ስራ አጥነት (Unemployment)

በአሁኑ ወቅት የወጣቶች ጉዳይ በአለም ፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ ለምን አንገብጋቢ ሆነ ሲባል  የእድሎች እየጠበቡ መምጣት ፣ የወጣቱ ቁጥር መብዛት በተለይም በርካታ የተማሩ ወጣቶች መኖር ነገር ግን የሚፈልጓቸው ነገሮች አለመሟላት ፣ ስራ ለመያዝ፣ የመኖሪያ ቤት ችግር ወዘተ … ናቸው ። ቀድሞ በኛም ሀገር በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን አንድ ወጣት ከውጪ ሀገር ተመርቆ ሲመጣ የሹመት ወንበር ፣  መኪናና ሌሎችም ነገሮች ይሟሉለት የነበረ ሲሆን በጊዜ ሂደትም እሚደረገው ጥቅማ ጥቅም እየቀነሰ እየቀነሰ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ግን እንኳንስ በኮሌጅ ደረጃ ያልተማረውን ትተን አንድ ከኮሌጅ ወይም ከዩንቨርስቲ ተመርቆ የሚወጣ ወጣት እንኳን ስራ ለመያዝ ብዙ ውጣ ውረድን ይጠይቀዋል ።

የአንድ ትውልድን ጉልበትንና ጊዜን በማባከን (Lost Generation) በርካታ አይነት ስራ አጥነት ሲኖር ለምሳሌ መዋቅራዊ ስራ አጥነት ፣ ወቅትን ጠብቆ የሚከሰት «ሳይክሊካል» ፣ የመሳሰሉት ናቸው ። በተለይም ደግሞ የተማረ ሀይል ስራ አጥነት የአእምሮ ብክነትን ይፈጥራል ። የአካል ጉልበትን አለመጠቀምን ብቻ ሳይሆን የአእምሮ ችሎታንም ጭምር እና ጊዜንም ጭምር ያባክናል ።

 

በዚህ ዘመን ስኬታማ ለመሆን አንድ ወጣት በጣም ተወዳዳሪ እና ብቁ መሆን መቻል አለበት ። የመማር እድል ያላገኘ ወጣት ግን ሊጠብቀው የሚችለው እድል ይበልጥ አስቸጋሪና ፈታኝ መሆኑ እርግጥ ነው ። የወጣት ስራ አጥነት የተማረም ይሁን ያልተማረ ስራ ማጣት ችግር የታዳጊ ሀገራት ችግር ብቻ መሆኑ እያበቃ ይመስላል ። ባደጉትም ሀገራት ያሉ ወጣቶች ስራ ለመያዝ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየገቡ ሲሆን ሀብታሙን የምእራቡን አለም ይሄ ችግር እየዳሰሰው ይመስላል ። ከዚህ ቀደም በርካታ ሰዎች ከአለም ዙሪያ ስራ ለመያዝ ወደ ሀብታሟ አሜሪካን ይጎርፉ የነበረ ቢሆንም ፣ ራሷም ብትሆን ሰራተኛ የሰው ሀይል አንሷት ከውጪ ሀገራት የዳይቨርሲቲ ቪዛ (DV) ሎተሪ ስርአትን የአሜሪካ ኮንግሬስ  እስከ መዘርጋት ቢደርስም እ.ኤ.አ. ከ2008 የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ግን ያንን የስራ እድል ማቅረብ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል ። የአለም የስራ ድርጅት (ILO) የዚህን አደጋውን ተረድቶታል ባወጣቸው ሪፖርቶችም ይህንኑ እውነታ ዘግቦታል ።

 

በእንግሊዝ አገር የታየው በከተሞች አካባቢ ያታየው የወጣቶች ረብሻ ፣ በአሜሪካም ዎል ስትሪትን መቆጣጠር የሚለው ሰልፍ ፣ ስርአቱ ለወጣቶችና ለድሆችና ለመካከለኛው መደብ ይሰጥ የነበረውን ጥቅሞችን ማስጠበቅ ባለመቻሉ የተፈጠረ የተቃውሞ ስሜት የፈጠረው ነው ። በነገራችን ላይ የምእራቡ አለም ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ከዚህ በፊትም በታሪክ ያስተናገደ ሲሆን ፤ ለምሳሌም በ1960ዎቹ በቬትናም ጦርነት ምክንያት በየአሜሪካ እና የምእራቡ አለም ወጣቶች ተተቃውሞ ወጥተው ነበረ ። ነገር ግን ያ ተቃውሞ በአብዛኛው አሜሪካ የገባችበትን የቬትናምን ጦርነት በመቃወም ሲሆን ፣ በ2012 ዓ.ም. በአውሮፓና በአሜሪካ የታየው ግን ጦርነቶችን መቃወም ብቻ ሳይሆን ስር የሰደዱትን የማህበራዊና የምጣኔ – ሀብታዊ ችግሮች ያባባሱት ሲሆን ከቀድሞዎቹ የበለጠ ውስብስብና መፍትሄውም ቀላል እንደማይሆን መገመት ይቻላል ። የኮርፖሬሽኖች ለትርፍ መስገብገብ ፣ የሀብት ክፍፍል መዛባትና የመሳሰሉት መሰረታዊ የሆኑ ምጣኔ – ሀብታዊ ችግሮች ለብዙ ዘመናት ሲብላሉ መጥተው እዚህ ደረጃ መድረሳቸው የፈጠረው ነው ማለት ይቻላል ።

 

የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር በማርጋሪት ታቸር ዘመን አ.ኤ.አ በ1981 እንዲሁ ተመሳሳይ ሰልፎችና ረብሻዎች በእንግሊዝ ሀገር ተከስተዋል ፣ በተለይ እንደ ሊቨርፑል ባሉ ከተሞች ስራ አጥነት ተስፋፍቶና ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ በነበረበት ወቅት ፣ አናሳ ይባሉ በነበሩ ማህበረሶች ዘንድ የአሁኑን አይነት ተመሳሳይ ክስተት ተከስቶ ነበረ ። ታቸርም ጠንካራ የፖሊስ ሀይልንና እና ሀይልን ለመጠቀም እስከማሰብ ደርሰው የነበረበት ጊዜም ነበረ ። እ.ኤ.አ. በ2012 እንዲሁ ሀብታም በምትባለዋ በሀገረ እንግሊዝ የወጣቶች ረብሻ ሲከሰት የተከሰተው በወጣቶች ስነ- ስርአት መጓደል ነው ቢባልም ዋናው ችግር ግን የወጣቶች ስራ አጥነት፣ የእድሎች መጥበብ ነው ማለት ይቻላል ።

 

ሁሉንም ነገር ገበያው ያስተካክለዋል ብሎ ለገበያው ትቶ መቀመጥ የዋህነትንና ባስ ሲልም አለማወቅን ያመለክታል ። ይህም ፖሊሲ ለአስርት አመታት ቀጥሎ የቆየ በመሆኑ በቀላሉ ነገሩን ወደ ነበረበት መመለስ ፈታኝ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም ። ሁሉም ሰው እኩል የመወዳደር አቅም አይኖረውም ፣ ስለዚህ ውድድሩ ወደኋላ ትቷቸው የሚያልፋቸውን የሚያቅፍና እንዳይጎዱ የሚያደርግ ስርአት መዘርጋት እንዳለበት መገመት ይቻላል  ። ካርል ማርክስ የካፒታሊዝም ስርአት ችግር ናቸው ብሎ ከሚገልፃቸው ጉዳዮች አንዱ ይሄው የስራ አጥነት ችግር አንዱና ዋናው ነው ።

 

ይህ ችግር ሀብታም በሆኑት የእስያ ሀገራትን እንደ ደቡብ ኮርያ ያሉትም ጭምር ቀድሞ ጥሩ የሆነና የጥራት ያለው ትምህርት እንደ ስራ ለማግኘት አስተማማኝ እንደሆነ ይታሰብ የነበረ ቢሆንም ፣ በእነሱም ሀገር ሳይቀር ትምህርት አስተማማኝ የስራ እድልን እንደማያስገኝ መታየት ጀምሯል ስለዚህ ወጣቱ ሌላ አማራጭን መፈለግ እንደሚኖርበት መገመት ይቻላል ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s