ካፒታሊዝምና የዲሞክራሲ ስርአት

በሊበራሊዝም ፖለቲካዊ ምጣኔ-ሀብት አስተሳሰብ መሰረት የካፒታሊዝም ስርአት ከዲሞክራሲ ስርአት ጋር አብሮ ህልውና ይኖረዋል ተብሎ ይታሰባል ። ይህም በምርጫ ስልጣን የሚያዝበትና ፣ ህዝቡ ራሱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ መሪዎቹን ራሱ እሚመርጥበት ስርአት ነው ። ጥያቄው ስርአቱ የዲሞክራሲ ስርአት መሆኑ ሳይሆን ይህ የዲሞክራሲ ስርአት የራሱን ህልውና መሰረታዊ መርሆዎቹን ሳይለቅ ምን ያህል መዝለቅ ይችላል የሚለው ነው ።

ታላቁ የግሪኩ ፈላስፋ ፕሌቶ ፖለቲካ መመራት ያለበት በፈላስፎች ነው ሲል ፤ አገርን የመምራትን ከባድ ሀላፊነትን ሊወጡ የሚችሉት እነሱ ብቻ ናቸው ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው ። የንግድ ሰዎች ግን እሚያስቡት ስለ ንግድና ስለ ገንዘባቸው ብቻ ስለሆነ አገርን ለመምራት የሚያስፈልገውን ንፅህናና ከሙስና የፀዳ አመለካከትን አይዙም በሚል እሳቤ ነው ። ለገንዘብ ብለው አገርን የሚጎዳ ድርጊትን ሊፈፅሙ ይችላሉ የሚል አመለካከት አለው ። ነገር ግን የአሁኑ የዲሞክራሲ ስርአት ግን በተዘዋዋሪ የሚመራው በሀብታም ኮርፖሬሽኖች ነው ፣ እንጂ ብዙሀኑ በመረጣቸው ፖለቲከኞችም አይደለም ።

የካፒታሊዝም ስርአትና የዲሞክራሲ ስርአት አብረው ምን ድረስ መጓዝ ይችላሉ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል ።

የካፒታሊዝም ሰርአት በሀብታሞች የኒውስ ኦፍ ዘወርልድ (The News of the World) ባለቤት የነበረው እንደ (Rupert Merdoc) ሩፐርት መርዶክ ፣ እና አሜሪካውያኑ (The Koch Brothers) የኮች ወንድማማቾች ባሉ ሀብታሞች ሊጠለፍና የሀብታም ኮርፖሬሽኖች ጥቅም አስጠባቂ ተቋም ሆኖ ቁጭ ሊል ይችላል ።

ለምሳሌ በምእራቡ አለም በተለይም በአሜሪካ ግዙፍ የጦር መሳሪያ ፋብሪካዎች ያሉ ሲሆን ፣ እነኚህ ፋብሪካዎች በጣም አትራፊ ሲሆኑ በፖለቲካ ውስጥ እጃቸውን የሚያስረዝሙ ናቸው ። ይህንንም በማየት ድዋይት አይዘንሀወር የተባሉት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በስልጣን ዘመናቸው መጨረሻ ላይ «ያልተቀደሰው ጥምረት» (unholy alliance) በማለት ሁኔታውን አስጥጠንቅቀው ነበረ ። ይሁን እንጂ ባንኮች፣ ግዙፍ ፋብሪካዎች ወዘተ በድጋፍ አሰባሳቢዎቻቸው አማካይነት የፖለቲካ ሰዎችን በቀላሉ መጠምዘዛቸው ለዲሞክራሲ ስርአት ህልውና አደጋ ነው ።

የካፒታሊዝም ስርአት ህጋዊ ተቀባይነቱን እያጣ በሚመጣበት ወቅት ያሉት አማራጮች ሶስት ናቸው ። አንደኛው ሰርአቱን አፍርሶ መልሶ መገንባት ሲሆን ልክ ጃፓኖች የፊውዳል ስርአትን ያፈራረሱት በስምምነት ነው ። ሰፋፊ መሬት ያላቸው ባላባቶች መሬታቸውን ለትናንሽ አራሾች በማከፋፈል የተሻለ የመሬት ክፍፍል ስርአትን መፍጠር ችለዋል ፣ ከፊውዳሊዝም ወደ ካፒታሊዝም ቀላል ሽግግርን ማድረግ ችለዋል ፣ ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ ያለምህረት ማሻሻያዎችን ማድረግ ፣ ሲሆን ሶስተኛው ማርክስ እንዳለው የስር ነቀል የሆነ አብዮትን ማካሄድ ናቸው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s