእራቡ አለም ሰፊ ተቀባይነትን እያገኙ ያሉ የምስራቃውያን እምነቶች ናቸው ።

በአለም ላይ ታላላቅ መንፈሳዊ የመገለጥን ብርሀን ለሰው ልጅ ይዘው ብቅ ያሉ የተከሰቱት ከዚሁ ከምስራቁ የአለማችን ክፍል ነው ፣ እነኚህ የምስራቅ መንፈሳዊ ፀሀዮች ፣ እየሱስ ክርስቶስ ፣ ቡድሀ ፣ በሀኡላ ፣ ነቢዩ መሀመድን የመሳሰሉ ለሰው ልጅ ብርሀንን የፈነጠቁ ናቸው ።  

Advertisements

የነፍስ ሚስጥር

የነፍስን ሚስጥር ያልተረዳ ወይንም በመረዳት ላይ ያልተመሰረተ ሀይማመኖት እድሜ ሊኖረው መቻሉ መኖሩ ያጠራጥራል ። የፕሌቶ ታሪክ እንደምንረዳው ፕሌቶ በነፍስያ ጉዳይ እጅግ ከመመሰጡ የተነሳ ስለ ነፍስ ብዙ ብዙ ማለቱ ይነገርለታል ።

ሁሉም የአለማችን ሀይማኖቶች የነፍስን ህልውና በአብዛኛው አይክዱም ። ከዝግመተ- ለውጥ ሳይንቶስቶች በስተቀረ በመንፈስ የሚያምን እምነት በነፍስ ህልውና አይክድም ። ነገር ግን በዝግመተ- ለውጥ የሚያምን ከሆነ የነፍስንም ሆነ የመንፈስን ህልውና ጨርሶ አይቀበልም ። ሀይማኖቶች የየራሳቸው መንፈሳዊ ሊቃውንት «ሚሴቲክስ» አሏቸው ። የመንፈስን ሚስትጥር በቅጡ የማይረዳ ሀይማኖት ፣ ሀይማኖት ሆኖ ሊቀጥል እንደማይችል ከጥንት ጀምሮ የታወቀ ነው ።

በፍልስፍናው አለም ውስጥ እጅግ አከራካሪ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ መንፈስ አለ ወይስ የለም የሚል ሲሆን ፣ ከዚህም በተጨማሪ መንፈስ ህልውና አለው ወይንስ የለውም የሚል ነው ። ማንም ሰው እንደሚያውቀው በአለም ላይ የሰው ልጅ ብቻ አይደለም ህይወት ያለው ፍጥረት ። እንሰሳትና እፅዋትም ጭምር ህይወት አላቸው ፣ ነገር ግን ነፍስም ሆነ መንፈስ የላቸውም ። የሰው ልጅ ጋር ብቻ ነው ነፍስ አለው ወይ የሚል ጥያቄ የሚነሳው ። የቁስ አካል ፈላስፎች ነፍስ የለችም ብለው እንደሚያምኑ ይታወቃል ።

ነፍስም ሆነ መንፈስ ከሰው ልጅ ጋር ተያይዘው የሚነሱበት ምክንያት የሰው ልጅ ማሰብ የሚችል ፍጡር በመሆኑ ነው ። የሰው ልጅ ህሎናዊ ንቃት እና የማስሰብና የማገናዘብ አቅም ያለው ፍጡር በመሆኑ ምክንያት ያንን ህሊናዊ ንቃቱን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሊያስተላልፍ የሚችልም ጭምር ነው ።

ማህበረሰባዊ ለውጦች

በአሁኑ ወቅት ከዚህ በፊት ተሰምተው የማይታወቁ ጥቃቶችና ድርጊቶችን ማስማት የተለመደ ነው ። የትዳር አጋሩን በጥይት ደብድቦ ገደለ ፣ በጩቤ ወጋ ፣ ሰዎችን በተኙበት ጭፍጭፋ ገደለች ወዘተ  የመሳሰሉትን ዜናዎችን መስማት የተለመደ ሆኗል ። ቀድሞ የዚህ አይነት ድርጎቶች በምእራቡ አለም መስማት የተለመዱ ሲሆን አሁን ደግሞ በኛም ህብረተሰብ ዘንድ የዚህ አይነት ዜናዎችን መስማት የተለመደ ሆኗል ።

በምእራቡ አለም እጅግ አደገኛ የሚባሌ ወንጀለኞች በእስር ቤቶች ውስጥ ከሰው ጋር ሳይገናኙ በአንድ ክፍል ውስጥ ለብቻቸው ለብዙ ሰአት በቀን ውስጥ እንደሚታሰሩ የሚታወቅ ነው ። በመምእራባውያን ዘንድ የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብቻ እየመረጡ እያሳደዱ በጭካኔ የሚገድሉ ፣ ለምሳሌ ሴተኛ አዳሪዎችን ብቻ እየፈለጉ ራቅ ወዳለ ቦታ እየወሰዱ ህይወታቸውን የሚያጠፉ ፣ ህፃናቶት ላይ ወሲባዊ ጥቃትን የሚፈፅሙ ብለውም የሚገድሉ የመሳሰሉ አደገኛ ግለሰቦች ሌሎችን በማሰቃየት ወ ይም የሌሎችን ስቃይ በማየት የሚደሰቱ «ሳዲስት» የሆኑ በማህበረሰቡ ውስጥ አሉ ። የዚህ አይነት ሰዎች ተደጋጋሚ ቅጣታቸውን ጨርሰው ከእስር ቤት ቢለቀቁም ከእስር ቤተት ወጥተው በዚህ አደገኛ ድርጊታቸው በተደጋጋሚ ሲገኘ የተቀረውን እድሜ ዘመናቸውን ከእስር ቤት ሳይወጡ እንዲኖሩ የተፈረደባቸው አሉ ።  

እነኚህ ጥቃቶች «ፆታዊ» ጥቃቶች ብቻ አይደሉም ። ለዚህ ምክንያቱ የቁጥር ልዩነት ብቻ ካልሆነ በስተቀር ፣ በሁለቱን ፆታዎች አማካይነት ፆታን ሳይለዩ ተደጋግመው የሚታዩ ስለሆነ ነው ። ከዚያ ይልቅ ቀድሞ የነበረው የህብረሰተሰቡ መቻቻል ፣ ልዩነቶችም በሰላማዊ መንግድ የመገፍታት አዝማሚያዎች እየደበዘዙ መምጣታቸውን የሚያሳዩ ናቸው ።  

የተዛባ የሀብት ክፍፍል

የአለምን የምጣኔ-ሀብት ታሪክ የሚመለከቱ ታዛቢዎች እንደሚናገሩት አለማችን ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ማለትም ከሶሻሊዝም ስርአት መመስረት ወዲህ በአለም ላይ ከፍተኛ የሀብት ልዩነት እየተከሰተ ነው ። የተዛባ የሀብት ልዩነት እ.ኤ.አ. 1789 ከተከሰተው የፈረንሳዩን አብዮት ጨምሮ በአለማችን ላይ ለተከሰቱ አብዮቶችና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ዋነኛ መንስኤ ነው ። 

ከበለፀጉት ሀገራት አሜሪካን ብንወስድ በዚህች ሀገር ያለው የሀብት ልዩነት በአለም ከፍተኛ ከሚባሉት አንዱ ነው ። ግብር ይጨመር ፣ አይጨመር የሚለው የአሜሪካ ፖለቲከኞች የምርጫ መከራከሪያ አጀንዳ ፣ የርእዮተ አለምና የኢኮኖሚ ፍልስፍና ጉዳይ ከሆነም ውሎ አድሯል ። የአሜሪካ ህልም «American Dream» ወደ «American Nightmare » ወደ የአሜሪካ አስፈሪ ቅዠት ተቀይሯል ብለው አሜሪካንን የሚተቹ ሰዎች ይናገራሉ ። በአሁኑ ወቅት በታላላቅ የአሜሪካ ከተሞች እምብርት ውስጥ በርካታ «ጌቶዎች» የድሆች የመኖሪያ ሰፈሮች እየተፈጠሩ እንዲሁም ይህን ተከትሎም ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ የወንጀል መበራከት ፣ እና የእስር ቤቶች መጨናነቅ እየታየ ነው ።

ዊንስተን ቸርቺል በአንድ ወቅት እንተናገሩት የካፒታሊዝም ስርአት ዋነኛው ችግር «የሀብት ክፍፍል አለማድረጉ» ነው ፣ ይህም ካርል ማርክስ የካፒታሊዝም ስርአት ዋነኛ ውስጣዊ ተቃርኖ በሚል የገለፀው ይሄን የተዛባ የሀብት ክፍፍል ሲሆን መንስኤውም ካፒታል ጉልበትን ስለሚበዘብዝ እንዲሁም የካፒታል ገቢ እያደገ ስለሚሄድ ፣ በአንፃሩ ግን የሰራተኛ ደሞዝ ዋጋ ግን የዚያን ያህል አለመጨመሩ ነው ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መግለጫ መሰረት በሀገራችን ያለው የሀብት ክፍፍል ፍትሀዊ እንደነበረ ተገልጿል ። ይህም እ. ኤ. አ. በ 2013 ዓ.ም. በተገለፀው መሰረት አገራት በአፍሪካ ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል ካለባቸው ሀገራት አንዷ ናት ። ይህም መልካም ዜና ሲሆን በዚህም ለወደፊቱ የሀገሪቱ ውስጣዊ የፖለቲካ መረጋጋት መሰረት ነው ።

የሀገራችን የሀብት ክፍፍል ፍትሀዊ ሊሆን የቻለው የራሱ ምክንያቶች አሉት ። ከ1966 አብዮት በፊትመ ምንም እንኳን በጊዜው ኮኢፊሸንት የሀገራችን የሀብት ክፍፍል ተሰልቶ ማወቅ ባይቻልም የነበረው የሀብት ክፍፍል እጅግ የተዛባ እንደነበረ መረዳት ይቻላል ። በነበረው የፊውዳል ስርአት ምክንያት ዋነኛው የሀብት ምንጭ የነበረው መሬት በጥቂት ታላላቅ ባላባቶች የተያዘ ስለነበረ ነው ።

በዚያን ወቅት የነበረው የሀብት ክፍፍል እጅግ የተዛባ በመሆኑ ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አብዮት ማካሄድ አስፈልጓል ። ከዚያ በኋላ በ 1966ቱ አብዮት ወደ ስልጣን የመጣው «ካፒታሊዝም ሊያቆጠቁጥ ሲል ደረስኩበት» የሚለው ደርግ በሶሻሊዝም ስርአቱ ዋና ዋና የሆኑትን የሀብት ምንጮችን በመውረሱ ምክንያት ሀገሪቱ ስትደኀይ ዊኒስተን ቸርችል እንዳሉት የሶሻሊዝም ክፋቱ «ሁሉንም ማደህየቱ» ነው ። በዚሀም ምክንያት በደርግ 17 አመታት ውስጥ የግል ሀብት ስላልነበረ የተፈጠረ ሀብት አለነበረም ። ሁሉም እኩል ሲደኀይ እንዲሁም የግል ሀብት እንዲፈጠር የነበረው ሁኔታ ስላልተመቻቸ ድህነቱ ተንሰራፍቶ ቆይቷል ። መጀመሪያም ሀብት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ የተዛባ የሀብት ክፍፍል ሊኖር እንደማይችል የታወቀ ነው ። ከዚህም በተጨማሪ በነበረው ጦርነት ምክንያት ራሱ መንግስትም ለልማት የሚያውለው በቂ ገንዘብ አልነበረውም ፣ በዚያን ወቅት መንግስት እንኳን የራሱን በጀት መሸፈን የሚያቅተው ጊዜ እንደነበረ የታወቀ ነው ።

ከዚያ በኋላ ግን የደርግ ስርአት ከወደቀ በኋላ የኢህአዴግ ስርአት ሲመጣ የግል ሀብትን የሚፈቅድ አዋጅን በማውጣቱ እንዲሁም የግል ኩባንያዎች ባንኮችን ጨምሮ እንዲቋቋሙ ስለፈቀደ የግል ኩባንያዎች ማቆጥቆጥና የግል ሀብት መፈጠር ጀምሯል ። አሁን ያለበት ሁኔታ ሀብት መፈጠር የጀመረበት ሁኔታ ነው ። ሀብት መፈጠር ሲጀምር የሀብት ልዩነቱ በአንድ ጊዜ አይሰፋም ፣ ነገር ግን ውሎ አድሮ የሀብት ልዩነቱ እየሰፋ መሄድ ይጀምራል ። ይህም በግልፅ በመታየት በሚጀምርበት ወቅት ግን ስለ ሀብት ክፍፍል ፍትዊነት ማውራት አስፈላጊ እየሆነ ይሄዳል ።

ምንም እንኳን የሀብት ክፍፍሉ በሀገራችን ያለው ፍትሀዊ ቢሆንምና ገና ወደ አሳሳቢ ችግር ደረጃ ባይደረስም ፣ የምጣኔ – ሀብት እድገት በራሱ ፖለቲካዊ ችግርን እንደማይፈታ የታወቀ ነው ። ለዚህ  ምክንያቱ በአንድ በኩል እድገቱ ለብዙሀኑ ሳይሆን ለጥቂቶች ትላልቅ ኩባንያዎች እና ነጋዴዎችና የህንፃና የተለያዩ ባለንብረቶች እጅ ስለሚገባ ሲሆን የብዙሀኑን ህዝብ የምጣኔ-ሀብት ችግር ወዲያው ስለማይቀርፍ ፣ እንደውም የዋጋ ግሽበትን በማባባስ ለመካከለኛውና ለደሀው ህብረተሰብ ክፍል የተባባሰ የኢኮኖሚ ችግርን ሊፈጥርና ብሶትን ሊፈጥር ስለሚችል ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ችግሮች በራሳቸው ከኢኮኖሚ የተለየ መሰረትና ምክንያትና የራሳቸው አካሄድና ምክንያት ያላቸው መሆናቸው የኢኮኖሚ ማደግ ብቻውን የአንድን አገር የፖለቲካ ችግር ሊቀርፍ አይችልም ።

ብዙውን ጊዜ የፖለቲካ ችግሮች ከሰብአዊ መብት አያያዝ ፣ ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅና ከዲሞክራሲ ባህል መዳበርና ከነፃ ምርጫ ጋር የተያያዙ ናቸው ። ለምሳሌ ቻይናን ብንወስድ ምንም እንኳን ቻይና ምጣኔ-ሀብቷ አድጎ በአለም ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ብትደርስም ፣ በአንድ ፓርቲ ማለትም በኮሚኒስት ፓርቲው የበላይነት በምትተዳደረው እንዲሁም በማ ህዝባዊ ምርጫንና ነፃ ፕሬስን የማታውቀው ቻይና ፣ በፖለቲካ ነፃነት በኩል ግን ከአሜሪካም ሆነ በአጠቃላይ አገራዊ ምርት ከበለጠቻቸው የአውሮፓ አገራት ጋር ጨርሶ አትወዳደርም ።   

አንድ ምጣኔ – ሀብት እድገት ማሳየት በሚጀምርበት ወቅት አብዛኛው እድገት ወደ ትላልቅ ኩባንያዎች ፣ ባንኮችና የገንዘብ ተቋማት እንዲሁም በዘመናዊው ምጣኔ – ሀብት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦት ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የታወቀ ነው ። እንደውም በአንዳንድ አገራት እድገት በሚመጣበት ወቅት የዋጋ ግሽበትን ስለሚፈጥር በመካከለኛውና በዝቅተኛው የገቢ ደረጃ ያለውን የህብረተሰብን ክፍል የሚያደኀይበት ወቀት በተደጋጋሚ በተለያዩ አገረት ሀገራት ተስተውሏል ። በምእራቡ አለም ሳይቀር ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ይታይ በነበረበት በ1970ዎቹና 80ዎቹ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሲታይ ነበረ ።      

በአገራችን ያለው የሀብት ክፍፍል ከህንድ ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው ይችላል ። በህንድ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት ቢያድግም ፣ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሆች በዚያች ሀገር አሉ ። በአንፃሩ እጅግ ሀብታም የሆኑና በአለም ስማቸው የሚጠሩ በርካታ ሀብታሞችም በዚህችው አገር ይገኛሉ ። ህንድ በአለም በርካታ ድሆች ያለባት ሀገር የመሆኗ እውነታ በምጣኔ – ሀብት እድገቷ ሊረጋገጥ አልቻለም ። ቻይና በአንፃሩ ከህንድ የተሻለ የሀብት ክፍፍል ያላት ቢሆንም ቻይናም ብትሆን ፣ በሀብታምና በደሀ ዜጎቿ መሀከል ያለው የሀብት ልዩነት የቻይናን አመራር መሳሰብ ጀምሯል ።

«መንጋውን» መጠበቅ

አንድ የሀይማኖት የመጨረሻ የበላይ ምድራዊ መሪ ሲሾም «መንጋውን» ለመጠበቅ መሆኑ ተደጋግሞ ይነገራል ። ብዙሀኑ ህብረሰተሰብ ያ ህብረተሰብን የሚመሩት የሚያውቋቸውን ነገሮች ላይረዳ ይችላል ። ቢነገረውም ግንዛቤው ሊረዳውም ላይረዳውም ይችላል ። ይህም የሀይማኖትን ሚስጥር ፣ በፖለቲካ በምጣኔ-ሀብት በመሳሰሉት በከፍተኛ የአመራር ደረጃ ያሉ ሁነቶች ቢገለፁም ምን ያህል ሰው ሊገነዘባቸው ይችላል የሚለው አጠያያቂ ነው ። ሙሴ እግዝአብሄር ሚስጥሩን ከገለፀለትና ሚስጥሩን ከተረዳ በኋላ ለእስራኤላውያን ሲያስረዳ «ደንቆሮና አላዋቂ የሆንክ ህዝብ ሆይ፣የምንልህን ስማ» ያለው ይህን ያለመረዳት ችግር ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው ። እንዲሁም ህዝቡ እሱ ካስቀመጠላቸው መንገድ እያፈነገጡ ወደ ሌላ አምልኮ በሚሄዱበት ወቅት ሙሴ አጥፊዎቹን ከመቅጣት ወደ ኋላ አላለም ። ሙሴ  በህይወት ዘመኑ መጨረሻ ላይ ለእስራኤላውያን ባደረገው ኑዛዜ ክፉዎችና የናትታዘዙ ስለሆናችሁ እኔ ከሞትኩ በኋላ «ከባድ ችግር ያገኛችኋል» ብሎ እስራኤላውያንን አስጠንቅቋቸው እንደነበረ መፅሀፍ ቅዱስ ይገልፃል ። ይህም አንድ ህብረተሰብ በፖለቲካም ሆነ በሀይማኖት መሪዎች እጅግ እንደሚያስፈልጉት መሪ የሌለው ህዝብ ጠባቂ እንደሌለው መንጋ ማለት ነው ተብሎ ይገለፃል ።

በአንድ ህብረሰተሰብ ውስጥ ፀሀፊዎችና ደራሲዎች ፣ የፖለቲካና የጥበብ መሪዎች ፣ ደራሲያን ፈላስፎችና የሀይማኖት መሪዎች የአንድን ማህበረሰብን አካሄድ የሚረዱ ናቸው ፣ የወደፊት አቅጣጫውን የሚጠቁሙ ልሂቃን «Elits» ናቸው ።

          ብዙሀኑ ህብረተሰብ ለዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውንና ትክክል ነው ብሎ ለምእተ አመታት ሲያምንበት የኖረውን አስረተሳሰቡን ፣ አመለካከቱን ሊቃረኑ ወይንም ሊፈታተኑ ለሚመጡ ምህረት የለውም ። ከእሱም በስተጀርባ ያው ባለው ወቅታዊ ሁኔታ ተጠቃሚ የሆኑ የአገዛዝ ሀይሎችም እንደሚኖሩ ግልፅ ነው ። ለዚህም አይነተኛ የሚሆነው በሶቅራጥስና በእየሲሱስ ክርስቶስ ላይ የተፈረዱት የሞት ፍርዶች አይነተኛ ማሳያዎች ናቸው ።

ቁሳዊው ህብረተሰብ

ምእራባውያን በካቶሊክ አስተምህሮ ላይ በማሮርቲን ሉተር አማካይነት አምፀው «ሪቮልት» አድርገው የፕሮቴስታንት ሀይማኖትን ከተነሳ በኋላ ፣ ሀብትን መፍጠር ቅዱስ ተግባር መሆኑን ካሰመሩበት በኋላና ታላላቅ ፈላስፎቻቸውም ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ሀብትን የመፍጠሩን ሂደት ሲያጠናክሩ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ግስጋሴያቸውም ላለፉት አምስት መቶ አመታት ቀጥለውበት ቆይተዋል ። ለምሳሌ ጀርመናዊው የማህበሰረብ ሊቅ ማክስ ዌበር እንደሚለው የካቶሊክ ሀይማኖት ስለ ስራና ሀብት ያለው አመለካከት «ወርክ ኤቲክ» ለብልፅግና እንቅፋት ነው የሚል ሲሆን ፣ እንዲሁም የክርስትና ሀይማኖት «ሀብታም መንግስተ-ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላታል» ሲል ይናገራል ። የተሀድሶ «ሪፎርሜሽን» ዘመን በሉተር አማካይነት መንገዱ ከተቀደደ በኋላ ግን እንደውም አንድ ሰው ሀብታም ሲሆን እግዝአብሄር ይወደዋል ፣ አንድ ሰው ሀብትንና ፀጋን የሚያገኘው እግዝአብሄር ሲወደው ነው በሚል አስተምህሮ ተተክቷል ።

በአንፃሩ ግን አይሁዳውያን ከጥንት ጀምሮ ሀብትን በተመለከተ እንደ ክርስትና ሀይማኖት ብዥታን የሚፈጥሩ አመለካከቶች ነገሮች የሉባቸውም ። አይሁዳውያን አራጣ ማበደርም ሆነ ማንኛውንም የንገድ ስራን ሲሰሩ የኖሩ ሲሆን ጥንትም ሆነ በዛሬው ዘመን በአለም ላይ ሀብታሞች አይሁዶች ዋነኞቹ ናቸው ። ለምሳሌ የቬኒሱ ነጋዴ የተሰኘው የዊሊያም የሸስፒር ስራ ሻይሎክ የተሰኘው ጨካኝ አራጣ አበዳሪ አይሁድ የሰውን ስጋ እስከመቁረጥ ድረስ ጭካኔ እንደነበረው የሚያሳይ የልቦለድ ስራ ነው ።

ከመፅሀፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ሙሴ ጀምሮ አብረሀምም ሆነ የሱ ልጆች ያእቆብ ፣ እንዲሁም የግብፅ ፈርኦን አማካሪና በጅሮንዱ የነበረው ፈርኦንን እጅግ ባለፀጋ ያደረገው የነበረው ዮሴፍ እንዲሁም ታጋሹ እዮብ ጭምር በዘመናቸው እጅግ ባለፀጋና ሀብታም እንደነበሩ መፅሀፍ ቅዱስ ያረጋግጣል  ። የጥንት ባቢሎናውያንና ፣ የግብፅ ስልጣኔ ባለቤት የነበሩት ፈርኦኖችም እጅግ ሀብታምና ባለፀጋ እንደነበሩ በታሪክ የተረጋገጠ ሀቅ ነው ።

በእርግጥ መፅሀፍ ቅዱስ አንድ ሰው ሳይሰራ መብላት እንደሌለበትና እግዝአብሄር አዳምን «ለፍተህ በወዝህ እንጀራን ትበላለህ» ብሎ እንዳለው መፅሀፍ ቅዱስ ገና ከጅምሩ ይገልፃል ። ሰው እስከ ሰራ ድረስ ሀብትንና ፀጋን ለማግኘት መሆኑም አሌ አይባልም ።

በአሁኑ ዘመን ጨካኝ መሆን እንደማወቅና እንደ ትክክለኛ የማወቅ ወይንም አራዳ የመሆን ድርጊት ተደርጎ  የሚወሰድበት ወቅት ነው ። በአሁኑ ወቅት የምንኖርበት ማህበሰረብ ስኬትንና የሚለካው በቁሳዊ ሀብት መሰብሰብ እና ማከማቸት ነው ።

ቁሳዊ ሀብትም የህይወትን ትርጉም የሚሰጥ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል ። ይህም በምእራቡ አለም ምንም እንኳን በምእራባውያን ከፍተኛ ሀብትን ቢፈጥሩም ፣ በተቃራኒው ግን ለገንዘብ ብሎ እርስ በእርሱ የሚገዳደል እና እጅግ የላላ ስነ- ምግባራዊ መሰረት ያለውን ህብረሰተብን ነው የፈጠሩት ። ለቁሳዊ ሀብት ስኬት መሯሯጥ የሚቅበዘበዝና ፣ እረፍት የለሽ ፣ እንዲሁም ባለው የማይረካ ህብረተሰብ እንዲፈጠር አድርጓል ። ይህ ከምእራብ ሀገራት የፈለቀው አስተሳሰብ ወደ ተቀረው ዓለምም የተስፋፋ ሲሆን

በአንድ በኩል ህብረተሰቡ ሌላ ጥያቄ እንሰዳያነሳ ይሄው ቁሳዊ ፍላጎትህ ተሟልቶልሀል በሚል አቅጣጫውን ለማስቀየር በመሪዎቹ በኩል ጥረት እንደሚደረግ ልብ ይሏል ። ይህም ሌላ ማህበረሰባዊ እድገት ማለትም መንፈሳዊ እና ህሊናዊ ንቃቶች ሳይኖሩት ቁሳዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩርና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮች ግንዛቤ የሌለውና ጥያቄን የማያነሳን ህብረተሰብ ለመፍጠር ረድቷል ።

እኩልነትን ማስፈን

በአለም ላይ በየትኛውም አገር ያለው ዋነኛ ፖለቲካዊ ሆነ ምጣኔ-ሀብታዊም ሆነ ሌላ ጥያቄ እኩልነትን ማስፈን ነው ። ታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ፕሌቶ ሪፐብሊክ በተሰኘው ታላቁ ስራው ላይ ዋነኛው ጥያቄው የነበረው የፍትህ መስፈን ነው ። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ እኩልነትን ማስፈን በጣም ውስብስብና አስቸጋሪ ጉዳይ ነው ። ወደ ኋላ መለስ ብለን የሰውን ልጅ ሰብአዊ መብትን በማስከበር በኩል እጅግ ተራምደዋል የምንላቸውን ምእራባውያንን ታሪክ ብንመረምር አሁን የደረሱበት ደረጃ ላይ እንኳን በቀላሉ አልደረሱም  ። ምእራቡ አለም ሰውን በባርነት የሸጠበትና የገዛበት ፣ በባርነት የሰዎች  ጉልበት በነፃ የተበዘበዘበት ፣ ሰዎች እንደ እቃ የተሸጡበት ዘመን በጣም ሩቅ አይደለም ። ከዚያም በኋላ ቢሆን በአሜሪካን አገር ያሉ ጥቁሮች መብታቸውን ለማስከበር እጅግ መራራና ፣ እልህ አስጨራሽ ትግልን አካሂደዋል ። የሴቶችንም መብት ብንመለከት ሴቶች ከወንድ እኩል መብታቸውን ለማስከበር እንዲሁ ትግልን አካሂደዋል ። አውሮፓዊቷ ስዊዘርላንድ እንኳን ሴቶች የመምረጥ መብታቸውን ያረጋገጠችው እ.ኤ.አ. በ1974 እንደሆነ በታሪክ የተመዘገበ ነው ።

የእኩልነት የመስፈን ጥያቄ የህግ ፣ የፖለቲካ ወይንም የአንድ ሰው ወይንም ግለሰብ መብት የመከበር ጉዳይ ብቻም ሳይሆን የአጠቃላይ የማህበረሰብ ደህንነትና ፣ የአንድ ማህበረሰብ ሞራል «ስነ- ምግባር» የማረጋገጥ ጉዳይ ነው ።

መብቶች በህግና በህገ-መንግስት ቢረጋገጡም ወደ ተግባር መለወጡ ግን ሌላ እጅግ ፈታኝ ስራ ነው ።  ይህም በአሜሪካን አገር በግልፅ የሚያታይ ነው ። ምንም እንኳን አሜሪካ በህግ ለአፍሪካ አሜሪካውያን ከነጩ እኩል መብታ ቸውን ያረጋገጠች ብትሆንም ፣ እንዲሁም ጥቁሩ ባራክ ኦባማ ተመርጠው ዋይት ሀውስ ገብተው አሜሪካንን መምራት የቻሉ ቢሆንም ፣ በተግባር የጥቁሮች የኑሮ ደረጃ ፣ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚሰጣቸው ቦታ አሁንም ብዙም አልተለወጠም ፣ ገና ብዙ የሚቀረው ነው ። በዚያች አገር ብዙዎች በድህነት የሚማቅቁት ፣ በእስር ቤቶች ውስጥ በብዛት የሚገኙት እንዲሁም ከፍተኛው የስራ አጥ ቁጥርና የመሳሰሉት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በጥቁሮች ዘንድ ጎልተው ይታያሉ ።

የእኩልነት መከበር ጉዳይ በአንድ ወቅት  ተከብሯል ተብሎ የሚዘጋ ሳይሆን በዘመናት ሂደት ውስጥ ቅርፁንና ይዘቱን እየቀየረ የሚመጣ ጉዳይ ነው ። በነገራችን ላይ ምእራባውያን አሁን የደረሱበት ደረጃ ከፍተኛ ቢሆንም አዳዲስ የመብት ጥያቄዎች በራሱ ምእራቡ አለም ዘንድ እያቆጠቆጡ ነው ። ለምሳሌ በማይድን ህመም የሚሰቀዩ ሰዎች የመሞት መበት ፣ አደንዛዥ እፆችን የመጠቀም መብት፣ የማስወረድ መብት፣ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ጥያቄና እንዲሁም የማደጎ ልጅ የማሳደግ መብት ወዘተ የመሳሰሉት አሁንም ድረስ የምእራብ አገራትን የፖለቲካ ምርጫ ውጤትን የሚወስኑ እና የምእራባውያንን ህብረተሰብ እኩል በእኩል የሚከፋፍሉ ጉዳዮች ከሆኑ ውለው አድረዋል ።    

እኩልነት በፆታዎች መሀከል ፣ በተለያዩ ዘሮች ፣ በተለያየ የሀብት ደረጃ ባላቸው መሀከል ፣ የተለያየ የእውቀት ደረጃ ባላቸው ፣ የተለያየ ሀይማኖትን በሚከተሉ ማህበረሰቦች መሀከል እኩልነትን ማስፈን በሰው ልጅ የታሪክ ዘመን የነበረና ወደፊትም የሚኖር ጉዳይ ነው ።

ነፃነት

ነፃነት ማለት ምን ማለት ነው ? ነፃነት ምንድነው ? ነፃነት ለብዙ ሰዎች ውጫዊ የሆኑ የነፃነት መገለጫዎች ማለትም ከቅኝ አገዛዝ ነፃ መውጣት ፣ ከብዝበዛ መላቀቅ ፣ በኢኮኖሚ ራስን መቻል ወዘተ አድርገው የሚወስዱት ነገር ነው፣ ግን ነፃነት ከላይ የተጠቀሱት ማለት ብቻ አይደለም ።
ነፃነት ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ብቻ የሚገለፅ አይደለም ። ከዚያ ይልቅ እውነተኛው ነፃነት ውስጣዊ በሆኑ ነገሮች የሚገለፅ ነው ። ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ነገር የህሊናዊ ንቃት «ኮንሸስነስ» ማደግ ሲሆን በዚህም ምክንያት ህሊናዊ ንቃት አንድ ሰው በሁለት መንገድ ሊጎናፀፍ ይችላል ። አንኛው ሰውየው ያሳለፋቸው አስቸጋሪና ውጣ ውረድ የበዛባቸው ሁኔታዎች ለሰውየው የተሻለ ንቃትን እንዲጎናፀፍ ያስችል ።
በህይወት ውስጥ ስኬታማ መሆን ለሰዎች በተወሰነ ደረጃ ነፃነትን ያጎናፅፋል ። ያ ሰው ለራሱ እሚፈልጋቸው ነገሮች ከተሟሉለት እና በሌሎች ሰዎች ለካይ ጥገኝነት ከሌለበት ለነፃነቱ አንድ ዋስትና ነው ። ነፃነት በህይወት ስኬት ብቻ የሚመጣ ነገር አይደለም ። ከዚያ ይልቅ የህሊናዊ-ንቃት እና የግብዛቤ መጨመር አንድን ሰው የበለጠ ነፃ ያደርገዋል ።
ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰው ራሱን ፈልጎ ሲያገኝና ራሱን መሆን ሲጀምር ነፃነት ይሰማዋል ። የሚፈልገውንና የሚያስደስተውን ስራ ሲሰራ… ወዘተ የሰውን ነፃነት የሚጨምር ነገር ነው ። ይሁን እንጂ አንድ ሰው የሚፈልገውን ስራ መስራት የሚችለው መጀመሪያ ራሱን ማወቅ ሲችል ነው ። ራሱን በትክክል የማያውቅ ሰው በሚገፈልገው ሙያ ስራ ላይ ሊሰማራ አይችልም ። አንድ ሰው በጣም በሚወደው ሙያ ላይ ሲሰማራና በዚያ ዘርፍ ስኬታማ መሆን ሲጀምር ራሱን ፈልጎ አገኘ ይባላል ። ለብዙ ሰዎች ህይወት ውስጥ በጣም ፈታኝ ነገር ራስን ፈልጎ ማግኘት የመጀመሪያው ሲሆን ሁለኛው ደግሞ በብዙ ጭንቅ ተፈልጎ የተገኘውን የራስን ማንነት የመከተል ድፍረት ነው ።
ብዙ ሰዎች የማያስደስታቸውን ፣ ነገር ግን በማህበረሰቡ ዘንድ እንደ ትልቅ ነገር የሚታይ ወይንም ክብርን ሊያስገኝላቸው የሚችልን ነገር ሲከተሉ ወይንም ሲሰሩ ይታያሉ ። ይሄ በአንድ በኩል ሰው ለመኖር ሲል ፣ ምንም እንኳን ያ ነገር ያን ያህል ባያስደስተውን ያን ነገር እያደረገ ወይም እየሰራ ሊኖር ግድ ሊሆንበት ይችላል ፤ ይሄ በአንድ በኩል በምንኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ተቃርኖን ላለመፍጠር ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ያ ነገር መተዳደሪያችን ከሆነ መከተል ግድ ሊሆንብን ይችላል ። ነገር ግን አንድ ሰው ውጫዊ ተቃርኖን ሳይፈጥር ውሰጣዊ ማንነቱን ማስከበር ይችላል ።

የህይወት ሚስጥር ?

ብዙ ሰዎች የህይወትን ሚስጥር ለማወቅ ይጥራሉ ። ህይወት የተገለጠች መፅሀፍ ነች «Life is an Open Secret » ። ህይወት «የተገለጠች» መፅሀፍ ብትሆንም ሊያነቧትና ሊደረዷት የሚችሉት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው ። በዚህች ምድር ከተፈጠሩ እጅግ ታላላቅ ሰዎች አንዱ የሆነው ቡድሀ ፣ የደረሰበትን እውቀት ለሰዎች እንዲያስተምር ተከታዮቹ ሲገፋፉት የሰጠው መልስ ባስተምርስ ማን ይረዳኛል የሚል ነበረ ። ተከታዮቹም መልሰው ጥቂት ሰዎችም ቢሆኑ የሚረዱህ ጥቂቶች አሉ ብለው ነበረ እንዲያስተምር ሊያሳምኑት የበቁት ።

ከቅዱሳን አስተምህሮዎች የምንረዳው ይሄን ነው ። ምንም እንኳን የህይወት ሚስጥራት ሁሉ በቅዱሳን መፅሀፍ ውስጥ ሰፍረው እሚገኙ ቢሆንም ፣ ቅዱሳን መፅሀፍን በትክክል መረዳት እሚችሉ ጥቂቶች ናቸው ። በዚህች ምድር ከተፈጠሩ ታላላቆች የደረሱበትን እውቀት አስተላልፈው አልፈዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁኔታ እነሱ ሲመጡ ከነበረው ፈቀቅ አላለም ። ይህ የሆነበት የራሱ ምክንያት አለው ።

ሰዎች የታላላቆቹን አስተምህሮ አለመረዳትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እውነትን ለመከተል ድፈረትንና የውስጥ ንፅህናንና ፍቅርን ይፈልጋል ። ሌሎች ሰዎችን መውድድን ፣ የራስን ጥቅምን ከማስቀደም ይልቅ ለሰዎች ደህንነት ማሰብንና መጨነቅን ይጠይቃል ። የውስጥ ንፅህና የሌለው ፣ ውስጡ ንፁህ ያልሆነ ፣ ክፋትን በውስጡ ያዘለ ከእውነት ጋር ትውውቅ የለውም ፣ ሊኖረውም አይችልም ።

የካባላህን ሚስጥር ካወቁ መሀል ፣ ላኦ ዙም እንደዛው ሲሆን፣ ቡድሀም እንደዛው ነው ። ጥቂቶች ይረዱሀል ብለው ነው ። የሊቁን ፎስት ታሪክ እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢነት አለው ። ሊቁ ፎስት እውቀትን ከሰይጣን ጋር የተለዋወጠ ሰው ነበረ ። የአለምን ሚስጥር ሁሉ እንዲገልጥነትና በልዋጩም ነፍሱን ሰይጣን እንዲወስዳት ነፍሱን ለሰይጣን ለመስጠት  ከሰይጣን ጋር የተዋዋለ ሰው ነበረ ።

ኦከልትንም ብንወሰድ እንደዛው ነው ። ለብዙሀኑ ቢታወቅ አደገኛ ነው ተብሎ ስለ ሚታሰብ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን አንድ ሰው ፓሪስ ወይንም ለንደን ሳይሄድ እዚሁ አዲስ አበባ ተቀምጦ ማወቅ ይችላል ። በድረ-ገፅ ላይ መመልከት ይችላል ። ለምሳሌ ፕሌቶ ለጥቂት ፈላስፋዎች ብቻ ይሰጥ የነበረውን እውቀት በመፅሀፍ መልክ በመፃፉ በዘመኑ በነበሩት ልሂቅ ፈላስፎች ተተችቶበታል ። በየትኛውም የታሪክ ዘመን ልሂቃኖች እውቀታቸውን ለብዙሀኑ ለማካፈል ፈቃደኛ ሆነው አያውቁም ። ለዚህም ምክንያቱ በርካታ ነው ፣ በአንድ በኩል ልሂቃኑ የተቀረው ህብረተሰብ ሊረዳው አይችልም ብሎ በማሰብ ወይም ፣ እውቀት የሀይል ፣ የስልጣንና የሀብት ምንጭ ስለሆነ ሚስጥርነቱን ለመጠበቅ በሚል ነው ።

ቻይናና ምእራባውያን

ምእራባውያን በቻይና ማንሰራራት የተደበላለቀ ስሜት ይሰማቸዋል ። በአንድ በኩል የቻይና ማደግ ለኢኮኖሚያቸው ሰፊ እድልንና ገበያን የፈጠረላቸው ሲሆን ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የቻይና ማቆጥቆጥና ማደግ በስጋት የሚመለከቱት ነው ። ይህም በአንድ በኩል ለምሳሌ ቻይና በእስያ ያላት የደሴት የገባኛል ባይነት እንዲሁም ፣ በአለም ዋነኛ ከሚባሉት የጦር መሳሪያ ነጋዴ ላኪ ሀገሮች ተርታ መሰለፏ እንዲሁም ይህም ስዊድን አገር የሚገኘው የሰላም ጥናት ተቋም በ እ.ኤ.አ 2013 ባደረገው ጥናቱ አረጋግጦታል ። እንዲሁም ቻይና በአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት እየቦጠቦጠች ነው በሚል በርካታ ትችቶች የሚቀርቡባት ሲሆን እንዲሁም ቻይና ለአፍሪካ የሰብአዊ መብት ረገጣ ደንታ የላትም በሚልም ትወቀሳለች ። በመጪዎቹ ጥቂት አስርት አመታት ውስጥ ቻይና ያለምንም ጥርጥር የአለም ግዙፉ ምጣኔ – ሀብት ባለቤት ስትሆን ይበልጥ ምእራባውያንን ስጋት ውስጥ ጨምሯል ።