የቡድሀ መንፈስ

በዚህች ምድር ተፈጥረው ከተራመዱ እጅግ ጥቂት ታላላቅ ሰዎች ቡድሀ አንዱ እንደሆነ በርካታ የቡድሀን የህይወት ታሪክ በመረመሩ ሰዎች የተመሰከረ ነው ። በሰሜናዊ ህንድ አሁን ኔፓል ተብላ በምትታወቀው አገር ውስጥ ያለች የአንድ ግዛት ንጉስ ልጅ የነበረው ልኡሉ ቡድሀ ብዙዎች ሊያደርጉ የማይደፍሩትን ፣ ያን ሁሉ ምድራዊ ስልጣኑን ፣ ሀብቱን ትቶ መመነኑና ለሰው ልጅ መንፈሳዊ መገለጥ የደረሰበትን ለሌሎች ብርሀን መሆኑ በታሪክ አስደናቂ ድርጊት ሆኖ ይኖራል ። ቡድሀ የደረሰበት የአብርሆት ንቃት «Enlightenment» ደረጃ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ በኋላ የሚመጣው የሰው ልጅ በቀላሉ እንደማይደርስበት የታወቀ ነው ።

ለሰዎች ድርጊት ከፍተኛ ርህራሄና እዝነት «Compassion» የነበረው ቡድሀ የሰዎችን ድርጊት በሚገባ የሚረዳና ፣ ሰዎች ጥፋትንም ጭምር ለምን እንደፈፀሙ በእነሱ ቦታ ሆኖ የሚረዳ ሰው ነበረ ። ቡድሀ ከዛሬ 2500 አመት በፊት ያስረተማረው ትምሀርት እርሱ ከሞተ ከጥቂት ክፍለ ዘመናት በኋላ ሀይማኖት ሆኖ በደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት እስከ ሲሪላንካና ታይላንድ ፣ ቬትናም ፣ በርማ ድረስ ሊሰራጭ የበቃ ነው ፣ ወደ ሩቅ ምስራቅም ህንድን አልፎ ቻይናን አዳርሶ ኮርያን አቋርጦ ጃፓን ድረስ በዜን ቡድሂዝም እምነት የተገለጠ ነው ።

አንዳንዶች የንጉስ ልጅ መሆኑና በማህበረሱ ውስጥ የታወቀ መሆኑ አስተሳቡንና አስተምህሮውን በቀላሉ እንዲያሰራጭ እና ተቀባይነትን ለማግኘት ረድቶታል ይላሉ ። በካስት ስርአት በምትመራው ፣ እንዲሁም ከጥንት ጀምሮ የአለም የመንፈሳዊነት ማእከል ተደርጋ የምትወሰደውና ፣ ለመንፈሳዊ መምህሮቿ የምትሰጠው ከፍተኛ ክብርና ግርማ በምትሰጠው ህንድ ምንም እንኳን የሂንዱ እምነትን ቢተችም በህይወቱ ላይ የደረሰበት ነገር አልነበረም ።

እንደማንም አዲስ ነገርን በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ለማስፋፋት እንደተነሳ ሰው ግን ከማህበረሱ ተቀባይነትን አለማግኘትንና ፣ በመንደሮች ውስጥ ሊያስተምር በሚገባበት ወቅት በድንጋት መመታት ፣ እንዲሁም ሌሎች በህይወቱ ላይ አደጋዎችም ጭምር አጋጥመውታል ። ቡድሀ በሂንዱ ሀይማኖት ላይ ያቀረባቸው ትችቶች የሂንዱ እምነት ራሱን እንዲያሻሽል ረድቷል ተብሎ ይገመታል ።

አንዳንድ ታዛቢዎች ቡድሂዝም በምእራቡ አለም በአሁኑ ወቅት ተቀባይነትን ማግኘቱ ያስገርማቸዋል ። ከጥቂት አስርት አመታት ወዲህ ሰላማዊ የሆነው የቡድሂዝም እምነት በምእራብ ሀገራት በመስፋፋት ላይ ነው ። በነገራችን ላይ ቡድሂዝም ብቻ ሳይሆን የባሀኢ እምነትም በአሁኑ ወቅት በምእራቡ አለም ሰፊ ተቀባይነትን እያገኙ ያሉ የምስራቃውያን እምነቶች ናቸው ።

በአለም ላይ ታላላቅ መንፈሳዊ የመገለጥን ብርሀን ለሰው ልጅ ይዘው ብቅ ያሉ የተከሰቱት ከዚሁ ከምስራቁ የአለማችን ክፍል ነው ፣ እነኚህ የምስራቅ መንፈሳዊ ፀሀዮች ፣ እየሱስ ክርስቶስ ፣ ቡድሀ ፣ በሀኡላ ፣ ነቢዩ መሀመድን የመሳሰሉ ለሰው ልጅ ብርሀንን የፈነጠቁ ናቸው ።  

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s