የስርአተ- መንግስት መሰረት

 

ጥንትም ሆነ አሁን አንድ ስልጣኔ ህልውናውን አስጠብቆ የሚኖረው ያንን የሚደግፈው ምጣኔ – ሀብት እስካለው ድረስ ብቻ ሲሆን ከራሳችን ሀገር እንኳን ብንጀምር የአክሱም ስልጣኔ ያንን የሚያክል ገናናነትን ሊቀዳጅ የቻለው በነበረው የኢኮኖሚ አቅም ሲሆን የራሱን የወርቅና የነሀስ ገንዘቦችን በማሳተም በእነዛ ይገበያይ የነበረ ሲሆን የአክሱም የገንዘብ ሳንቲሞች በዘመኑ እንደአክሱም ሀያላን በነበሩት በግሪክ ፣ በሮማ ፣ በፐርሺያ ከተሞች ሲገኝ በአክሱምም የእነዚህ ጥንታዊ ሀገራት ሳንቲሞች ተገኝተዋል ። ይሁን እንጂ አክሱም ያንን ስልጣኔውን ማጣት የጀመረው ያንን የሀብት ምንጩ የሆነውን የንግድ መስመሩን ለማስጠበቅ የሚያስችለውን ሀይል እያጣ ሲመጣ፣ ከውስጥና ከውጪ የመጣበትን ጫና መቋቋም ሲያቅተው ስልጣኔው ተዳክሞ ሊከስም ችሏል ።

አሁንም ከዘመናችን የአሜሪካንን ሀያልነት ብንወስድ አንዱና ዋናው የሀያልነቷ ምስጢር የኢኮኖሚ አቅሟ ሲሆን ያንን የኢኮኖሚ ሀይል እያጣች በሄደች ቁጥር ወይም አንፃራዊ በሆነ ሁኔታ አቅሟ እየደበዘዘ ሲሄድ ግን ሌላው ሁሉ የበላይነቷና ሀያልነቷ እየደበዘዘ ይሄዳል ። ጠንካራ ምጣኔ ሀብት ያለው ሀገር ለሀያልነቱ ድጋፍ የሚያደርጉለትን እንደ ጠንካራ ወታደራዊ አቅምን በቀላሉ መገንባት ሲችል ፣ በሳይንስ ምርምር ፣ በቴክኖሎጂና ለአዳዲስ ምርምሮችየሚያስፈልገውን ገንዘብ መመደብ ይችላል ። በስነ – የጥበብም እንዲሁ አርቲስቶች ሊደግፋቸው የሚችል ህብረተሰብ ስለሚኖር እያደገ ይሄዳል ።

በአጭሩ ሲጠቃለል የምጣኔ – ሀብት መሟላት ማለት መሰረታዊ የሆኑ የሰው የልጅ ፍላጎቶች ማለትም መብላት ፣ መጠጣት ፣ መጠለያ ማግኘት መሟላት ማለት ሲሆን እኒኚህ የተሟሉለት ሰውም ወደ ሌላው ከዛ ወደ በለጠ ነገር መሸጋገር ይችላል ። የኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች መሟላት ለሰው ልጅ ከደረሰበት ስልጣኔ አንፃር ጅማሬው ነው እንጂ ፍፃሜው አይደለም ። ሌሎች እንሰሳትን ብንወስድ ተስማሚ የመኖሪያ ቦታ ካገኙ ፣ ከበሉ ፣ ከጠጡ ፣ ከተራቡ (ከተዋለዱ) ከዛ በላይ የሚፈልጉት ነገር የለም ። ለሰው ልጅ ግን እነኚህ ነገሮች መሰረታዊ የሆነውን ነገር ማሟላት ሲሆን እነኚህን ካሟላ በኋላ ደግሞ ሊያሟላቸው ወደ የሚፍለጋቸው ከዛ ከፍ ወዳሉ ደረጃዎች ይሄዳል ።

በጣም አስገራሚ ነገር በአሁኑ ወቅት ባደጉት ሀገራት ተደጋጋሚ የምጣኔ – ሀብት ቀውሶች ቢከሰቱም በስፖርት ፣ በፊልምና በሙዚቃ ዘርፎች ግን አልተነኩም ። እንደውም በሚያስገርም ሁኔታ እድገታቸው ቀጥል ። ለምሳሌ በሀገራችን ተወዳጅ የሆኑት የአውሮፓ የእግር ኳስ ውድድሮች ለተጫዋቾች የሚከፈለው ደሞዝ ሲጨምር ፣የስፖርት ትጥቅ አምራቾችም ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳላቸው ሲሆን በአጠቃላይ ዘርፉ እያደገ በመሄድ ላይ ነው ። ለዚህም ምክንያቱ የአውሮፓም ሆነ የአሜሪካን ህዝብን መሰረታዊ ፍላጎቱን ያሟላ በመሆኑ ተደጋጋሚ የምጣኔ ሀብት መዋዠቆች ቢያጋጥሙም የመዝናኛ ዘርፎች ግን ፈላጊ እንዳላቸው ነው ።

ሰው መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ካሟላ በኋላ የበለጠና ከፍ ያለ ነፃነትን መመኘትና መፈለግ ፣ ታላላቅ ስነ – ጥበቦችን ማድነቅ ፣ በመንፈሳዊ ተግባራት መሳተፍ የመሳሰሉት ከሰው እድገትና ፍላጎት መሟላት ጋር አብረው እያደጉ የሚሄዱ ናቸው ።

በተለይም በአሁኑ የአለም አቀፍ ትስስር እየተጠናከረ ባለበት በዚህ ዘመን አለም በኢኮኖሚም በፖለቲካም እየተሳሰረች ባለችበት ጊዜ በአንዱ የአለም ክፍል የሚፈፀም በሌላውም አለም በቅፅበት ይሰማል ፣የራሱን በጎም ሆነ አሉታዊ ተፅእኖም ይኖረዋል ።የአሁኑን ዘመን ለየት የሚያደርገው አንዱ ነገር ደግሞ በአንዱ የአለም ክፍል የሚፈጠሩ ችግሮች ወደ ሌላውም የአለም ክፍል በፍጥነት የሚዛመቱበት ሁኔታ ነው ።

ሌላው ደግሞ የአሁኑ ዘመን ምናልባትም በሰው ልጅ ታሪክ በጣም ነፃ የሚባል ዘመን ነው – ካለፉት ዘመናት ጋር ሲነፃፀር ። የሰው ልጅ በታሪኩ የዚህን ያህል ነፃነትን አግኝቶ አያውቅም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ከዚህ ቀደም ሰው እንደ እቃበባርነት የተሸጠበትና ጉልበቱ የተበዘበዘበት ዘመን የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላም በቅኝ አገዛዝተረግጦ የተገዛበት ፣ሀብቱ በቅኝ ገዢዎች ሀብቱና ጉልበቱ የተዘረፈበትና የተጋዘበት፣ከቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣ በኋላም ከራሱ ጉያ በወጡ ፈላጭ ቆራጭ አምባገነኖች ለበርካታ አመታት ሲገዛ ኖሯል ።

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በአለም ላይ ያለው ትልቁ ትግል ከውጪ ወራሪዎች ጋር የሚደረግ ትግል ሳይሆን ፣ የውስጥ ጨቋኝ መንግስታትን ማስወገድ በርካታ ሀገራት የሚታይ ሲሆን በተለይም ከአረቡ አለም አመፅ በኋላ ይሄ ነገር በአለም ዙሪያ በስፋት የሚታይ ጉዳይ ነው ። ይሄም አንድ ዘመን አይሽሬ የሆነ እውነታን ያስታውሰናል ፣ ይኀውም አንድ መንግስት ከህዝብ አቅም በላይ ሊሆን እንደማይችል ሲሆን ፣ ህዝቡ ያ መንግስት ካለ የመኖር ዋስትና አይኖረኝም ብሎ ካሰበና ፣ ምንም ለውጥ አይመጣም ብሎ ተስፋን ከቆረጠ ፣መመለሻ ወደ ሌለው አመፅ ተሸጋግሮ የዛን መንግስት ህልውና ማብቂያ ይሆናል ።  በአረቡ አለም የታየው ይኀው ነው ።

ባደጉት ሀገራትም የሚገኙ ህዝቦችም ስለ መንግስታቶቻቸውና ፖለቲከኞቻቸው ባህሪ በሚገባ በመረዳት የተሻለ ምርጫን ማካሄድ የቻሉበትና መንግስቶቻቸው ላይ የተሻለ ጫናን ማሳደር የቻሉበት ዘመን ነው።የሰው ልጅ በአሁኑ ወቅት የማያውቀውምን ነገር ከመፍራት ነፃ እየወጣ የሚገኝበት ፣ በየሀገሩ ያሉ መንግስታትና አስተዳደሮች እየተሻሻሉ የሚገኙበትና በበርካታ የአለማችን ክፍል የሚገኙ ህዝቦች በነፃነት የራሳቸውን የወደፊት እጣ ፋንታ በእጃቸው እያስገቡ የሚገኙበት ወቅት ነው።እንዲሁም በብዙ ሀገራት ቁጥሩ በርካታ የሆነ የትምህርትን እድል ያገኘ ወጣት ትውልድ እየተፈጠረ ስለሆነ ሌላው ቀርቶ ዲሞክራሲ ሊታሰብባቸው አይችልም ሲባልባቸው የነበሩ የአረብ ሀገራት ሳይቀሩ ዲሞክራሲያዊ መንገድን መከተል ግዴታ እየሆነባቸው ነው ። ያለበለዚያ ግን ወደ አደገኛ የእርስ በእርስ ጦርነትና መበጣበጥ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ የታየ ሁኔታ ነው ።

ፖለቲካ ማለት የማህበረሰብ ወይም የህዝብ አገልግሎት በማለት የጥንታዊት ግሪክ ታላቁ ፈላስፋ አሪስቶትል ይገልፀዋል ። ይሁን እንጂ ይህ በተግባር በብዙ ሀገራት ሚታየው ፣ የአሪስቶትል የተቀደሰ ሀሳብ ወይም ይደረስባቸዋል ተብለው የሚታሰቡ ቅዱሳን ሀሳቦች (Ideals) ጋር ራቅ የማለት ባህሪ አለው ። ዲሞክራሲ ለይስሙላ አለባቸው በሚባሉ ፣ወይም ዲሞክራሲ ጨርሶ የሌለባቸውን ትተን፣ የዳበረ የዲሞክራሲ ስርአት አላቸው በሚባሉት የምእራብ ሀገራት ሳይቀሩ ሀገራት ሳይቀር አልፎ አልፎ የሚታይ ነው ። ህዝብን ማገልገያ መሳሪያ ከመሆን ይልቅ የስልጣንንና የዝና የጋለ ፍላጎት ያላቸው ሊጠቀሙበት ይችላሉ ።ይሁን እንጂ አሪስቶትል ካለው በተቃራኒ ፣ የፖለቲካ መሪዎች ለስልጣን ብለው ስነ – ምግባርን (Ethics) ወደ ጎን ሊገፉ እንደሚችሉ ካለፉ በርካታ የታሪክ ልምዶች መገንዘብ ይቻላል ።

አንድ መንግስት እሚንቀሳቀስበትን ገንዘብ ከህዝብ በሚያገኘው ግብርና በሚሰብስበው የሚንቀሳቀስ ሲሆን ፣በተጨማሪም አቅሙ ደከም የሚል ከሆነም የውጭ እርዳታንና ብድርን በህዝቡ ስም ሆኖ ይቀበላል ። ስለዚህ ተጠያቂነቱ ለህዝቡ መሆን ሲኖርበት ነገር ግን ከህዝቡ ፍላጎት ውጪ ልሁን ካለ ከሚመራው ህዝብ ጋር ቅራኔ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ ነው ። በ17 እና 18ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩት አውሮፓውያን ፈላስፎች ይህንን ሀቅ በመረዳት በዘመኑ በፃፏቸው በርካታ ፅሁፎቻቸው ይህንን ሀሳብ ሲያንፀባርቁ ፣ በርካታ የአውሮፓ መንግስታትም በዚህ መስመር መቃኘት የጀመሩት ፤ ይህም የህዝብን የበላይነት የተቀበሉ መንግስታት ለመፈጠር የፍልስፍና መሰረት ሆኖ አገልግሏል ። በዛን ወቅት የተመሰረተችው አሜሪካም የፈላስፎቹን የእነ ጆን ሎኬን ሀሳብ በመውሰድ ዘላቂ የሆነ ስርአትን ለመመስረት ችላለች ።

በአሁኑ ዘመን በአለማችን በበርካታ የአለማችን ክፍል የተዛባ የሀብት ክፍፍል ስለመኖሩ በርካታ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ ። ስለአለማችን ቱጃሮች የሚዘግበው የፎርብስ መፅሄት እንደገለፀው ከ25 አመት በፊት በአለማችን ላይ ያሉ ቢሊየነሮች ቁጥር 140 ብቻ የነበረ ሲሆን በ2012 ዓ.ም. ግን የቢሊየነሮቹ ቁጥር ወደ 1226 ደርሷል ። ይህም የሚያሳየው የአለማችን ሀብት በጥቂት ሰዎች እጅ ስር መከማቸቱ ሲሆን ፣ ቀድሞ በጣም ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ይታይባቸው የነበሩ ሀገራት ሳይቀሩ የሀብት ስርጭታቸው ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየሰፋ ይገኛል ። ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የምትሆነው ስዊድን ስትሆን በአለም ላይ በጣም ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል ያላት ሀገር ስትሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ሀብታሞቹ የተሻለ ክፍያን ስለሚያገኙና ከውጭም እየገባ ያለው ስደተኛ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት በሀብታሙና በደሀው መሀከል ያለው የሀብት ስርጭት መዛባት እየጨመረ በመምጣት ላይ ይገኛል ።

ይህ ብቻ ሳይሆን ከፖሊሲዎች  ውጪም እንዲሁ የአለም ህዝብ ቁጥር መጨመር ፣ እንዲሁም የተፈጥሮና ያካባቢ ሀብቶች በተወሰነ እጅ በኋላ አዲስ የሚመጣው ትውልድ ሁሉም ነገር በሌሎች ከተያዘ በኋላ በሚወለድበትና በሚያድግበት ወቅት ለብዙሀኑ ህዝብ አንዳንድ የዘመናችን የምጣኔ ሀብት ሊቃውንት ሲገልፁት  ልማትን ሲገልፁት የወደፊት ትውልዶችን ሀብት ሳያሟጥጡ አሁን መኖር የሚለ ል አሰዲስ ገለፃ ሰጥተዋል ። እነኚህ ሁሉ ስጋቶች ለዲሞክራሲና ለአለማችን ስልጣኔዎች ስጋትን ሊደቅኑ የሚችሉ ናቸው 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s