የተዛባ የሀብት ክፍፍል

የአለምን የምጣኔ-ሀብት ታሪክ የሚመለከቱ ታዛቢዎች እንደሚናገሩት አለማችን ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ ማለትም ከሶሻሊዝም ስርአት መመስረት ወዲህ በአለም ላይ ከፍተኛ የሀብት ልዩነት እየተከሰተ ነው ። የተዛባ የሀብት ልዩነት እ.ኤ.አ. 1789 ከተከሰተው የፈረንሳዩን አብዮት ጨምሮ በአለማችን ላይ ለተከሰቱ አብዮቶችና የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ዋነኛ መንስኤ ነው ። 

ከበለፀጉት ሀገራት አሜሪካን ብንወስድ በዚህች ሀገር ያለው የሀብት ልዩነት በአለም ከፍተኛ ከሚባሉት አንዱ ነው ። ግብር ይጨመር ፣ አይጨመር የሚለው የአሜሪካ ፖለቲከኞች የምርጫ መከራከሪያ አጀንዳ ፣ የርእዮተ አለምና የኢኮኖሚ ፍልስፍና ጉዳይ ከሆነም ውሎ አድሯል ። የአሜሪካ ህልም «American Dream» ወደ «American Nightmare » ወደ የአሜሪካ አስፈሪ ቅዠት ተቀይሯል ብለው አሜሪካንን የሚተቹ ሰዎች ይናገራሉ ። በአሁኑ ወቅት በታላላቅ የአሜሪካ ከተሞች እምብርት ውስጥ በርካታ «ጌቶዎች» የድሆች የመኖሪያ ሰፈሮች እየተፈጠሩ እንዲሁም ይህን ተከትሎም ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ የወንጀል መበራከት ፣ እና የእስር ቤቶች መጨናነቅ እየታየ ነው ።

ዊንስተን ቸርቺል በአንድ ወቅት እንተናገሩት የካፒታሊዝም ስርአት ዋነኛው ችግር «የሀብት ክፍፍል አለማድረጉ» ነው ፣ ይህም ካርል ማርክስ የካፒታሊዝም ስርአት ዋነኛ ውስጣዊ ተቃርኖ በሚል የገለፀው ይሄን የተዛባ የሀብት ክፍፍል ሲሆን መንስኤውም ካፒታል ጉልበትን ስለሚበዘብዝ እንዲሁም የካፒታል ገቢ እያደገ ስለሚሄድ ፣ በአንፃሩ ግን የሰራተኛ ደሞዝ ዋጋ ግን የዚያን ያህል አለመጨመሩ ነው ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መግለጫ መሰረት በሀገራችን ያለው የሀብት ክፍፍል ፍትሀዊ እንደነበረ ተገልጿል ። ይህም እ. ኤ. አ. በ 2013 ዓ.ም. በተገለፀው መሰረት አገራት በአፍሪካ ፍትሀዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል ካለባቸው ሀገራት አንዷ ናት ። ይህም መልካም ዜና ሲሆን በዚህም ለወደፊቱ የሀገሪቱ ውስጣዊ የፖለቲካ መረጋጋት መሰረት ነው ።

የሀገራችን የሀብት ክፍፍል ፍትሀዊ ሊሆን የቻለው የራሱ ምክንያቶች አሉት ። ከ1966 አብዮት በፊትመ ምንም እንኳን በጊዜው ኮኢፊሸንት የሀገራችን የሀብት ክፍፍል ተሰልቶ ማወቅ ባይቻልም የነበረው የሀብት ክፍፍል እጅግ የተዛባ እንደነበረ መረዳት ይቻላል ። በነበረው የፊውዳል ስርአት ምክንያት ዋነኛው የሀብት ምንጭ የነበረው መሬት በጥቂት ታላላቅ ባላባቶች የተያዘ ስለነበረ ነው ።

በዚያን ወቅት የነበረው የሀብት ክፍፍል እጅግ የተዛባ በመሆኑ ምክንያት ችግሩን ለመፍታት አብዮት ማካሄድ አስፈልጓል ። ከዚያ በኋላ በ 1966ቱ አብዮት ወደ ስልጣን የመጣው «ካፒታሊዝም ሊያቆጠቁጥ ሲል ደረስኩበት» የሚለው ደርግ በሶሻሊዝም ስርአቱ ዋና ዋና የሆኑትን የሀብት ምንጮችን በመውረሱ ምክንያት ሀገሪቱ ስትደኀይ ዊኒስተን ቸርችል እንዳሉት የሶሻሊዝም ክፋቱ «ሁሉንም ማደህየቱ» ነው ። በዚሀም ምክንያት በደርግ 17 አመታት ውስጥ የግል ሀብት ስላልነበረ የተፈጠረ ሀብት አለነበረም ። ሁሉም እኩል ሲደኀይ እንዲሁም የግል ሀብት እንዲፈጠር የነበረው ሁኔታ ስላልተመቻቸ ድህነቱ ተንሰራፍቶ ቆይቷል ። መጀመሪያም ሀብት በሌለበት ሁኔታ ውስጥ የተዛባ የሀብት ክፍፍል ሊኖር እንደማይችል የታወቀ ነው ። ከዚህም በተጨማሪ በነበረው ጦርነት ምክንያት ራሱ መንግስትም ለልማት የሚያውለው በቂ ገንዘብ አልነበረውም ፣ በዚያን ወቅት መንግስት እንኳን የራሱን በጀት መሸፈን የሚያቅተው ጊዜ እንደነበረ የታወቀ ነው ።

ከዚያ በኋላ ግን የደርግ ስርአት ከወደቀ በኋላ የኢህአዴግ ስርአት ሲመጣ የግል ሀብትን የሚፈቅድ አዋጅን በማውጣቱ እንዲሁም የግል ኩባንያዎች ባንኮችን ጨምሮ እንዲቋቋሙ ስለፈቀደ የግል ኩባንያዎች ማቆጥቆጥና የግል ሀብት መፈጠር ጀምሯል ። አሁን ያለበት ሁኔታ ሀብት መፈጠር የጀመረበት ሁኔታ ነው ። ሀብት መፈጠር ሲጀምር የሀብት ልዩነቱ በአንድ ጊዜ አይሰፋም ፣ ነገር ግን ውሎ አድሮ የሀብት ልዩነቱ እየሰፋ መሄድ ይጀምራል ። ይህም በግልፅ በመታየት በሚጀምርበት ወቅት ግን ስለ ሀብት ክፍፍል ፍትዊነት ማውራት አስፈላጊ እየሆነ ይሄዳል ።

ምንም እንኳን የሀብት ክፍፍሉ በሀገራችን ያለው ፍትሀዊ ቢሆንምና ገና ወደ አሳሳቢ ችግር ደረጃ ባይደረስም ፣ የምጣኔ – ሀብት እድገት በራሱ ፖለቲካዊ ችግርን እንደማይፈታ የታወቀ ነው ። ለዚህ  ምክንያቱ በአንድ በኩል እድገቱ ለብዙሀኑ ሳይሆን ለጥቂቶች ትላልቅ ኩባንያዎች እና ነጋዴዎችና የህንፃና የተለያዩ ባለንብረቶች እጅ ስለሚገባ ሲሆን የብዙሀኑን ህዝብ የምጣኔ-ሀብት ችግር ወዲያው ስለማይቀርፍ ፣ እንደውም የዋጋ ግሽበትን በማባባስ ለመካከለኛውና ለደሀው ህብረተሰብ ክፍል የተባባሰ የኢኮኖሚ ችግርን ሊፈጥርና ብሶትን ሊፈጥር ስለሚችል ነው ። በሌላ በኩል ደግሞ ፖለቲካዊ ችግሮች በራሳቸው ከኢኮኖሚ የተለየ መሰረትና ምክንያትና የራሳቸው አካሄድና ምክንያት ያላቸው መሆናቸው የኢኮኖሚ ማደግ ብቻውን የአንድን አገር የፖለቲካ ችግር ሊቀርፍ አይችልም ።

ብዙውን ጊዜ የፖለቲካ ችግሮች ከሰብአዊ መብት አያያዝ ፣ ሀሳብን በነፃነት ከመግለፅና ከዲሞክራሲ ባህል መዳበርና ከነፃ ምርጫ ጋር የተያያዙ ናቸው ። ለምሳሌ ቻይናን ብንወስድ ምንም እንኳን ቻይና ምጣኔ-ሀብቷ አድጎ በአለም ከአሜሪካ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ብትደርስም ፣ በአንድ ፓርቲ ማለትም በኮሚኒስት ፓርቲው የበላይነት በምትተዳደረው እንዲሁም በማ ህዝባዊ ምርጫንና ነፃ ፕሬስን የማታውቀው ቻይና ፣ በፖለቲካ ነፃነት በኩል ግን ከአሜሪካም ሆነ በአጠቃላይ አገራዊ ምርት ከበለጠቻቸው የአውሮፓ አገራት ጋር ጨርሶ አትወዳደርም ።   

አንድ ምጣኔ – ሀብት እድገት ማሳየት በሚጀምርበት ወቅት አብዛኛው እድገት ወደ ትላልቅ ኩባንያዎች ፣ ባንኮችና የገንዘብ ተቋማት እንዲሁም በዘመናዊው ምጣኔ – ሀብት ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦት ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የታወቀ ነው ። እንደውም በአንዳንድ አገራት እድገት በሚመጣበት ወቅት የዋጋ ግሽበትን ስለሚፈጥር በመካከለኛውና በዝቅተኛው የገቢ ደረጃ ያለውን የህብረተሰብን ክፍል የሚያደኀይበት ወቀት በተደጋጋሚ በተለያዩ አገረት ሀገራት ተስተውሏል ። በምእራቡ አለም ሳይቀር ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት ይታይ በነበረበት በ1970ዎቹና 80ዎቹ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ሲታይ ነበረ ።      

በአገራችን ያለው የሀብት ክፍፍል ከህንድ ጋር ተመሳሳይነት ሊኖረው ይችላል ። በህንድ ኢኮኖሚያቸው በፍጥነት ቢያድግም ፣ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሆች በዚያች ሀገር አሉ ። በአንፃሩ እጅግ ሀብታም የሆኑና በአለም ስማቸው የሚጠሩ በርካታ ሀብታሞችም በዚህችው አገር ይገኛሉ ። ህንድ በአለም በርካታ ድሆች ያለባት ሀገር የመሆኗ እውነታ በምጣኔ – ሀብት እድገቷ ሊረጋገጥ አልቻለም ። ቻይና በአንፃሩ ከህንድ የተሻለ የሀብት ክፍፍል ያላት ቢሆንም ቻይናም ብትሆን ፣ በሀብታምና በደሀ ዜጎቿ መሀከል ያለው የሀብት ልዩነት የቻይናን አመራር መሳሰብ ጀምሯል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s