ቁሳዊው ህብረተሰብ

ምእራባውያን በካቶሊክ አስተምህሮ ላይ በማሮርቲን ሉተር አማካይነት አምፀው «ሪቮልት» አድርገው የፕሮቴስታንት ሀይማኖትን ከተነሳ በኋላ ፣ ሀብትን መፍጠር ቅዱስ ተግባር መሆኑን ካሰመሩበት በኋላና ታላላቅ ፈላስፎቻቸውም ቡራኬያቸውን ከሰጡ በኋላ ሀብትን የመፍጠሩን ሂደት ሲያጠናክሩ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ግስጋሴያቸውም ላለፉት አምስት መቶ አመታት ቀጥለውበት ቆይተዋል ። ለምሳሌ ጀርመናዊው የማህበሰረብ ሊቅ ማክስ ዌበር እንደሚለው የካቶሊክ ሀይማኖት ስለ ስራና ሀብት ያለው አመለካከት «ወርክ ኤቲክ» ለብልፅግና እንቅፋት ነው የሚል ሲሆን ፣ እንዲሁም የክርስትና ሀይማኖት «ሀብታም መንግስተ-ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ብትሾልክ ይቀላታል» ሲል ይናገራል ። የተሀድሶ «ሪፎርሜሽን» ዘመን በሉተር አማካይነት መንገዱ ከተቀደደ በኋላ ግን እንደውም አንድ ሰው ሀብታም ሲሆን እግዝአብሄር ይወደዋል ፣ አንድ ሰው ሀብትንና ፀጋን የሚያገኘው እግዝአብሄር ሲወደው ነው በሚል አስተምህሮ ተተክቷል ።

በአንፃሩ ግን አይሁዳውያን ከጥንት ጀምሮ ሀብትን በተመለከተ እንደ ክርስትና ሀይማኖት ብዥታን የሚፈጥሩ አመለካከቶች ነገሮች የሉባቸውም ። አይሁዳውያን አራጣ ማበደርም ሆነ ማንኛውንም የንገድ ስራን ሲሰሩ የኖሩ ሲሆን ጥንትም ሆነ በዛሬው ዘመን በአለም ላይ ሀብታሞች አይሁዶች ዋነኞቹ ናቸው ። ለምሳሌ የቬኒሱ ነጋዴ የተሰኘው የዊሊያም የሸስፒር ስራ ሻይሎክ የተሰኘው ጨካኝ አራጣ አበዳሪ አይሁድ የሰውን ስጋ እስከመቁረጥ ድረስ ጭካኔ እንደነበረው የሚያሳይ የልቦለድ ስራ ነው ።

ከመፅሀፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ሙሴ ጀምሮ አብረሀምም ሆነ የሱ ልጆች ያእቆብ ፣ እንዲሁም የግብፅ ፈርኦን አማካሪና በጅሮንዱ የነበረው ፈርኦንን እጅግ ባለፀጋ ያደረገው የነበረው ዮሴፍ እንዲሁም ታጋሹ እዮብ ጭምር በዘመናቸው እጅግ ባለፀጋና ሀብታም እንደነበሩ መፅሀፍ ቅዱስ ያረጋግጣል  ። የጥንት ባቢሎናውያንና ፣ የግብፅ ስልጣኔ ባለቤት የነበሩት ፈርኦኖችም እጅግ ሀብታምና ባለፀጋ እንደነበሩ በታሪክ የተረጋገጠ ሀቅ ነው ።

በእርግጥ መፅሀፍ ቅዱስ አንድ ሰው ሳይሰራ መብላት እንደሌለበትና እግዝአብሄር አዳምን «ለፍተህ በወዝህ እንጀራን ትበላለህ» ብሎ እንዳለው መፅሀፍ ቅዱስ ገና ከጅምሩ ይገልፃል ። ሰው እስከ ሰራ ድረስ ሀብትንና ፀጋን ለማግኘት መሆኑም አሌ አይባልም ።

በአሁኑ ዘመን ጨካኝ መሆን እንደማወቅና እንደ ትክክለኛ የማወቅ ወይንም አራዳ የመሆን ድርጊት ተደርጎ  የሚወሰድበት ወቅት ነው ። በአሁኑ ወቅት የምንኖርበት ማህበሰረብ ስኬትንና የሚለካው በቁሳዊ ሀብት መሰብሰብ እና ማከማቸት ነው ።

ቁሳዊ ሀብትም የህይወትን ትርጉም የሚሰጥ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል ። ይህም በምእራቡ አለም ምንም እንኳን በምእራባውያን ከፍተኛ ሀብትን ቢፈጥሩም ፣ በተቃራኒው ግን ለገንዘብ ብሎ እርስ በእርሱ የሚገዳደል እና እጅግ የላላ ስነ- ምግባራዊ መሰረት ያለውን ህብረሰተብን ነው የፈጠሩት ። ለቁሳዊ ሀብት ስኬት መሯሯጥ የሚቅበዘበዝና ፣ እረፍት የለሽ ፣ እንዲሁም ባለው የማይረካ ህብረተሰብ እንዲፈጠር አድርጓል ። ይህ ከምእራብ ሀገራት የፈለቀው አስተሳሰብ ወደ ተቀረው ዓለምም የተስፋፋ ሲሆን

በአንድ በኩል ህብረተሰቡ ሌላ ጥያቄ እንሰዳያነሳ ይሄው ቁሳዊ ፍላጎትህ ተሟልቶልሀል በሚል አቅጣጫውን ለማስቀየር በመሪዎቹ በኩል ጥረት እንደሚደረግ ልብ ይሏል ። ይህም ሌላ ማህበረሰባዊ እድገት ማለትም መንፈሳዊ እና ህሊናዊ ንቃቶች ሳይኖሩት ቁሳዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩርና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ጉዳዮች ግንዛቤ የሌለውና ጥያቄን የማያነሳን ህብረተሰብ ለመፍጠር ረድቷል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s