የሰዎች ባህሪ ለመሪነት ስኬት

የመጀመሪያዎቹ አይነቶች ሰላማዊ የሆኑና ሽኩቻ ውስጥ የማይገቡ ፣ እንዲሁም ራሳቸውን ከውድድር የሚያርቁ ሲሆኑ ፤ በአብዛኛው የዚህ አይነት ሰዎች ሰላማዊ ህይወትን የሚመሩ ናቸው ። ምክንያቱም በየትኛውም አይነት ውድድርና ውስጥ ስለማይገቡ ከሰዎች ጋር የመጋጨት እድላቸው አነስተኛ ነው ። ነገር ግን የዚህ አይነት ሰዎች ችግር ምንድነው ቢባል ወደ ከፍተኛው የሃላፊነት ደረጃመ ብዙም አይታጩም ፣ ምክንያቱም ከእውነታው ጋር ብዙም ሰስለማይዛመዱና በገሀዳዊው  አለም ካለው ውድድርና ፉክክር ጋር ብዙም ትውውቅና ፣ ለመሳተፍም ፈቃደኝቱ ስለሌላቸው ሲሆን በአብዛኘ! ኛው ባሉበት የመቆየት ፣ በተደጋጋሚም ሌሎች አብረዋቸው ሲሰሩ በነበሩ ሰዎች እየተቀደሙ ይሄዳሉ  ።

ሁለተኛው አይነቶች መጀመሪያ ላይ ባልጠረጠሩ ሰዎች መሀከል ፍላጎታቸውን ማሳካት ወይንም በቡድን ውስጥ የተደበቀ አጀንዳቸውን ማስፈፀም ይሆንላቸዋል ። በአንድ ከባቢ ወይም ሁኔታ ውስጥ የዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰዎች  ይኖራሉ ። ውሎ አድሮ ማንነታቸው እየታወቀ ስለሚሄዱ ፣ብዙውን ጊዜ በባህሪያቸው ምክንያት እየተፈሩና ስለሚሄዱወደ ከፍተኛ የስልጣን ደረጃ አይታጩም ። ነገር ግን አልፎ አልፎ ተሳክቶላችቸው ከፍተኛ ስልጣንን ሊጨብጡ የሚችሉ ሲሆን ፣ ነገር ግን እየቆዩ ሲሄዱ ብዙ ሰዎችን ስለሚያስቀይሙ መጨረሻ ላይ የማይገፉት ግድግዳ ያጋጥማቸዋል ፣ ይህም ውድቀታቸው ይሆናል ። የዚህ አይነት መሪዎች ስልጣናቸውን ከላይ ከመለኮት የተሰጣቸው አድርገው የሚቆጥሩና በስልጣናቸው ላይ ምንም አይነት ፈተናን ወይንም ከማንም መፈታተን እንዲመጣባቸው የማይፈልጉ ናቸው ። ፍፁም ታዛዥነትን ከሌሎች የሚጠብቁ ሲሆን ማንም በምንም አይነት መንገድ ማንም እንዲፈታተናቸው የሚፈቅዱ አይደሉም ። አልፎ አልፎም ከሌሎች በጥቂቱም ቢሆን ላቅ ያለ ችሎታ ያላቸው ናቸው ። በአንፃራዊነት እነኚህ ከሌሎች የበለጠ ብልሆች ስለሆኑ ከነሱ የበለጠ ችሎታ ያለው ሰው ካለ የሱን ስራ የራሳቸው አድርገው በማቅረብ የራሳቸውን ስምና ዝና ጎላ ብሎ እንዲታይ ያደርጋሉ እንጂ እንደ ሌሎቹ እውቀትን በማባረር የሚወቀሱ አይደሉም ፣ ይህም ቢሆንም ግን ከተወሰነ በላይ ሊያስኬዳቸው እንደማይችል ይታወቃል ።

ሶስተኛው አይነት ሰዎች ደግሞ ፣ ሁለቱንም አጣምረው የያዙ ማለትም በእውነተኛው አለም ያለውን ፈተና በአግባቡ የሚረዱና ለዛም እውቅና የሚሰጡ ነገር ግን ደግሞ በጎውንም መጥፎውንም ነገር በሚዛናዊ አይን የሚያዩናቸው ። በማድረግ ብቻ ያልተወሰኑ ናቸው ፤ እነኚህ በአብዛኛው ሚዛናዊ የሆነ ፍርድን አተያይን የሚከተሉ ሲሆኑ ፣ በአብዛኛው ለመሪነት የሚታጩ ናቸው ። በፖለቲካው አለም ብንወስድ በተለይም በአሁኑ ዘመን መራጩ ህዝብ ከፍተኛ ግንዛቤ ያለው እየሆነ ስለመጣ የዚህ አይነት ሰዎች በቀላሉ የህዝን ድጋፍን አግኝተው ወደ ስልጣን የመምጣት እድላቸው ሰፊ ነው ። የዚህ አይነት ሰዎች በአሁኑ ዘመን የፖለቲካ ትክክለኛነት ከምንም ነገር በላይ እውቅና በተሰጠውና ፣ መሪዎች በተለይም በከፍተኛ ደረጃ ያሉት በአነጋገርም ሆነ በባህሪ  የፖለቲካ ትክክለኛ መሆን በሚጠበቅባቸው መዘን ተፈላጊዎች ናቸው ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s