የፈጣሪ ህልውና

     የፈጣሪ ህልውናን ለማስረገጥም ሆነ ውድቅ ለማድረግ የሚደረጉ ክርክሮች በሁለት አቅጣጫ  ሊቀርቡ ይችላሉ ። አንዱ አፈጣጠር «ከክርኤሽን» አንፃር ሊታይ ይችላል ። በዚህም ሳይንስ በርካታ ማስረጃዎች ያሉት ሲሆን አንደኛው ምክንያት አለም እንዴት ተፈጠረች የሚለው ሀይማኖቶች ተፈጠረ የሚሉትና ሳይንስ በዚህ መንገድ ነው የተፈጠረው የሚለው  የተለያየ ነው ። አለም በአዝጋሚ ለውጥ ተፈጠረች ለዚህም በቃች በሚሊየን አመታት ዝግመታዊ ለውጥ ነው የሚለው በሳይንስ ሰዎች የሚራመደውና እየገነነና በርካታ ተከታዮችን እያገኘ የመጣው አስተሳሰብ ነው ። ለምሳሌ የዳይነሰሮችን እንኳን ብንወስድ እነሱ በዚህ ምድር ላይ የሰው ልጅን የመሳሰሉ አጥቢዎች ከመፈጠራቸው በፊት ከ60ና 70 ሚሊየን አመታት በፊት ኦ እንደኖሩ በሳይንስ ተረጋግጧል ። በዚህም አንፃራዊ በሆነ መልኩ በርካታ ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ከባዮሎጂ ፣ በካርቦን የዘመን ቅመራ መንገድ (Carbon Dating) ፣ በዝግመተ – ለውጥ ማስረጃ  በሚሆኑ በርካታ ቅሪተ – አካላት ማስረጃዎች ተገኝተዋል ። ከዚህ አንፃርም ባሀኡላ «አለም እንደዚህ አንድ ቀን ተፈጠረች የሚለው ላይሆን ይችላል» ይላል ።

     ዝግመተ – ለውጥ ፣ ባዮሎጂ ፣ ፊዚክስ ፣ ስነ – አለምን ፣ ስነ – ክዋክብትን የመሳሰለው ሁሉ አለም በተፈጥሮ የተፈጠረች ነች የሚያስብል ሲሆን ፣ በአንፃሩ ደግሞ (intelligent design) ከዚህ ጋር ተቀራራቢነት አለው ።  ሌላው ደግሞ በታላቁ እንግሊዛዊ የፊዚክስ ሊቅ ስቴፋን ሀውኪንግስ የተቀመረው የታላቁ ንድፍ (Grand Design) ነው ይህንንም ሀሳቡን ለማስረዳት ሀውኪንግስ አንድ መፅሀፍ በዚህ ርእሰ – ጉዳይ ላይ ፅፏል ።

            የጥንታዊው ሰው አፅሙና ቅሪተ አካሉ ብቻ ሳይሆን ፣ ከመቶ ሺዎች አመታት በፊት የረገጠው የእግር ዱካው በደቡብ አፍሪካ በአንድ ዋሻ ውስጥ በሳይንቲስቶች አማካይነት ሊገኝ በቅቷል ። ይሁን እንጂ ሳይንቲስቶችም ቢሆኑ መንፈሳዊ ነገርን በተመለከተ እንዲሁም መንፈሳዊ ህሊናዊ – ንቃትን (Spiritual Consciousness) በተመለከተ ከተቀረው ማህበረሰብ የበለጠ ግንዛቤው የላቸውም ማለት ይቻላል  ። ነገር ግን የአብዛኞቹ ሳይንቲስቶች እውቀትን ግንዛቤ አእምሯዊ ንቃተ – ህሊና (Mind Consciousness) ነው ። ስለዚህምንም እንኳን በርካታ ሳይንሳዊ መረጃዎችን ቢያገኙምና ወደፊትም በርካታ ማስረጃዎችንና መረጃዎችን ሊያገኙ ቢችሉም ወደ መንፈሳዊ ግንዛቤ ግን እየራቁ ነው የሚሄዱት ። ስለሆነም የሳይንስ ግኝቶች የሰውን ልጅ የመንፈስ ረሀብን ሊመልሱ አይችሉም ። እንደውም ሳይንቲስቶች የበለጠ መረጃዎችን ባገኙ ቁጥር ከመንፈሳዊነትም ሆነ ከሀይማኖቶች እየራቁ ነው የሚሄዱት ።

     ከስበት ህግ አንፃር ሲታይ ደግሞ በስበት ህግ መሰረት አንድ ሰው መልካም ነገሮችን ወደ ራሱ ከሳበ መልካም ነገር ብቻ ወደሱ ይመጣለታል ፣ መጥፎና የማይጠቅሙ ነገሮችን ወደራሱ ከሳበ ችግርና መከራ ብቻ ወደ ራሱ ይመጣል የሚል ነው ። በዚህ አመክንዮ ስንሄድ መልካም ነገርን ማድረግ እንደ እግዝአብሄር ወይንም እንደ ትክክለኛው መንገድ ሊቆጠር ይችላል ። በአንፃሩ ትክክለኛውን መንገድ አለመከተል እንደ ሰይጣን መንገድ ሊቆጠር ይችላል ።

                በሌላ በኩል ደግሞ ከህሊናዊ ንቃትና ግንዛቤ (consciousness) አንፃር ሲታይ ሀይማኖት ጠንካራ ክርክሮችን ማቅረብ ይችላል ። መንፈሳዊ መገለጥን እንዲሁም አለም አቀፋዊ ህሊናዊ – ንቃትን ብንወስድ ግን አንድ አፅናፈ – አለማዊ የሆነ ልእለ – አእምሮ እንዳለ ይገመታል ። ይህ ሀይል ለአንድ ሰው ብሎ የሚሰራ አይደለም ፣ ነገር ግን እከሌ ከእከሌ ብሎ የሚለይም አይደለም ። እውነት አንድ ነች ብለን ከተነሳን የጥንት አይሁዳውያን በሙሴ ግዜ ጀምሮ «ምድርና ሰማዩ ናስ ይሆንብሀል» ፣ «በዙሪያህ ላሉ ለአህዛብ ድንጋጤ ትሆንባቸዋለህ» የመሳሰሉት አገላለጦች የአይሁድ ህዝቦች ከትክክለኛው መስመር ሲያፈነግጡ ይደርስባቸው የነበረውን ስቃይ ለማስታወስና ከዚያም እንዳያፈነግጡ የሚመክሩ አባባሎች ናቸው ። እንዲሁም በመዝሙረ ዳዊት ላይ በርካታ የዚህ አባባሎች አሉ ። ለምሳሌ ከመስመሯ የሚያፈነግጡ «ነደው ይጠፋሉ »

እውነትን ምንነት ብንናነሳ እውነት አንድ ልትሆን ነው እምትችለው ። በዚህ በርካታ የአለማችን ፈላስፎች የሚስማሙ ሲሆን ያገራችንን ፈላስፋ ዘርአያቆብን ጨምሮ ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች ማንኛውም ነገር አንፃራዊ ነው የሚል አባባልን ይጠቀማሉ ። ነገር ግን እውነት አንድ ከመሆኗ አንፃራዊ ልትሆን አትችልም ።ለምሳሌ አንድ ሰው አንድ ወንጀልን ቢሰራ ያን ወንጀልም ሰርቷል ፣ ወይንም አልሰራም ነው ሊሆን የሚችለው እንጂ በአንፃራዊነት ያንን ወንጀል ሰርቷል ፣ ወይም በአንፃራዊነት ያንን ወንጀል አልሰራም ሊባል አይችልም – ወይ አድርጓል ወይም አላደረገም ። ስለዚህ እውነት አንድ ነች ማለት ነው ። እውነት አንድ ብቻም ሳይሆን ዘላለማዊም ጭምር ነች ።

ይህችን የእውነት መስመር የጥንት አይሁዳውያን ፈጣሪ ወይንም እግዝአብሄር ብለው ጠርተውታል ። በነገራችን ላይ ጥንታዊ ሰልጣኔዎች ይህንን መስመር አግኝተውት ነበረ ። ለምሳሌ ቻይናውያን ታኦ ብለው ሲጠሩት ፣ የጥንት ግብፃውያንም እንዲሁ በጥንታዊ ፅሁፎቻቸው ላይ ቀርፀውታል ። ለብዙ መቶ አመታት በጥንታዊ ግብፆች የተፃፈውና ፣ ሲደበቅ በነበረው ኤመራልድ የተሰኘው ጥንታዊ ድንጋይ ላይ የተቀረፀ ፅሁፍ ይህንኑ እውነት የሚያስገነዝብ ነው ።  ግብፃውያን እጅግ ጥንታዊ በሆነ መፅሀፋቸው (The Book of the Dead) ላይም እንዲሁ በርካታ የአለም ሚስጥሮችን ስለ – ነፍስ ሚስጥርን ጭምር አትተዋል ።

     በነገራችን ላይ አንስታይን የአንፃራዊነትን ንድፈ – ሀሳብን ባገኘበት ወቅት የሀይማኖት ሰዎች የሀይማኖትን መሰረት ይንዳል በሚል አንፃራዊነትን ንድፈ – ሀሳብን መቃወማቸው ይታወቃል ።አንድ ማመሳከሪያ ነጥብን ያስቀራል በሚል ። ኮሚኒስቶችም በበኩላቸው እንዲሁ ደስተኞች አልነበሩም እነሱም የራሳቸውን ምክንያት አቅርበዋል ።

     የታላላቅ ሀይማኖቶችን ብንወስድ ለምሳሌ ቡድሀ «እግዝአብሄር አለም የለምም ብሎ»  አስተምሯል ። ሂንዱዎች ምንም እንኳን በርካታ አማልክቶች ቢኖሯቸውም በአንድ አምላክ ወይም ፈጣሪ ያምናሉ ። የታላላቅ እምነቶችን ቅዱሳን መፅሀፍትን ብንወስድ የተዘጋጁት በአንድ በኩል ከፍተኛ ግንዛቤ ላላቸው በሚገባ መልኩ ፣ ከዛ ቀጥሎ መሀከለኛ የመረዳት ችሎታ ላላቸው ፣ ከዚያም ቀጥሎ አነስ ያለ የመረዳት ችሎታ ላላቸው ተመጥኖ የተዘጋጁ ናቸው ። በዚህም አንድ ሰው ቅዱሳን መፅሀፍትን የሚያነብ ሰው የእነኚህን ልዩነቶችን በዚያው በመፅሀፉ ውስጥ ማስተዋል ይችላል ። ለምሳሌ ባሀኡላ ስለምድር አፈጣጠር በመፅሀፍ ቅዱስ ስለተሰጡት መረጃዎች እርስ በእርሳቸው ሊቃረኑ እንደሚችሉ ገልጿል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s