አይሁዳውያን

የአለማችንን ዋና ዋና የሆኑትንና መሰረታቸው ከአብረሀም የሆኑትን ሀይማኖቶችን ለመረዳት መንፈሳዊ መሰረት የጣሉትን አይሁዳውያንን ታሪክና ማንነትን ማወቅ ሳይረዳ አይቀርም ። አይሁዳውያን በዚህ በኩል በርካታ ስቃይን ያዩ ህዝቦች ናቸው ። በዚህ ምክንያት አይሁዳውያን ከበርካታ አመታት ስቃይ ብዙ ትምህርትን ቀስመዋል ። በነገራችን ላይ አይሁዳውያን ይሄ ሁሉ ስቃይ የደረሰባቸው እየሱስ ክርስቶስን በመስቀላቸው ሊመስለው ይችላል ። ይሁን እንዲያም በፊት ቢሆን አይሁዳውያን ከአውሮፓውያን የበለጠ ስልጣኔ የነበራቸው ቢሆኑም መሬታቸው ጠባብና ህዝባቸውም ትንሽ ስለነበረ በቀላሉ በሮማውያን ፣ በኦቶማን ቱርኮችና በሌሎች ገዢዎች ቀንበር ስር በመቶዎች ለሚቆጠሩ አመታት ወድቀው ቆይተዋል ። ከጥንት ዘመን ጀምሮ የጥንቶቹን ኢትዮጲያውያንን ጨምሮ ፣ ከአይሁዳውያን ጋር ያልተዋጋ የአካባቢው አገር የለም ማለት ይቻላል ፣ ኢትዮጲያውያን ብዙ ሺ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠው እስራኤላውያንን ሊዋጉ እንደዘመቱ በመፅሀፍ ቅዱስ ጭምር ተጠቅሷል ። በዚህ ብቻ ሳያበቃ በባቢሎን የመጨረሻ በሚባል የኑሮ ደረጃ በስደተኝነት ከአገር አገር በመንከራተት ቆይተዋል። ከክስቶስ ልደት በኋላም ከአውሮፓውያን በመጣ የመስቀል ጦርነት ምክንያት ተወረዋል ። በአሁኑ ወቅት አይሁዳውያን በአሜሪካና በአውሮፓና በሌሎችም በርካታ ሀገራት  በከፍተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ።

ነገር ግን እስራኤላውያን በስነ – ምግባር የሚያምኑ ህዝቦች ሆን ነው ሳለ ፣ ነገር ግን በፍለልስጥኤማውያን ላይ የሚወስዷቸው ከረር ያሉ ምላሾች ከአለም ውግዘትን ሲያስነሳባቸው ይስተዋላል ።

ናዚዎች አይሁዳዊነትን ዘር ነው ብለው የሚያምኑ ሲሆን ይሁን እንጂ አይሀዳዊነት ዘር ሳይሆን ሀይማኖት ነው ። የሩስያ ፣ የአሜሪካ ፣ የጀርመን ፣ የአረብ ፣ የአበሻ የመሳሰለው አይሁዶች በአለም ዙሪያ ላይ ሲኖሩ ፣ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር አይሀዳዊ እምነታቸው ነው እንጂ ዘራቸው የተለያየ ነው ። ናዚዎች ግን አይሁድነትን እንደ ዘር በመውሰድ በዘር ጥላቻ በመነሳሳት በአይሁዳውያን ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ ጉዳትን አድርሰዋል ። አስገራሚው ነገር ራሳቸው ናዚዎች የርእዮተ – አለም ምንጭ አድርገው የሚወስዱት የፅዮናውያንን ፕሮቶኮል ነው ። ፅዮናውያን ዘረኞች ናቸው ከሚል ሀሳብ በመነሳትና የኛ ዘር ፅዮናውያንን ይበልጣል ፣ ስለሆነም አለምን መግዛት አለብን ከሚል በተዛባ መረጃ በመነሳት ነው ።

ብዙ ጊዜ አይሁዳውያን ገንዘብ ይወዳሉ ቢባልም ሀገር ስላልነበራቸውና ብዙ ሀገራት ውስጥ ስለተንከራተቱ ያላቸው ብቸኛው ህልውናቸውን ሊያስጠብቁ የሚችሉበት ነገር ገንዘብና እወቀታቸው ብቻ ስለነበረ በእነኚህ በሁለቱ ከሌሎች ህዝቦች በላቀ ተወዳዳሪ የሌለው ሀብትንና እውቀትን ማከማቸት ችለዋል ። አይሁዳውያን አገር ሳይኖራቸው ለሺ በሚቆጠሩ አመታት በመላው አለም በመንከራተት መኖር ችለዋል ፣ የነሱን ያክልም በአለም ላይ የተሰቃየ ህዝብ የለም ይባላል ። እንደውም በደረሱበት ሀገር ሁሉ ከሌላው ከአገሬው በበለጠ የሀብት ፣ የስልጣንና እውቀት ደረጃ መድረስ ችለዋል። ይህም ሊሆን የቻለው አንድ ሰው የሰብአዊ መብቱ መቅደም እንዳለበት ሀገር ባይኖረውም የሰብአዊ መብቱ መከበር እንዳለበት ፣ ሀገር ስለሌለው የሰብአዊ መብቱን አይገፈፍም በሚል ሀሳብ ላይ የተመሰረተው በሆነው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቻርተር ነው ።

አንድ ሰው ሀገር ከሌለው ፣ ምንም እሚተማመንበት ነገር በማይኖርበት ጊዜ ያለው ብቸኛው መተማመኛ ነገር ገንዘብ ነው ሊሆን የሚችለው ። ስለዚህ የአይሁዳውያን ገንዘብ ወዳድነትና በገንዘብ በኩል ያገኙት ስኬት ምንም አስገራሚ አይሆንም ። ነገር ግን ይሄ ብቻ ሳይሆን የአለማችን ስልጣኔ የተጀመረው በዚሁ በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ሲሆን የባቢሊሎን ፣ የእስራኤላውያን ፣ የሜሶፖታሚያ ስልጣኔዎች የተፈጠሩት በዚሁ በመካከለኛው ምስራቅ አካባቢ ሲሆን የአይሁዳውያን በምድር ስኬታማ መሆን አስገራሚ አይሆንም ። እሁዳውያን የላቀ ጥረትና ትጋትም ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውንም መዘንጋት የለበንም ።

የአይሁዳውያን መናኀሪያ የሆነችውን እየሩሳሌምን ብንወስድ በብዙ ሀያላን እጅ ገብታለች። አይሁዳውያን መሬታቸውም ጠባብ በመሆኑና ህዝባቸውም አነስተኛ በመሆኑ በርካታ ሀያላን ሀይላቸውን ሲያጠናክሩ እየሩሳሌም ላይ አይናቸውን ሲጥሉና ሲቀባበሏት ቆይተዋል ። የጥንት ባቢሎናውያን ፣ ሮማውያን ፣ ኦቶማን ቱርኮች ፣አረቦች በኋላም እንግሊዞች እነኚህ ሁሉ እየሩሳሌምን ለመቆጣጠርና ለመያዝ ይዘውም ሀይላቸው እስኪደክም ድረስ ተራ በተራ አስተዳድረዋታል ።

ናዚዎች አይሁዳዊነትን እንደ ሀይማኖት በመውሰድ በደል ሲፈፅሙባቸው ፣ ነገር ግን አይሁዳዊነት ሀይማኖት እንጂ ዘር አለመሆኑን አልተረዱም። በአለም ላይ ባሉ ብዙ ሀገራት የሰው ዘሮች አይሁዳውያን ይገኛሉ ።

አይሁዳውያን እየሱስ ክርስቶስ ሚስጥሩን በማውጣቱ ዝም እንደማይሉት ግልፅ ነው ። ዝም ብለው እንደማያልፉት ግልፅ ነው ። በነገራችን ላይ በመንፈሳዊነት አይሁዳውያን ከከፍተኛ መገለጥ ያላቸው ህዝቦች ናቸው ። በዙሪያቸው ያሉ ታላላቅ ስልጣኔዎች በሙሉ ሲወድሙ ፣ ነገር ግን አይሁዳውያን በግዞትና በስደት በባእድ አገር እየኖሩም ጭምር እንኳን መንፈሳዊ ሚስጥራቸውንና እውቀታቸውን ጠብቀው መኖር የቻሉ ህዝቦች ናቸው ። አይሁዶች በርካታ  መንፈሳዊ ጥበቦችን የቀሰሙት ከጥንት ግብፃውያን መሆኑ ግልፅ ነው ። በሙሴ ጊዜ እንኳን ሙሴ የግብፃውያንን  የቤተመንግስትና ጥበብ ተምሮ እንዳደገ ይገልፃል ። ነገር ግን አይሁዳውያን በዙራቸው የነበሩ የፋርስ ፣ የግብፅ ፣ የአሶርያውያን ፣ የባቢሎን የመሳሰሉት ስልጣኔዎች ሲወድቁና ሲፈራርሱ እንዲሁም ስልጣኔቸውና እውቀታቸው ሲወድም ተመልክተዋል ። ከእነኛ ውድቀቶች ሁለሉ ትምህርትን የወሰዱት አይሁዳውያን መሆናቸው ይታወቃል ። ይህም ማንም ብሉይ ኪዳንንና አዲስ ኪዳንን ያነበበ ሰው እንደሚረዳው ነቢያቶች ፣ ሀዋርያቶች የመሳሰሉት በሙሉ አይሁዳውያን ናቸው ። የበርካታ ስልጣኔዎችን ታሪክ በብሉይ ኪዳን ሲመዘግቡም ይሕንን የቀድሞ ስልጣኔዎችን ውድቀትንና መነሾዎችን በሚገባ እንደተንደተረገዲት ግልፅ ነው ።

ክርስቶስን የሰቀሉት ሮማውያን ናቸው የሚል ክርክር አንዳንድ አይሁዳውያን ያቀርባሉ ነገር ግን ፣ ሮማውያን ገዢዎች የነበሩ እንደመሆናቸው ፣ በሚገዙት ግዛት ላይ አለመረጋጋት እንዲፈጠር አይፈልጉም ፣ በአንፃሩ ግን ሮማውያን የአይሁዳውያንን ሀይማኖት ሊረዱ የሚችሉበት አቅምም ሆነ ባህላቸው ያልነበረ ሲሆን በዛን ወቅት ሮማውያንን ትተን ፣ ከእነሱ በፊት በአለም ገናና የነበሩትና በብዙ እውቀቶች የሰለጠኑት ሰልጥነዋል የሚባሉት ግሪኮች እንኳን በተለያዩ በርካታ አማልክትና ጣኦታትን የሚያመልኩ ስለነበሩ ፣ በአንፃሩ ግን አይሁዳውያን በሙሴ ህግጋት የሚመሩ እና በአጠቃላይ በአንድ አምላክና በህገ – ኦሪት የሚመሩ ነበሩ ። ጉዳዩን ሊረዱ የሚችሉትና ከእነሱ ሀይማኖት ጋር እንደ ተፃረረ እንደተፈታተነና ሊያውቁ የሚችሉት የአይሁድ የሀይማኖት መሪዎች ብቻ ናቸው ።

ይሁን እንጂ ከአለም ህዝቦች ሁሉ አለምን አንድ ቀን እንገዛለን የሚል አስተምህሮ ያላቸው አይሁዳውያን ብቻ ናቸው ፣ በአለም ላይ የትኛውም ህዝብ አንድ ቀን አለምን እገዛለሁ የሚል ንግርት ያለው የለም ። አይሁዳውያን ከጠቢቡ ሰለሞን ዘመን ጀምሮ አለምን በምን አይነት መንገድ እንደሚገዙ በርካታ ስልቶችን ሲቀይሱ ኖረዋል ተብለው የሚታሙ ሲሆን ፣ ለዚህም ምክንያት ሊሆን የሚችለው አይሁዳውያን ቀደምት ስልጣኔና ረቂቅ እውቀት ካላቸው ፤ ህዝቦች አንዱ መሆናቸው ይታወቃል ። የአይሁዳውያን ታላላቅ ሽማግሌዎች ፃፉት በተባለው ፕሮቶኮልስ የሚባለውም መፅሀፍ ይህን ስልቶችን በስፋት የሚዘረዝር ሲሆን፣ መዝሙረ ዳዊት ላይ አህዛብን ርስት አሰድጌ እሰጥሀለሁ ሲል ፣ እንዲሁም በሙሴ «ያልማስከውን ጉድጓድ ውሀ ትጠጣለህ ፣ ባልገነባኀው ከተማ ውስጥ ትኖራለህ ፣ ያልተከልከውን ወይን ትበላለህ» እንደሚል ይታወቃል ።

በመዝሙረ ዳዊት ላይም «አህዛብን ርስት አድርጌ ሰጥቼሀለሁ» የሚል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በዚያው መዝሙረ ዳዊት ላይ «ከብቶቸ ከበቡኝ» የሚል አለ ። እግዝአብሄር  «የአህዛብን የወይፈኖችንና የበሬዎችን ጉባኤም ይገስፅ» ዘንድ ይማፀናል ። ይህም የሚያመለክተው አይሁዳውያን በዙሪያቸው «አረማዊ» ወይም አህዛብ ብለው ለሚጠሯቸው ህዝቦች የነበራቸውን ዝቅተኛ አመለካከትና የነበራቸውን መንፈሳዊ እውቀት ልቀትን ያሳያል ። አይሁዳውያን አህዛብ እያሉ የሚጠሯቸው በተደጋጋሚ አይሁዶችን እየወረሩ ያሰቃያቸው ስለነበርና ፣ ቤተመቅደሳቸውን ያፈራርሱባቸውና ንዋየ ቀድሳቶቻቸውን ዘርፈው ይወስዱባቸው ስለነበረ ነው ። የባቢሎኑ ንጉስ የነበረው ሀያሉ ናባከደነፆር እየሩሳሌምን ወርሮ ፣ የሰለሞን ቤተ መቅደስ ከማፈራረሱም በተጨማሪ ንዋየ ቅዱሳኖቻቸውን ዘርፎ ወደ ባቢሎን ወስዶባቸዋል ። ብቸኛው ከአህዛብ ቅዱስ የሚሉት ታላቁ የፋርስ ንጉስ ቂሮስ አይሁዳውያንን ንዋየ ቅዱሳኖቻቸውን ወደ ሀገራቸው መልሰው እንዲወስዱና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በደብዳቤ ለሁሉም የአካባቢው ገዢዎች በፅሁፍ በማስታወቁ ፣ አይሁዳውያን ወደ ሀገራቸው እየሩሳሌም መመለስ ችለዋል ። ለዚህም ብቸኛው አህዛብ ቅዱስ ተብሎ ስሙ በብሉይ ኪዳን ሊሰፍር ችሏል ።

የሀገራችን ፈላስፋ ዘርአያቆብም ይህንን በተመለከተ «ለአህዛብ መቼም ቢሆን አይገልፅላቸውም» ማለቱ ለአይሁዶች ያደላ ነው ሲል ፣ ምእራባውያን ፈላስፎች በበከላቸው ዘርአያቆብን ፀረ-ሴማዊ ነው የሚል ትችት አሰንዝሮበታል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s