የተቃርኖዎች መኖር

ማንኛውም ነገር የራሱ ተቃራኒ አለው ፣ ሊኖረውም ይገባል ። የተቃርኖዎች መኖር በአንድ በኩል አንዱ ያላንዱ መኖር አይችልም ፤ ሁለተኛው ተቃርኖ ደግሞ አንዱ የአንዱን ጉድለት የሚያሟላ ተቃርኖ ነው ። ወንድና ሴት ፤ ብርሀንና ጨለማ – አንዱ አንዱን የሚያሟላና የጋራ ህልውና ያላቸው ናቸው ፣ ሌላው አንዱ አንደኛውን ሊያጠፋ የሚፈልግበት ሁኔታ የለም ፣ ከዚያ ይልቅ አንደኛው ያለአንደኛው ህልውና ሊኖረው እንደማይችል ስለሚገነዘብና እንዲሁም ተፈጥሮ ራሱ ያስገድደዋል ።

ሌላው የተቃርኖ አይነት ፣ ልክ ካርል ማርክስ እንደሚለው በሰራተኛና በካፒታሊስት መሐከል ያለው የአንዱ ህልውና ከሌላው ህልውና ጋር ተፃርሮ እሚቆምበት እና ውሎ አድሮ አንደኛው አንደኛውን የሚያጠፋበት ነው ።

ሄራክላይተስ የተሰኘው የጥንታዊ ግሪካዊው ፈላስፋ እንደሚለው የተቃርኖዎች መኖር ግድ ነው ። ጨለማ ካለ ብርሀን ፣ ወንድ ካለ ሴት ፣ መጥፎ ካለ ጥሩ ፣ ህይወት ካለ ሞት ፣ ወዘተ የመሳሰሉት ተቃርኖዎች ይኖራሉ ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s