የስልጣኔዎች ግጭት

አንዳንድ ሰዎች አሁን በምእራባውያንና በእስልምና አክራሪዎች መሀከል የሚደረገውን ትግል በምእራባዊው የጁዶ – ክርስትያንና (Judo-Christian) በእስልምና መሀከል የሚደረግ የስልጣኔዎች ግጭት አድርገው ይወስዱታል ። ሀይማኖትና ስልጣኔ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ። ነገር ግን ሀይማኖት እንደ ስልጣኔ ሊወሰድ ሊወሰድ አይችልም ። ሀይማኖት በተለያዩ ስልጣኔዎች ውስጥ መልኪኩን እየቀያየ የሚኖር እጅግ ዘመናትን አልፎ ህልውናው የሚቀጥል ነገር ነው ።  ስለዚህ ሰልጣኔና ሀይማኖት ሊጋጩ አይችሉም ። ግጭት ሊፈጠር የሚችለው በፖለቲካ ፣ በርእዮተ-ዓለም ፣ በአገራዊ ብሄራዊ ጥቅም ልዩነት በሚፈጠርበት ወቅት ነው ። ነገር ግን ለእነኚህ ሁሉ ግጭቶች ሀይማኖት ለክፍለ-ዘመናት እንደ ሽፋን ሆኖ ኖሯል ።

ስልጣኔዎች አንድ በአንድ ወቅት ተፈጥረው ፣ ቀስ ብለውንም የሚከስሙ ነገሮች ናቸው ። በአንፃሩ ሀይማኖቶች በተለያዩ ስልጣኔዎች ህልውናቸውን አስቀጥለው ለሺዎች አመታት መጓዝ እሚችሉ ናቸው ። ስልጣኔዎች በእውቀት የሚፈጠሩ ናቸው ። የሂሳብ ፣የሳይንስ፣ የጂኦሜትሪ የህክምና ፣ የመሳሰለው እውቀት ላይ ተመስርተው የሚስፋፉ እና የሚፋፉና የሚያድጉ ናቸው ። ስልጣኔዎች በአንድ ጀንበር አይፈጠሩም ። ሁሉንም በአለም ላይ የነበሩትን ሀያል ስልጣኔዎችን ብንወስድ እዛ ደረጃ ለመድረስ በርካታ ክፍለ ዘመናትን ፈጅተው ነው ። የስልጣኔዎች እውቀት እነሱ ተዳክመው በሚፈራርሱበት ወቅት ለሚቀጥለው ትውልድና ለሌላ አካና ባቢ እ አምደ ንዳንደዶቹ ሊተላለፉ ሲችሉ ፣ የአንዳንዶቹ እውቀት ግን ተቀብሮ ተረስቶ ይቀራል ። ለምሳሌ የጥንት ግብፃውያን የደረሱባቸው ስለ ነፍስ ፣ ስለ መሚ የአስከሬን ማድሪያ የመሳሰሉት እውቀቶች ሙሉ በሙሉ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ ሳይተላለፉ ቀርተዋል ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s