ከዚህም ከዚያም

ገናናነትና ስም
ስሙን የማይጠብቅ የኋላ ኋላ ገናናነቱን ማጣቱ አይቀሬ ነው ። በጣም ስልታዊ የሆኑ ተቀናቃኞች የተቀናቃኛቸውን ሰው ስም የዛን ሰው በማጥፋት ይጀምራሉ ። ምናልባት ገናናነት የቀድሞዎቹ በነገስታት ታሪክ ሊመስላቸው ይችላል ። ከቅርቡ እንኳን ስማቸውን ያጡ ወዲያውም የነበራቸውን ማንኛውንም ነገር ያጡ ሰዎች በርካታ ናቸው ። በተለይ በምእራቡ አለም የአንድ ሰው ተሰሚነቱ ፣ ገናናነቱ ወይንም ተወዳጅነቱ ጭምር በስሙ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ይታያል ። ገናና የሆኑ ሰዎች ሌላው ሰው እሚያከብራቸውን ህግጋት ለምንድነው እንደሌላው ሰው እማያከብሩት ? በነገራችን ላይ አንድ ሰው ትልቅ ስልጣንን ወይንም ሀይልን ወይንም ስምን ሲይዝ የሚኖርበትም ሀላፊነት እንደዛው ከባድ ነው ። በእርግጥ በዘመናችን በልሂቃኑና በተቀረው ህብረተሰብ መሐከል ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሐብት ፣ በእውቀት በአኗኗር የጎሉ ልዩነቶችም በመታየት ላይ ይገኛሉ ። ልሂቃኑ ሀብታቸው ፣ ዝናቸው የሚያስገኝላቸው የአኗኗር ደረጃ በጣም ከመስፋቱ የተነሳ ቀድሞ ከነበረው ሰፍቶ ይታያል ።

አይሁዳውያንና ኑሯቸው
በአለም ላይ የአይሁዳውያንን ያክል የተሰቃየ ህዝብ የለም ። ይሁን እንጂ አይሁዳውያን ብዙ ስቃይን ግፍን በማየታቸው ብዙ ትምህርት አግኝተዋል ።

የፖለቲካ ሳይንስ
ማን ይምራ ? ሲባል እንደ ጥንታዊ ግሪክ ታላላቅ ፈላስፎች አባባል አገርን መምራት የሚችለው ፣የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ፣ በልምድና በተሞክሮ የዳበሩ ሰዎች ናቸው አገርን ምመራት ያለባቸው ነው እሚሉት ጥንታዊ ግሪኮች ። ይህ ብቻ እንደ ጥንታዊ ግሪኮች አባባል ጥሩ መሪ ማለት መምራትን ብቻ ሳይሆን መመራትንም እሚያውቅ መሆን ይኖርበታል ይላሉ ። ይህም ማለት ሁልግዜም ብቸኛ መሪ ያልሆነ ፣ ባጠገቡ ካሉ ሰዎች ጋር የሚማከር ፣ የሌሎች ሰዎችን ሀሳብ እሚያዳምጥ ማለት ነው ። ይህ ህዝቡንም ይጨምራል ፣ ህዝቡን ፍላጎት ፣ ስሜትን መከተልም ሲኖርበት ፣ህዝቡ እማይፈልጋቸውን ወይም እማይስማማባቸውን ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት የህዝቡን ፍላጎትን ጭምር ለመጠበቅ ፈቃደኝነትን ማሳየት አለበት የሚል አስተሳሰብ አላቸው ።

ከጥንት ግሪካውያን ወዲህ በመካከለኛው ዘመን የነበረው የስዩመ – እግዝአብሄር የዘውዳዊ ስርአቶች በተለያዩ የአለም ክፍሎች የነበሩበት ሲሆን ። አንድ ፈላስፋ እንደገለፀው ስዩመ – እግዝአብሄር ማለት የእግዝአብሄርን ህግጋትንና ትእዛዛቱን በመፅሀፉ ውስጥ የተደነገጉትን ነገሮች በሙሉ ስዩመ – እግዝአብሄር መንግስት መከተል አለበት ። እዚህ ጋ ስዩመ – እግዝአብሄር ለማሳሳቻውም ተግባራዊ ሳያደርግ ለማስመሰል ሳይሆን ህግጋቱንናና ደንቦቹን ከልቡ የተቀበለ መሆን አለበት።

ስዩመ – እግዝአብሄር ንጉስ ትልቅ ሀላፊነትን የተሸከመ እንደመሆኑ ትልቅ የሞራል ወይም የስነ – ምግባር ሸክም አለበት ። ሲነግስ ቤተሰቡ ከሰጠው ስም በተጨማሪ የንግስና ስምን ይሰጠዋል ። አሁን ሲነግሱ ስዩመ – እግዝአብሄር ስለሆነ ከሰው የተለየና ከሰዎች የበለጠ ፍርድንና ፍትህን መስጠት አለበት ።

ወደ ዘመናዊ የመንግስት ስርአቶች ብንሄድ ስዩመ – ህዝብ ነው ። ይህም ፓርላማዊ ወይም ሪፐብሊክ ይሆናል ። ዲሞክራሲ የሚለው ቃል ዲሞክራቲያ ከተባለው ቃል የመጣ ሲሆን ዲሞክራሲ ከመልካም አስተዳደር የሰፋ ፅንሰ – ሀሳብ ነው ። መልካም አስተዳደር አንዱ የዲሞክራሲ መሰረት ነው ። መልካም አስተዳደር የአንድ ተቋም በትክክል መተዳደር ፣ ትክክለኛ አስተዳደር መኖር ማለት ነው ። ዲሞክራሲ ከመልካም አስተዳደር ሰፋ ያለ ፅንሰ – ሀሳብ ሲሆን የዲሞክራሲም አንድ አካል ነው ።

በህዳሴው ዘመን (ሬነሳንስ) በአውሮፓ ከተፈጠሩ ፈላስፎች መሐከል ማክያቬሊ ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስን መደላድል ፈጠረ ሰው ሲሆን ። እርሱም አዲስ የፖለቲካ አህጉርን ፈጠርኩ ነው እሚለው። ይሁን እንጂ የእርሱ ስራ ባለፉት 300 እና 400 በተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጓሜ ሲሰጠው ኖሯል ። በዚህም ማክያቬሊዝም የሚባል የፍልስፍናና የአስተሳሰብ ዘውግ የተፈጠረ ሲሆን አልፎ አልፎም እርሱ ከራሱ አስተምህሮዎች የተለዩ ሀሳቦችንም ያያዘ ነው ።

ወደ ዋናው ሀሳብ ስንመጣ የራሱን አዲስ ሀሳብ ሲያዘጋጅ በፕሌቶና በአሪስቶትል ፍልስፍናዎች ላይ የተመሰረቱትን የቀደምት ግሪኮችን እንዲሁም በክርስትና ሀይማኖት ላይ የተመሰረተውን የመካከለኛውን ዘመን ፍልስፍናን በመተቸት ነው እሚነሳው ። እንደ እርሱ አስተሳሰብ ፈላስፋዎች የሰውን ልጅ ከጨለማ ወደ ብርሀን ለማውጣት ይፈልጋሉ ። ለምሳሌ የፕሌቶ የዋሻው ተምሳሌት ሀሳቡ የሰውን ልጅ ከጨለማው ዋሻ ወደ ብርሀኑ የማውጣት እና ብርሀነ – ህሊናን (enlightenment) እንዲቀዳጅ የማድረግ አለማ ያለው ነው ። ይሁን እንጂ እንደ ማክያቬሊ አስተሳሰብ ደግሞ ወደ ብርሀኑ እምመራችሁ መሲህ ሳይሆን እንዴት የሰው ልጅ በዚህ ጨለማ በሆነ አለም ህልውናችሁን እንደምታስጠብቁ ፣ እና ይህንን የጨለማ አለም እንደምትቋቋሙት አሳያችኋለሁ ነው እሚለው ።

ካበረከታቸው ሀሳቦች መሀከል ስነ – ምግባርን ወይም ሞራልን በተመለከተ ቀድሞ በነበረው በሀይማኖት ላይ ተመስርቶ በነበረው አስተሳሰብ ላይ ያቀረበው ትችት ነው ። እንደ ማክያቬሊ አባባል ሁለት አይነት ስነ – ምግባሮች ወይም ሞራሎች ሲኖሩ አንደኛው በህዝብ ፊት የሚደረግ ስነ – ምግባር ሲሆን ይህም ፖለቲካዊ ስነ – ምግባርን ይጨምራል ። ሁለተኛው አይነት ስነ – ምግባር ደግሞ ግለሰባዊ የሆነ ስነ – ምግባር ሲሆን ፤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ እሚመራው እሚዳኘው በፐብሊክ ሞራሊቲ ነው እንጂ በግለሰብ ሞራሊቲ አይደለም ።መሪው የሚጠየቅብበት ሞራሊቲና ግለሰብ የሚጠየቅበት ሞራላቲ ይለያያል ።

ሌላው ደግሞ ያለው የልሂቅ (elite) የሚባለው ህብረተሰብ ክፍል አስተሳሰብ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ህብረተሰብ እየሰረፀ በሄደ ቁጥር ያ መንግስት ሊናወጥ ወይም ሊፈራርስ ይችላል ። የዛን ሀሳብ ትክክለኛነት እየተረዳ በሚመጣው ተራው ህብረተሰብ ያ ሀሳብ ቦታን እያገኘ የበለጠ ጉልበት እየጨመረ ይሄዳል ። ይሄድና የዛ መንግስት ወይም ስርአት አደጋ ውስጥ ይወድቃል ። እንደሚታወቀው የትኛውም የፖለቲካ ስርአት ውድሎ አድሮ በልሂቃን ቁጥጥር ስር መውደቁ አይቀሬ ነው – ኮሚኒዝምም ይሁን ሊበራል ዲሞክራሲ ዞሮ ዞሮ በመሪነትና በገዢነት ወንበር ላይ የሚቀመጡት ያው ልሂቃኑ ናቸው ።

የጥንቶቹ ግሪካውያን ፍልስፍና የሰው ልጅ ሄዶ ሄዶ የፖለቲካ ፀጋን (political virtue) ደረጃ ላይ ማድረስ ነው አላማው ወይም የመጨረሻው ግቡ ። በጥንት ግሪክ አባባል (man is a political animal) እናም ደስታውን ኑሮውን ሁሉንም ነገር እሚፈልገውም እሚያገኘውም (city state) ውስጥ ነው ። በነገራችን ላይ ይህ አስተሳሰብ ከምስራቃውያን የመንፈሳዊ እውቀት ጋራ በእጅጉ ይለያያል ። በምስራቃውያን አንድ ሰው ራሱን ማንቃት በእውቀት መንጋቃት ደረጃ መድረስ ነው ዋናው አላማው መሆን ያለበት ። ቡድሂዝምን ብንወስድ ንቃት ከመንግስት ህልውና ጋር ምንም እሚያገናኘው ነገር የለም ።

በነገራችን ላይ የጥንቱን የግሪካውያንን ፍልስፍና በተለይም የፕሌቶን ፍልስፍና ከክርስትና ሀይማኖት ጋር ማስማማት ቀላል የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ የመጣውን የአሪስቲቶትልም ፍልስፍና ግን ከብዙ ጊዜያት በኋላ ነው ከክርስትና ሀይማኖት ጋራ ያስማሙት ። እሱ የሚለው እማይሆን አይነት ። (ideal) ላይ ትፈጥራላችሁ ሰውን በጎ (virtuous) ለማድረግ ትጥራላችሁ ነገር ግን ሰው ምን አይነት አስቸጋሪ እንደሆነ አልተረዳችሁም ፣ ሰው በትምህርት እና በምክር ብቻ ጥሩ አይሆንም የሀይል ዱላ ያስፈልጋል ነው እሚለው ።

ከዚህም በተጨማሪ ይህም (morality) ከ (immorality) ይመነጫል ፣ ፍትህም (Justice) ከኢ – ፍትሀዊነት (injustice) ይመነጫል ። አገር እሚመሰረተው ከወንጀል ነው ። ትልቅ ስልጣኔ የሚመሰረተው ትልቅ ወንጀል ተሰርቶ ነው ፣ በቀላሉ አይገኝም ፣ አልጋ ባልጋ አይሆንም የሚል ነው ።

ሱን ሱ የተባለው ጥንታዊ የቻይና ፈላስፋ «የሰዎች ክፋት የሚወገደው በትምህርት ነው» ይላል ። በምእራቡ አለም ታዋቂ አርቲስቶች በአንድ በኩል በንግድ በቢዝነስ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ስራዎችን ነው እሚሰሩት ። ይህም በአንድ በኩል ለረጅም ጊዜ የሚቆይ (Timeless) የሆነ ስራን እሚሰሩ አርቲስቶች ረጅም ጊዜ የሚቆይን ስራን ሊሰሩ እድል ያገኛሉ ። ነገር ግን ለንግድ ወይም ለገቢ ብቻ ብለው ስራን እሚሰሩ ግን ስራቸው የአንድ ሰሞን ብቻ ሆኖ ይቀራል ።

የማስታወቂያ ስታዎችን ብንወስድ በእኛ ሀገር በአርቲስቶች የሚሰራ ሲሆን በሌላው አለም ግን በሰለጠኑ የገበያ ባለሙያዎች ነው እሚሰራው ።
አራቱ እውቀት እሚሰበሰብባቸው መንገዶች ምልከታ (Observation) ፣ ነገሮችን የማየትና የመረዳት ችሎታ፣ የማሰብ ችሎታ ፣ እርግጥ የማስታወስ ችሎታ በላይ የማሰብ ችሎታ የበለጠ ነው ። ማንም ሰው ሊያስታውስ ቢችልም ያንን ነገር በተለየ መንገድ የማሰብ ችሎታ ግን የተለመደ አይደለም ። በአለም ላይ የምናያቸው በርካታ ታላላቅ ነገሮች የተፈጠሩት የማሰብ ችሎታ ባላቸው ሰዎች ሲሆን ። የማስታወስ ችሎታ፣ ትምህርትና ብዙ ማንበብ ፣ ሲሆኑ እነኚህ ሁሉ ነገሮች ቢኖሩም ለአንድ ሰው ስኬታማ እንዲሆን ትጋት (ዲሲፕሊን) መሰረት ነው ።

መንፈስ

መንፈስን በተመለከተ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ጳውሎስ እጅግ ብዙ ፅፏል ፤ «በመንፈስ ያለ ሰው ሌሎችን ይመረምራል እንጂ ሌሎች እርሱን አይመረምሩትም» ይላል ። እያንዳንዱ ሰው አንድ አይነት መንገስፈስን ይወክላል ። ሁላችንም አንድ አይነት መንገሰ ፈስን ይዘን የየተወከድን ሲሆን ፣ ስቴንሰር የተባለው የረቂቅ መንፈሳዊ ሊቅ እንደሚለው «ማንኛውም መንፈስ መጥፎ የለውም » ይላል ። መጥፎ ወይም ጥሩ ከመሆን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ። መንፈስ በራሱ መጥፎም ፣ ጥሩም አይደለም – በሚይዘው ሰውና ለሚጠቀምበት አላማ ነው የመንፈስ አካሄድ የሚገለጠው ።
ለምሳሌ የክርስትና ሀይማኖትን ብንወስድ ሰይጣን ከሌሎች መላእክት የበለጠ ስልጣንና እው ቀት የነበረው መልአክ እንደነበረ ነገር ግን የተሰጠውን ስልጣን በፈጠረው በእግዝአብሄር ላይ በመቅናትና ለክፋት ስላዋለው ከሰማይ ቤት እንደተባረረ በክርስትና ሀይማኖት ሊቃውንት ይገለፃል ። ይህም ትልቅ ስልጣንና እውቀትን የያዙ ፣ ነገር ግን የተሰጣቸውን መንፈስ ለክፋት እና አለአግባብ የተጠቀሙ ግን ከስልጣኑ ወንበር እንደሚወድቁ የሚያሳውቅ ነው ።
በነገራችን ላይ ከማንኛውም ምድራዊ የፖለቲካ ስልጣን ወይም ሀብት በበለጠ የመንፈስ ስልጣን እጅግ የላቀ ነው ። በሠው ልጅ ታሪክ የተፈጠሩ ታላላቅ የጥበብ ስራዎች ፣ ስእሎች ፣ ስነ-ፅሁፎች ፣ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ስራቸውን ያከናወኑት በመንፈስ እየተመሩ መሆኑ ይታወቃል ። በእውቀቱ ስዩም መግባትና መውጣት በተሰኘው መፅሀፉ መግቢያ ላይ ይህንን እውነት ከትቦት እናገኘዋለን ።

ረቂቅ መንፈሳዊነት «mysticism»

በመሀከላችን የረቂቅ መንፈሳዊ እውቀት ባለቤቶች ይገኛሉ ። ረቂቅ መንፈሳዊነት ወይም «ሚስቲዝም» ይባላል ። ይህ እውቀት ጥቂቶች ይዘውት የሚወለዱት ለብዙሀኑ ህብረተሰብ ግን ስውር ነው ። የመንፈስ ሚስጥራት ለረቂቅ መንፈሳውያን ግልጥ ሲሆኑ ፣ ይህ እውቀት ጥቂቶች ይዘውት የሚወለ ዱት ለብዙሀኑ ህብረተሰብ ግን ስውር ነው ። የመንፈስ ሚስጥራት ለረቂቅ መንፈሳውያን ገሀድ ሲሆን ፣ ስለ ረቂቅ መንፈሳዊነት ምንም ለማያውቅ ሰው ግን እንግዳ ነው ። ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ እናንተ በመንፈስ ህፃናት ናችሁ ይላል ። ቡድሀ በበኩሉ በርካታ «የተጨናነቁ ነፍሳትን » መመልከቱን ይናገራ ል ።

የወንዶች ዓለም ክፍል -2
በብዙ እንሰሳት ውስጥ የወንዱ ቦታ ጎላ ሊል ይችላል ። በአንበሳ ብንመለከት ዋናውን አደን የምታከናውነው ሴቷ አንበሳ ስትሆን ፣ በአንፃሩ ወንዱ አንበሳ ብዙውን ጊዜ አያድንም ። ሴቷ አንባሳ የሚያስቸግር ነገር ሲመጣ ካልሆነ በስተቀር ወንዱ ብዙም በአደን አይሳተፍም ። ይሁን እንጂ አንድ አነስተኛ የአንበሳ መንጋ የሚመራውም ሆነ ጥበቃ የሚደረግለት በወንዱ አንበሳ አማካይነት ነው ። ይሁን እንጂ ይህ በአንበሶች ዘንድ «የፖለቲካ» ችግር የለም ።

እኛና ስሜቶቻችን
ዋና ዋና የሚባሉት ስሜቶች በአንዳንድ ሰዎች ለምሳሌ ዎለሽ እንደሚለው የሰው ልጅ ዋና ዋና ስሜት የሚባሉት ፍርሀትና ፍቅር ሲሆኑ ፣ ደግሞ ዋና ዋና የሚባሉት የሰው ልጅ ስሜቶች ሶስት ናቸው እነሱም ናቸው ።

ሶስቱ ጠንካራ ስሜቶች በመባል በዶ/ር ሄለን ፊቨር በተሰኙ የሰው ዘር አጥኚ ወይም አንትሮፖሎጂስት የተገለፁት ጠንካራ የጉጉትና አንድን ነገር የመሻት ወይም ጥማት ስሜት «lust» ፣ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የመነቃቃት ስሜት «infatuation» እና በፍቅር የመጣመር ስሜት «attachment » ናቸው ። እንደ ዶክተሯ ገለፃ እያንዳንዱ ጥልቅ ስሜት በአእምሮ ውስጥ የራሱ የሆነ ባዮ ኬሚስትሪ እንቅስቃሴ አለው ። ይሄውም ግለሰቡ ከአንድ ሰው ጋር በሚጣመርበት ጊዜ አእምሮውን የማንቃትና የማብራት ሚናውን ይወጣል የሚል አመለካከት አላቸው ።

ክርስቶስና ቡድሀ
ቡድሀ የዚህ ምድር ሲሆን ፣ በአንፃሩ ግን እየሱስ ክርስቶስ ግን የዚህ ምድር አይደለም ። ከዚህ ምድር የመጣ አይደለም ። ዮሀንስ «የጫማውን ክር መፍታት የማይገባኝ ይመጣል» ብሎ ተናግሮለታል ። በርካታ ነቢያት ስለ እየሱስ ክርስቶሰ ወደ ዚህች ምድር ከመምጣቱ በፊት እጅግ ብዙ ብዙ ብለዋል ። በአንፃሩ ቡድሀ ሰው ሲሆን ከአንድ የንጉስ ቤተሰበነብ የተወለከሰ ለንግስተና የተቀባና የአባቱን ዙፋን ለመውረስ ይዘጋጅ የነበረ ልኡል ነው ። ቡድሀ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የአስተሳሰብና የአውቀት ደረጃ ከደረሱ ጥቂት ሰዎች አንዱ ነው ።

እውቀትና ስልጣን
ታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ፕሌቶ «ፈላስፎች መምራት አለባቸው » ሲል እውቀት ስልጣንን ሊጨብጥ ይገባል ከሚል አስተሳሰብ ነው ። ስልጣን በእውቀት ስር መዋል አለበት እንጂ ፣ ስልጣን ከእውቀት ማፈንገጥ የለበትም ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው ። ብዙውን ጊዜ በአለም ላይ እውቀት ሳይኖር ስልጣንን መጨበጥ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ ነው ። ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ያሉ ፣ በአመፅ ከፍተኛውን የእውቀትን ደረጃ በሚጨብጡበት ወቅት በርካታ ጥፋቶችን በተለያዩ አገራት ላይ እንዳደረሱ በታሪክ የተመዘገበ ነው ። ብዙውን በዘላቂ እውቀት ላይ ያልተመሰረተ ስልጣን ዘላቂ የማይሆን ሲሆን ፣ መምራት ራሱን የቻለ እውቀትን የሚጠይቅ ሲሆን ፣ ስልጣን ዘለቄታ አይኖረውም ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s