እምነት ወይስ ህግ ?

በአይሁዳውያንና በክርስትያኖች መሀከል ሰፊ ክፍፍልን ከፈጠሩት ነገሮች መሀከል ፤ በእምነትና በህግ መሀከል ያለው ልዩነት ነው ። ክርስቶስ የእምነትን የበላይነት አጉልቶ ያስተማረ ሲሆን ፣ በአንፃሩ አይሁዳውያን ግን ህግ ይበልጣል ብለው ያምኑ ነበረ ። በዚህም ሰዱቃውያንና ፈሪሳውያን በተደጋጋሚ ከክርስቶስን ሊፈትኑት ሞክረዋል ። እየሩሳሌም በ70 አመተ አለም በሮማውያን ስር በምትወድቅበት ወቅት በታሪክ እንደሚታወቀው እነኚህ ሁለቱ ከታሪክ ገፆች ጠፍተዋል ። ከዚያ በኋላ ታሪክ አልታዩም  ለዚህም ምክንያቱ በቀል እንዳይደርስባቸው በመፍራት ራሳቸውን ከተቀረው የአይሁድ ህብረተሰብ ጋር መቀላቀላቸው ግልፅ ነው ።

      ይሁንና ብዙ ሰዎች ህግን ከሚያከብሩ ይልቅ ማመን ይቀላቸዋል ። ማመን ለሰዎች ቀላል ሲሆን ፣ ግን ህግን ማክበሩ ብቻ ሳይሆን ፣ መረዳቱ ራሱ ለብዙዎች ፈታኝ ነው ። አይሁዳውያን የሙሴን ህግጋትን በማክበራቸው እጅግ ይኮሩና ራሳቸውን ከሌሎች በዙሪያቸው ከነበሩት «አህዛብ» ወይንም «አረማዊ» ብለው ከሚጠሯቸው ህዝቦች የላቁ አድርገው ይመለከቱ ነበረ ። እየሱስ ክርስቶች እግዝአብሄር ህግን በማክበር ብቻ ሳይሆን ፣ በማመንም ጭምር እንደሚገኝ ማስተማሩ ብዙሀኑን እግዝአብሄርን የማያውቁት ህዝቦች ወደ እግዝአብሄር አምልኮት እንዲመጡ አስችሏል ። ይሁን እንጂ አይሁዶች የእምነታቸው ሚስጥር እንዲገለጥ አይፈልጉም ነበረ ። ይህም በሀዲስ ኪዳን ላይ በሀዋርያት ስራ ላይ «ህግ ነው ወይስ ፣ እምነት ነው እሚበልጠው?» ብሎ ሰፍሮ ይገኛል ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s