የአለማችን ምጣኔ ሀብት

የአለም ምጣኔ ሀብት እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ባደጉት የምእራብ ሀገራትና በጃፓን ቁጥጥር ስር ሆኖ ቆይቷል ። ይሁን እንጂ በቅርቡ የአውሮፓና የአሜሪካ ሀገራት በአለም የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ላይ ያላቸዉ የበላይነት እየተሸረሸረ እየመጣ ሲሆን ሌሎች ሀገራት በተለይም የእስያና የላቲን አሜሪካ ሀገራት በአለም የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ያላቸው አንፃራዊ ድርሻ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል።አውሮፓውያን በተለይ ከህዳሴው ዘመን በኋላ ላለፉት አምስት መቶ አመታት ያልተቋረጠ የሳይንስን፣ የቴክኖሎጂን እና የኢኮኖሚ ብልፅግና ዉስጥ ሲኖሩ አልፎ አልፎ ከተደረጉየአንደኛውና የሁለተኛውን ጦርነቶች ከመሰሉ አውዳሚ ከነበሩ ጦርነቶች በስተቀር፣ የተቀረዉ አለም ግን እንደውም ወደታች በመውረድ የነበረውን ደረጃ በማጣት በኋላቀርነትና በድህነት ዉስጥ ሲዳክር ያለምንም እድገት ቆይቷል።

ይሁን እንጂ በተለይ በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ዘመናዊ እውቀት እየተስፋፋ ፣ ሌሎቹ በማደግ ላይ ያሉትም ሀገራት ካደጉት ሀገራት እኩል ለመሆን እድል ያገኙበት ክፍለ ዘመን በመሆን ላይ ይገኛል። ብዙዎቹ በማደግ ላይ ያሉት ሀገራት ከቅኝ አገዛዝ የተላቀቁበት ክፍለ ዘመን ቢሆንም ወዲያውኑ ከቅኝ አገዛዝ እንደወጡ ወደ እድገትና ልማት አልገቡም ።አንዳንዶቹ ቅኝ ገዢዎች ትተዋቸዉ የሄዷቸዉን ችግሮች በማስታመም ሌሎቹ ደግሞ ራሳቸዉ በምሁራኖቻቸውና በልሂቃኑ መሀከል በተፈጠረ የፖለቲካና የፍልስፍና ልዩነቶች ምክንያት ወደ እርስ በእርስ ጦርነቶች ሲያመሩ ፣ በግርግር በርካታ ሀገራት በወታደራዊ አገዛዝ ስር የወደቁበት ሁኔታም ተፈጥሮ ቆይቷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በተለይም ከእስያ ሀገራት የኢኮኖሚ ስኬት በኋላ በርካታ ሀገራት መነሳሳትን በመፍጠራቸዉ ሌሎች ሀገራትም በጣም ደሀ ሆነው የቆዩት የአፍሪካ ሀገራት ሳይቀር የተለያዩ ተስማሚ ፖሊሲዎችን በመቅረፅ የያገራቸውን ምጣኔ ሀብት ለብዙ አመታት ተኝቶ ከነበረበት በማንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

ምንምእንኳን የአለም ባንክና በተለይም የአለም የገንዘብ ድርጅት በርካታ ትችቶች ቢሰነዘርባቸውም ፣ለዚህም አንዱ ምክንያት የአለም የገንዘብ ድርጅትን የበላይ ሀላፊነትን አውሮፓውያን ፣ የአለም ባንክን አሜሪካውያን ላለፉት በርካታ አስርት አመታት ድርጅቶቹ ከተመሰረቱባቸው ጊዜያት ጀምሮ የሌሎች ሀገራት ዜጎች ከዚህ በመገለላቸው ምክንያት ብሪክስ የተባሉት ሀገራት የራሳቸውን የልማት ባንክ ለማቋቋም እስከማሰብ ደርሰዋል። ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በኋላ የነፃ ገበያን ስርአት በመስበክና በርካታ ኮሚኒስት የነበሩ ሀገሮች ወደ ነፃ ገበያ ስርአት እንዲመለሱ ከፍተኛ እገዛን አድገዋል ። በእርግጥ በአንዳንድ ሀገራት ለውጡ በተፋጠነ ሁኔታ እንዲካሄድ አንዳንድ መራር የሆኑ እርምጃዎችን ለምሳሌ የሰራተኛ ቅነሳ፣የመንግስትን ድርጅቶችን ወደ ግል ማዛወር የመሳሰሉት አወዛጋቢ ከሆኑ የተቋማቱ እርምጃዎች ይታወሳሉ ። ከዚህም ሌላ ደግሞ እነዚህተቋማት ለደሀ ሀገራት ላይ እርዳታንና ብድር ለመስጠት ቅድመ – ሁኔታንና ግዴታዎችን ማስቀመጣቸዉ በከፍተኛ ትችቶችን አስነስቶባቸዋል። በተለይም የአለም የገንዘብ ድርጅት ጠንካራ አበዳሪ እንደሆነም ይታወቃል ፣ ለሀገራት ጥብቅ መመሪያዎችን በማውጣትና ያንንም መከተላቸውን ሳያረጋግጥ ምንም አይነት ብድር እንደማይሰጥም ይታወቃል ።

እነኚህ አለም አቀፍ ተቋማት አመሰራረታቸው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ስለነበረ ከበርካታ አስርት አመታት በኋላ የህጋዊ ውክልናቸውና ተቀባይነታቸው ጥያቄ ምልክት ውስጥ ቢገባ  አስገራሚ አይሆንም ። እነኚህ ተቋማት ሲመሰረቱ ፣ የአለምን 80 በመቶ ሀብት እሚያመርቱት ምእራባውያን የነበሩ ሲሆን ለዛ ውስጥ ደግሞ ግማሹን የምታመርተው ደግሞ አሜሪካን ነበረች ። ይህ ሁኔታ በበርካታ አስርት አመታት በኋላ ተለዋውጧል ።  

ለምሳሌ በአለም የገንዘብ ድርጅት ውስጥ ያለው የድምፅ መስጠት አብዛኛው ሀይል ያለው በአሜሪካኖች እጅ ሲሆን ከሷ ቀጥሎም አውሮፓውያን ናቸው ፤ ነገር ግን አሁን ባለው የአለም የኢኮኖሚ ሁኔታ ሲታይ ግን አውሮፓውያን ብቻ ሳይሆኑ አሜሪካም ጭምር የድሮ አቅም የሌላት ሲሆን ፣ ሌሎች ያደጉና አቅምን የፈጠሩ ሀገራት ቻይናን ጨምሮ ምጣኔ ሀብታቸውን አቅም በሚያንፀባርቅ ሁኔታ በድርጅቱ ውስጥ ውክልናና ድምፅ የመስጠት ድርሻ የላቸውም ። ለዚህም ሀያላኑ ሀገራት ያላቸውን አቅም አሳልፈውለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው እነኚህ ተቋማት ብዙሀኑን የአለም ሀገራትን አሳታፊ ሆነው ሰፊ መሰረት ያለው አለም አቀፋዊ ውክልና ሊኖር አልቻለም ።

አንዳንድ ጊዜም በራሳቸው ሀገር የማያደርጓቸውን ነገሮች ደሀ ሀገሮች እንዲያደርጓቸው መገፋፋታቸው ብሎም ደሀ ሀገሮች የነሱን ምክርና ፖሊሲ ካልተቀበሉ እርዳታና ብድር እስከ መከልክል ድረስ መድረሳቸው ተሰሚነታቸውንና ፣ የበላይና የበታች ግንኙነት አይነት ግንኙነትን መፍጠራቸው ተደማጭነታቸውን በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ አድረጓል።

ሩስያ ከጥቂት አመታት በኋላ ሩስያ ከአለም አምስተኛ ግዙፍ ምጣኔ – ሀብት ይኖራታል ተብሎ ይገመታል ። ሩስያ ያንሰራራችው ባላት የተፈጥሮ ሀብት ነው የሚሉ አሉ ይሁን እንጂ ያ ነገሮችን በጣም አቅሎ ማየት ሊሆን ይችላል ። ሩስያ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሀገር ፣ ሰፊና ለግብርና ተስማሚ የሆነ መሬት ለያላት ሀገር ስትሆን፤ ይሁን እንጂ አንዳንድ ሩስያውያን እንደሚሉት ሩስያ ግዙፍ የሆነው የነዳጅና፣ የተፈጥሮ ጋዝና ሌላም የማእድን የተፈጥሮ ሀብቷ ጠላት ሆኖባታል ፣ ይህንን የሚሉት ምክንያት የዚህን ሀብት በመጠቀም ስልጣን ላይ የሚቆይ መንግስትንና ፣ የጥቂት ሀብታሞችን መደብ ማለትም ኦሊጋርኮችን በመፍጠሩ ነው ።

     የምእራባውያን ምጣኔ – ሀብት በእዳ ላይ የተመሰረተ መሆኑ ውሎ አድሮ ከአትላንቲክ ወዲህና ወዲያ ማዶ ላሉት ሀገራት ጤና የሚሰጥ ነገር አልሆነም ። መንግስታቶቻቸው ከአጠቃላይ አገራዊ ምርቶቻቸው በላይ እዳ ውስጥ መዘፈቅ ውሎ አድሮ እየፈጠረ ያለው ችግር ፣ ባንኮችንም ጭምር ይዞ በመውረዱና በማክሰሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቀድሞ ወደ በሩበት የምጣኔ – ሀብት እንቅስቃሴ ደረጃ መመለሳቸው ፈታኝ እንደሚያደርገው የታወቀ ነው ።

ባንኮች ላይ መመስረቱ ፣ አጠቃላይ ምጣኔ – ሀብቱ ከሚያመኘጨው ትርፍ ምርታማ ከሆነው ዘርፍ ይልቅ ወረቀቶችን በማገለባበጥ ላይ የተመሰረተው በገንዘብ ስርአቱ የገንዘብ ዘርፉ ለብቻው 40 በመቶውን ሲወስድ ፣ በአንፃሩ ምርታማ የሆነው ዘርፍ የተቀረውን ይወስዳል ፣  በዚህም ምክንያት አጠቃላይ ምጣኔ – ሀብቱ ከሚያመነጨው ሀብትና ትርፍ በግመታ (Speculation) ላይ የተመሰረተው የገንዘብ ዘርፉ ያንን ሀብት በግመታ ማክሰሩና ማባካኑ ፣ ለሀገራቱ ከፍተኛ ኪሳራን ፈጥሯል ።

ቀድሞ ብዙም ቦታ እማይሰጣቸው ሀገራት የአለምን ንግድ ያንቀሳቅሳሉ ተብለው እሚጠበቁ ሀገራት አሉ ። ለምሳሌ ካላቸው ቁልፍ ከሆነ መልከአ – ምድራዊ አቀማመጥና ፣ ካላቸው ወጣት ህዝብ እንዲሁም በአንፃራዊነት የኢንዱስትሪ መሰረት ምክንያት ኢንዶኔዥያ፣ ቬትናምና ግብፅ በአለም የንግድ ስርአት ውስጥ ቁልፍ ቦታን ይይዛሉ ተብለው ይጠበቃሉ ። ግብፅን ብንወስድ በአውሮፓ ፣ቱርክ፣ እስያ እና በአፍሪካ መገናኛ ማእዘን ላይ የምትገኝ ሀገር እንደመሆኗ ፣ የአለም ንግድ እሚንቀሳቀስባቸው እሚተላለፍባት ቁልፍ ሀገር ስለሆነችና  በአንፃራዊነትም እያደገ ያለ ኢንዱስትሪና ወጣት ህዝብ ስላላት ለንግድ ያላት ቦታ እየጨመረ እንደሚሄድ ተገምቷል  ሲሆን የሌሎቹ ሀገራትም ከላይ የተጠቀሱት ሀጋራትን ተመሳሳይ ነው ።

ቆዳን ወደ ጃኬት ፣ ቦርሳና ጃኬት ቀይሮ ወደ ውጪ መላክ የበለጠ ገቢም የሚያስገኝ በሚሆንበት ወቅት ቆዳውን በጥሬው መላክ የበለጠ ወጪን የሚያስከትል ነው ። ቀድሞ የምእራባውያን ኢንቨስተሮች ሀብታቸውን ወደ ቻይና የሚልኩ የነበረ ሲሆን ፣ ነገር ግን በቻይና ያለው የጉልበት ዋጋ ከ400 እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር ሲሆን ፣ በአንፃሩ በሀገራችን ያለው የጉልበት ዋጋ (ደሞዝ) 80 ዶላር ብቻ ነው ። ይህም የውጩ ባለሀብቶች ርካሽ በሆነ ሁኔታ በኢትዮጲያ ውስጥ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርቶችን ማምረት ያስችላቸዋል በ2012 ዓ.ም. በተጠኑ ጥናቶች መሰረት ። ይህም በርካታ የዚህ አይነተኛ ኢንዱስትሪዎች በሀገራችን እንዲቋቋሙ በርን ይከፍታል ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s