አረቦችና ኢትዮጲያ

በአረቦችና በኢትዮጲያ መሐከል ያለው ግንኙነት «በወጃጅነትና ጥላቻ» love hate relationship የተሞላ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ፣  በአንድ በኩል አረቦች ከኢትዮጲያ ጋር በርካታ ሺህ አመታትን ያስቆጠረ የዘር ግንድ ትስስር ፣ የሀይማኖት እና የታሪክ ቁርኝት አላቸው ፤ በተለይም ከግብፅ፣ ከሳኡዲ አረቢያና ከየመን ጋር ያለው ግንኙነት ሰር የሰደደና በርካታ ቁርኝቶች የያዘ ነው ። ከግብፅ ጋር ያለው ግንኙነት ከኢትዮጲያ የሚነሳው የናይል ወንዝ ለግንኙነቱ ዋነኛ መሰረት ሲሆን በበጎም ይሁን በመጥፎ ይሄው ወንዝ የግብፅና የሱዳን ህልውና መሆኑ ዋነኛው የሶስቱ አገራት የግንኙነት መሰረት ነው ።

ከመልከአ ምድራዊ አቀማመጥ አንፃር ኢትዮጲያ ከግብፅ ይልቅ ለሳኡዲ አረቢያና ለየመን ትቀርባለች ። ከጥቂት መቶዎች የባህር ክልል ድንበር በኋላ እነኚህ ሁለቱ አገራት ለኢትዮጲያ ተዋሳኝ ሲሆኑ ይህም የአገራችን ዜጎች በስደት ከአገር ለመውጣት አንደ አማራጭ የሚወሰዱ ሆነው ተገኝተዋል ። በሌላ በኩል በነዳጅ ዘይት ምርት ሽያጭ እጅግ የከበሩት የመካከለኛው ምስራቅ አገራት «መጣያ ያጣ ገንዘባቸውን» ወደ ውጪ ሐገራት በመዋእለ-ንዋይ መልክ ማፍሰስ ይፈልጋሉ ። ለምሳሌ ሳኡዲ አረቢያ በረሀማ አገር ስትሆን ፣ የምግብ ሰብል ለማምረት አመቺ መሬት የላትም ፣ ነገር ግን ከነዳጅ ዘይት ሽያጭ ያገኘችው እጅግ የበዛ ገንዘብ ባለቤትም ነች ። ስለዚህ ይህን ገንዘቧን በመዋእለ- ንዋይ መልክ ወደ ኢትዮጲያ በማፍሰስ የምግብ ፍላጎቷን ቅርቧ ከሆነችውና በወንዞች የተንጣለለ ለም መሬትና የበርካታ ወንዞች ባለቤት ከሆነችው ኢትዮጲያ ማስገባት ይቀላታል ።  

ከስትራቴጂ አንፃር አረቦች ዋነኛ ቀንደኛ ጠላታቸው እስራኤል እንደሆነች አለም ያወቀው፣ፀሀይ የሞቀው ጉዳይ ከሆነ ክፍለ ዘመናት ተቆጥረዋል ። ለዚህም በአካባቢው አቀማመጧ ስልታዊና ቅርብ ከሆነችውና በቆዳ ስፋቷም ትልቅ ከሆነችው ኢትዮጲያ ድጋፍን ይፈልጋሉ ።Image

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s