አሜሪካ እንደ ሮማ ኢምፓየር ?

አንዳንድ የአለምን የፖለቲካ፣ የምጣኔ-ሀበት የወታደራዊና የጂኦ-ፖለቲካዊ አሰላለፍን የሚታዘቡ ታዛቢዎች የምእራባውያን የበላይነት እያበቃለት ነው የሚል ትንታኔን በመስጠት ላይ ሲገኙ ፣ የአሜሪካንንም ማቆልቆል ከጥንቱ የሮማውያን ኢምፓየር አወዳደቅ ጋር ያመሳስሉታል ፡።

የአሜሪካ ገናናነትና የሮማ ኢምፓየር ተመሳሳይነትም ልዩነትም አላቸው ። ሮማውያን የማይመስሏቸውን ህዝቦችና አገሮቾችን በግዛትነት ሲያስተዳድሩ የነበረ ሲሆን ይህም ሰሜን አፍራካን ፣ መካከለኛው ምስራቅን እየሩሳሌምን ጨምሮ እንዲሁም ምእራብ አውሮፓን እስከ እንግሊዝ ድረስ የገዙ ሀያላን ነበሩ ። በአንፃሩ አሜሪካውያን ቅኝ ግዛትን ያስዳደሩ አይደሉም ፣ ከራሳቸው ግዛት ውጪ ። የሮም አወዳደቅ በታሪክ እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ የውድቀት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ ነው ።  

ይሁን እንጂ አሜሪካ ምንም እንኳን የበላይነቷን እያጣች ብትመጣም አንደ ሮም ግን ጨርሶ ትንኮታኮታለች ማለት አይደለም ። ያላት የቴክኖሎጂ የበላይነት እንዲሁም ያሏት ግዙፍ ኩባንያዎች እንደ አፕል ፣ ማይክሮሶፍት ፣ ጎግል ፣ ያሆ እና ኮካ ኮላ የመሳሰሉት እንዲሁም በሳይንስ ምርምርና ፈጠራ «ሪሰርችና እና ልማት» በመሳሰለው ከአለም መሪነቷን በቀላሉ እንደማያሳጧት መገመት ይቻላል ። እንዲሁም ስርአተ – መንግስቷ በአንፃራዊነት ያላት የዲሞኮረክራሲ ስርአት እንደ ጠንካራ ጎን ሊታይ ይችላል ።

 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s