የህይወት ሚስጥር ?

ብዙ ሰዎች የህይወትን ሚስጥር ለማወቅ ይጥራሉ ። ህይወት የተገለጠች መፅሀፍ ነች «Life is an Open Secret » ። ህይወት «የተገለጠች» መፅሀፍ ብትሆንም ሊያነቧትና ሊደረዷት የሚችሉት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው ። በዚህች ምድር ከተፈጠሩ እጅግ ታላላቅ ሰዎች አንዱ የሆነው ቡድሀ ፣ የደረሰበትን እውቀት ለሰዎች እንዲያስተምር ተከታዮቹ ሲገፋፉት የሰጠው መልስ ባስተምርስ ማን ይረዳኛል የሚል ነበረ ። ተከታዮቹም መልሰው ጥቂት ሰዎችም ቢሆኑ የሚረዱህ ጥቂቶች አሉ ብለው ነበረ እንዲያስተምር ሊያሳምኑት የበቁት ።

ከቅዱሳን አስተምህሮዎች የምንረዳው ይሄን ነው ። ምንም እንኳን የህይወት ሚስጥራት ሁሉ በቅዱሳን መፅሀፍ ውስጥ ሰፍረው እሚገኙ ቢሆንም ፣ ቅዱሳን መፅሀፍን በትክክል መረዳት እሚችሉ ጥቂቶች ናቸው ። በዚህች ምድር ከተፈጠሩ ታላላቆች የደረሱበትን እውቀት አስተላልፈው አልፈዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁኔታ እነሱ ሲመጡ ከነበረው ፈቀቅ አላለም ። ይህ የሆነበት የራሱ ምክንያት አለው ።

ሰዎች የታላላቆቹን አስተምህሮ አለመረዳትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እውነትን ለመከተል ድፈረትንና የውስጥ ንፅህናንና ፍቅርን ይፈልጋል ። ሌሎች ሰዎችን መውድድን ፣ የራስን ጥቅምን ከማስቀደም ይልቅ ለሰዎች ደህንነት ማሰብንና መጨነቅን ይጠይቃል ። የውስጥ ንፅህና የሌለው ፣ ውስጡ ንፁህ ያልሆነ ፣ ክፋትን በውስጡ ያዘለ ከእውነት ጋር ትውውቅ የለውም ፣ ሊኖረውም አይችልም ።

የካባላህን ሚስጥር ካወቁ መሀል ፣ ላኦ ዙም እንደዛው ሲሆን፣ ቡድሀም እንደዛው ነው ። ጥቂቶች ይረዱሀል ብለው ነው ። የሊቁን ፎስት ታሪክ እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢነት አለው ። ሊቁ ፎስት እውቀትን ከሰይጣን ጋር የተለዋወጠ ሰው ነበረ ። የአለምን ሚስጥር ሁሉ እንዲገልጥነትና በልዋጩም ነፍሱን ሰይጣን እንዲወስዳት ነፍሱን ለሰይጣን ለመስጠት  ከሰይጣን ጋር የተዋዋለ ሰው ነበረ ።

ኦከልትንም ብንወሰድ እንደዛው ነው ። ለብዙሀኑ ቢታወቅ አደገኛ ነው ተብሎ ስለ ሚታሰብ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን አንድ ሰው ፓሪስ ወይንም ለንደን ሳይሄድ እዚሁ አዲስ አበባ ተቀምጦ ማወቅ ይችላል ። በድረ-ገፅ ላይ መመልከት ይችላል ። ለምሳሌ ፕሌቶ ለጥቂት ፈላስፋዎች ብቻ ይሰጥ የነበረውን እውቀት በመፅሀፍ መልክ በመፃፉ በዘመኑ በነበሩት ልሂቅ ፈላስፎች ተተችቶበታል ። በየትኛውም የታሪክ ዘመን ልሂቃኖች እውቀታቸውን ለብዙሀኑ ለማካፈል ፈቃደኛ ሆነው አያውቁም ። ለዚህም ምክንያቱ በርካታ ነው ፣ በአንድ በኩል ልሂቃኑ የተቀረው ህብረተሰብ ሊረዳው አይችልም ብሎ በማሰብ ወይም ፣ እውቀት የሀይል ፣ የስልጣንና የሀብት ምንጭ ስለሆነ ሚስጥርነቱን ለመጠበቅ በሚል ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s