ነፃነት

ነፃነት ማለት ምን ማለት ነው ? ነፃነት ምንድነው ? ነፃነት ለብዙ ሰዎች ውጫዊ የሆኑ የነፃነት መገለጫዎች ማለትም ከቅኝ አገዛዝ ነፃ መውጣት ፣ ከብዝበዛ መላቀቅ ፣ በኢኮኖሚ ራስን መቻል ወዘተ አድርገው የሚወስዱት ነገር ነው፣ ግን ነፃነት ከላይ የተጠቀሱት ማለት ብቻ አይደለም ።
ነፃነት ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ብቻ የሚገለፅ አይደለም ። ከዚያ ይልቅ እውነተኛው ነፃነት ውስጣዊ በሆኑ ነገሮች የሚገለፅ ነው ። ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ነገር የህሊናዊ ንቃት «ኮንሸስነስ» ማደግ ሲሆን በዚህም ምክንያት ህሊናዊ ንቃት አንድ ሰው በሁለት መንገድ ሊጎናፀፍ ይችላል ። አንኛው ሰውየው ያሳለፋቸው አስቸጋሪና ውጣ ውረድ የበዛባቸው ሁኔታዎች ለሰውየው የተሻለ ንቃትን እንዲጎናፀፍ ያስችል ።
በህይወት ውስጥ ስኬታማ መሆን ለሰዎች በተወሰነ ደረጃ ነፃነትን ያጎናፅፋል ። ያ ሰው ለራሱ እሚፈልጋቸው ነገሮች ከተሟሉለት እና በሌሎች ሰዎች ለካይ ጥገኝነት ከሌለበት ለነፃነቱ አንድ ዋስትና ነው ። ነፃነት በህይወት ስኬት ብቻ የሚመጣ ነገር አይደለም ። ከዚያ ይልቅ የህሊናዊ-ንቃት እና የግብዛቤ መጨመር አንድን ሰው የበለጠ ነፃ ያደርገዋል ።
ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰው ራሱን ፈልጎ ሲያገኝና ራሱን መሆን ሲጀምር ነፃነት ይሰማዋል ። የሚፈልገውንና የሚያስደስተውን ስራ ሲሰራ… ወዘተ የሰውን ነፃነት የሚጨምር ነገር ነው ። ይሁን እንጂ አንድ ሰው የሚፈልገውን ስራ መስራት የሚችለው መጀመሪያ ራሱን ማወቅ ሲችል ነው ። ራሱን በትክክል የማያውቅ ሰው በሚገፈልገው ሙያ ስራ ላይ ሊሰማራ አይችልም ። አንድ ሰው በጣም በሚወደው ሙያ ላይ ሲሰማራና በዚያ ዘርፍ ስኬታማ መሆን ሲጀምር ራሱን ፈልጎ አገኘ ይባላል ። ለብዙ ሰዎች ህይወት ውስጥ በጣም ፈታኝ ነገር ራስን ፈልጎ ማግኘት የመጀመሪያው ሲሆን ሁለኛው ደግሞ በብዙ ጭንቅ ተፈልጎ የተገኘውን የራስን ማንነት የመከተል ድፍረት ነው ።
ብዙ ሰዎች የማያስደስታቸውን ፣ ነገር ግን በማህበረሰቡ ዘንድ እንደ ትልቅ ነገር የሚታይ ወይንም ክብርን ሊያስገኝላቸው የሚችልን ነገር ሲከተሉ ወይንም ሲሰሩ ይታያሉ ። ይሄ በአንድ በኩል ሰው ለመኖር ሲል ፣ ምንም እንኳን ያ ነገር ያን ያህል ባያስደስተውን ያን ነገር እያደረገ ወይም እየሰራ ሊኖር ግድ ሊሆንበት ይችላል ፤ ይሄ በአንድ በኩል በምንኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ተቃርኖን ላለመፍጠር ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ያ ነገር መተዳደሪያችን ከሆነ መከተል ግድ ሊሆንብን ይችላል ። ነገር ግን አንድ ሰው ውጫዊ ተቃርኖን ሳይፈጥር ውሰጣዊ ማንነቱን ማስከበር ይችላል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s