ስልጣኔ

 
በአለም ላይ የምንለው ስልጣኔ የመጣው ሰዎች አደጋን በመጋፈጥ የመጣ ነው ማለት ይቻላል ። ከዚህም ሌላ የሰው ልጅ ራሱን ከጠላቱ ለመከላከል ፣ ሌላውን በልጦ ለመታየት የተገኙ ግኝቶችና ሳይንሳዊ ግኝቶች የተሰደረሰባቸው እጅግ በርካታ ናቸው ። ለምሳሌ አውሮፕላንን ብንወስድ ሲጀመር በአየር መብረር አደገኛ ነበር በርካታ ሰዎች ስላልተሳካላቸው ህይወታቸውን አጥተዋል ። ስኬታማ የሆነው በሁለት አሜሪካውያን ወንድማማቾች ናቸው ።
ሌላው የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ያደረጋቸው ምርምሮች ለበርካታ ፈጠራዎች በርን ከፍቷል ከዚህም ሌላ የአሜሪካው የመከላከያ መስሪያ ቤት ለጦርነት ይጠቅማሉ ያላቸውን በርካታ ምርምሮች ከተወሰኑ አመታት በኋላ ለሲቪል አገልግሎት እንዲውሉ ይፋ አድርጓቸዋል ። ዳርፓ ተባለው የአሜሪካ የምርምር ተቋም ይጠቀሳል ። ዳርፓ ይጠቀሳል ።
ነገር ግን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ምንም እንኳን ሰዎች ስልጣኔን ቢፈጥሩም ፣ በመጨረሻ የአለም ስልጣኔዎች በራሳቸው በሰሪዎቹ ሰዎች እጅ እንደሚጠፉ በተደጋጋሚ በታሪክ የታየ ሀቅ ነው ። ለምሳሌ የጥንቶቹ አዝቴክሶች በሜክሲኮ የነበሩ የጥንንት ስልጣኔ ባለቤት የነበሩ ህዝቦች ምንም እንኳን ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ ስልጣኔ ባለቤቶች የነበሩ ቢሆንም ፣ ልጆቻቸውን መስዋትእት አድርገው ያቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ የጥንት ባቢሎኖችንም ብንወስድ እግዝአብሄርን እንይ ብለው ትልቅ ህንፃ ይሰሩ እንደነበሩና በዚህም እ ግዝአብሄር ተቆጥቶ ንግግራቸውን እንዳደበላለቀባቸውና እርስ በእርስ መግባባት እንዳልቻሉ መፅሀፍ ቅዱስ ይተርካል ።
ከዚህ በኋላ ግን የሰው ልጅ በዚህ ምድር ላይ ያለውን ኑሮ ካሳካ በኋላ ሌሎች ፕላኔታቸውኔቶችን ለያዝና ፣መኖር ይጀምራል ። አሁን አሁን ግን የተቀረው አለም ይህን በመረዳት ወደ ሳይንስ ፣ ቴክኖሎጂና ምድራዊ ህይወትን ወደ ማጣፈጥ በመዞሩ በቅርቡም ይሄ ልዩነት እየጠበበ መምጣቱ አይቀርም ።
Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s