Justice

ፍትህና እውነት
እየሱስ ክርስቶስ ከሳሾቹ ጲላጦስ ፊት ባቀረቡት ወቅት ከጲላጦስ ጋር እንካ ሰላንታ በገጠመበት ወቅት ጲላጦስን «እውነት ምንድነች?» ብሎ ይጠይዋል ፣ በተመሳሳይም ታላቁ ፈላስፋ ሶቅራጥስ ተማሪዎቹን «ፍትህ ምንድን ነው?» ብሎ ይጠይቃቸዋል ። የእውነትና የፍትህ ጥያቄ በታሪክ ውስጥ በተደጋጋሚ የተከሰተና ቁልጭ ያለ መልስ ያላገኘ ነው ።
ንግድ ፍትህን ያሰፍናል ብለን ብናስብ ፣ አን ራንድ እንደምትለው «በሰዎች መሐከል በጣም ፍትሀዊ የሆነው ግንኙነት ንግድ ነው» ትላለች ። ንግድ የራሱ ስርአት ያለው ሲሆን ፣ በአለም የንግድ ስርአት ውስጥ የአለም የንገድ ስርአት ፍትሀዊ አለመሆኑ የተገለፀ ጉዳይ ስለሆነ ምንም እንኳን ሁለት ሐገራት ቢነግዱም ያ የንግዳቸው ስርአት ፍትሀዊ ነው ማለት አይቻልም ። ንግድ የራሱ ስርአት ፣ ደንብና አካሄድ ያለው ነገር ሲሆን ንግዱ በምን መንገድ መካሄድ እንዳለበት የሚወስነው አካል በንግዱ ሂደት ውስጥ የበላይነቱን ለራሱ ማስፈን ይችላል ። ስለዚህ በአንድ ደሀ ፣ በግብርና የሚተዳደር አገርና አንድ በኢንዱስትሪ የበለፀገ አገር እኩል እና ፍትሀዊ የሆነ የንገድ ስርአት በመሀከላቸው መኖረ መፈጠር መቻሉ እጅግ አጠራጣሪ ነው ።
ለምሳሌ አንድ ሀብታምና አንድ ደሀ እርስ በእርሳቸው ቢነግዱ ሀብታሙ ለደሀው ጉልበቱን ቢገዛው ፣ ደሀው ጉልበቱን ለመሸጥ አማራጭ ስለሌለው ለሀብታሙ በሰጠው ዋጋ የመሸጥ ግዴታ ሊኖርበት ይችላል ። በአንፃሩ ሀብታሙ አማራጭ ስላለው በገንዘቡ የፈለገውን የማሰራት አማራጭ አለው ። ደሀው አማራጩ ጠባብ ስለሚሆን ያለው አማራጭ ሀብታሙ በሰጠው ዋጋ ጉልበቱን መሸጥ ሊሆን ይችላል ።
በአለም ላይም እንዲሁ በሀብታም በኢንዱስትሪ በበለፀጉና በደሀ ሀገራት መሀከል የሚደረግ የንግድ ግንኙነት ፍትሀዊ አለመሆኑ የታወቀ ነው ። አንድ በኢንዱስትሪዎቹ አማካይነት ያለማቋረጥ ሰራተኞችን እየቀያየረ በፋብሪካዎቹ ማምረት የሚችል ሀገርና ፣ አንድ በግብርና የሚተዳደር ሀገር እኩል ሊነግዱ አይችሉም ።

ስልጣኔ የት ተጀመረ ?
ይህ ጥያቄ ለበርካታ መቶ አመታት እጅግ አወዛጋቢ ሆኖ የቆየ ሲሆን ከአውሮፓ የህዳሴው ዘመን በኋላ ግን አውሮፓዉያን በማያሻማ ሁኔታ የስልጣኔ የበላይነቱን ጨብጠው ቆይተዋል። አውሮፓውያን ፀሀፊዎች በተልም በህዳሴው ዘመን የነበሩ እና ከዚያ በኋላ የተፈጠሩ የስልጣኔ ምንጭ አድርገው የሚቆጥሩት አውሮፓን ሲሆን የተቀረውን አለም ማለትም አፍሪካን ፣ እስያንና የአሜሪካ አህጉርን ያልሰለጠነ ወይንም ኋላ ቀር አድርገው ሲቆጥሩት ኖረዋል ። ይህ ጥያቄ የመጀመሪያውን ሀሳቦችን ያመነጨው ማነው ? የመጀመሪያውን እውቀት ያወቀው ማነው ወይንም እነማን ናቸው የሚለውን የሚመልስ ሲሆን ።
አትላንቲስ
የጥንት ግብፃውያን እጅግ የላቀ የእውቀት ደረጃ ላይ ደርሰው የነረበሩ ህዝቦች እንደመሆናቸው ሐሳናባዊ የሆነች አትላንቲስ ስልጣኔን ነገር ለፕሌቶ አሳይተውት ነበረ ። ፕሌቶም ይህችን ስልጣኔ አትላንቲስ በሚል ስያሜ በርካታ ድርሳናትን ፅፎላታል ። አትላንቲስ ስልጣኔዋ በገንዘብና በጥቅም ያልተበረዘ ፣ በስልጣን ወድድር ያልተከፋፈለና ለእርስ በእርስ ጦርነት ያልተጋለጠ ነበረ ። ውሎ አድሮ ግን የሰዎች ባህሪ መበላሸት ሲጀምርና ሰዎች ስልጣንን ፣ የበዛ ገንዘብንና ዝናንና ገናናነትን ሲሹ ስልጣኔዋ እንዴት አንደወደቀ ያትታል ። በዚህ ወቅትም ተፈጥሮም ጭምር ተቃራኒ ሆኖ ተነስቶባት በውጪ ወራሪዎች በተወረረችበት ወቅት ከመሬቷ ስር የተነሳው እሳተ ገሞራ ፣ መሬት መንቀጥቀጥና ሱናሚ ከምድረ- ገፅ ለአንዴና መጨረሻ ጊዜ እንዳጠፋት እና ውቅያኖስ ውስጥ እንደቀበራት ዘግቧል ።
ይሁን እንጂ አትላንቲስ እ.ኤ.አ በ 2013 ዓ.ም. ከብራዚል በሪዮ ዴ ጂነሮ በ90 ማይል ርቀት ላይ በሳይንቲስቶች ልትገኝ በቅታለች ። ይህችው በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ተቀብራ የተገኘችው ከተማ ።
ስልጣኔ ምንድነው ?
ስለ ስልጣኔ ምንነት የተለያዩ ፍቺዎችና ብያኔዎች ይሰጣሉ ። አንዳንዶች ስልጣኔ ማለት ስነ- ምግባር ፣ ባህልና ሀይማኖት ማለት ነው ሲሉ ። በሌላ በኩል ደግሞ ስልጣኔ ቁሳዊ ሀብትን ከመፍጠር ጋር የሚያያይዙት አሉ ። በአጭሩ ግን ስልጣኔ ቁሳዊ ሀብትን መፍጠር እንዳለ ሆኖ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ግብረ-ገብነት ፣ መንፈሳዊነት እና ሀይማኖትንም እንዲሁ የማንኛውም ስልጣኔ አካል ናቸው ።
አንድ ስልጣኔ በአንዱ ዘርፍ ብቻ እምርታን አሳይቶ ነገር ግን በሌላው ምንም እድገት ከሌለው ህልውናው ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው ። ለምሳሌ በመንፈሳዊ እውቀቱ የላቀ ሆኖ ነገር ግን ምንም ቁሳዊ ሀብትና ፣ ቁሳዊ ሀብትን ለመፍጠር የሚያስፈልገው የሳይንስና የቴክኖሎጂ እውቀት ከሌለው ፤ በተቃራኒውም መንፈሳዊ እና ሀይማኖታዊ ሆኖ ነገር ግን ምንም አይነት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ምንም የላቀ ሀብትን ቢፈጥር ፣ እንዲሁም ጨረቃንና ማርስን ቢረግጥ መንፈሳዊ እውቀት ከሌለው ፍትሀዊና ሞራላዊ ስልጣኔ መሆን ስለማይችል የስነ- ምግባር መላሸቅ ውስጡን ይቦረቡረዋል ።
ለምሳሌ ስፓርታንና አቴናን ብንወስድ ፣ እነኚህ ሁለት የጥንታዊ ጎረቤት ስልጣኔዎች ለረጅም አመታት የቆየ የእርስ በእርስ ፉክክር በመሀከላቸው የነበረ ሲሆን ከተራዘመ ጦርነት በኋላ በወታደራዊ አቋማቸው የላቁት ስፓርታውያን ጦርነቱን በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል ። አቴንም በስፓርታውያን አገዛዝ ስር ልትወድቅ በቅታለች ። ስፓርታውያን በስነ-ጥበብ፣ በፍልስፍና ፣ በቲአትር ፣ በንግድ በመሳሰሉት ጥበባት የላቀ እውቀት የነበራቸውን አቴናውያንን ማስተዳደር ቀላል ስራ አልነበረም በየብስ በተከበበ ምድር ላይ ለብቻቸው ወታደራዊ አቅማቸውን ብቻ በመገንባት ለኖሩት ከዚያ ውጪ ይህ ነው የሚባል ተሞክሮ ፣ ልምድና እውቀት አልነበራቸውም – ለስፓርታውያን ። በሶስት አስርት አመታት በኋላ በዋናው ስፓርታ የነበሩት ነገስታት በአቴን ግዛታቸው የሚያዩት ነገር ጤና የሚሰጣቸው አልነበረም ። ስፓርታውያን በአቴን አስተዳደራቸው በሙስና መዘፈቅና አስተዳደሬ በመላሸት ጀመረ ፤ ከጥቂት አመታት በኋላም ስፓርታውያን ዋና በተባለ ጦርነት ተሸነፉና ፍፃሜአቸው ሊሆን በቃ ። ለስፓርታውያን መውደቅ ምክንያት የሆነው ስፓርታውያን ትኩረታቸውን ወታደርን በመገንባት ብቻ በማድረጋቸው ስለ ንግድ ፣ ስለ ፍልስፍና ስለመሳሰሉት ረቂቅ ጥበቦች ምንም የሚያውቁት ነገር አለመኖሩ ውሎ አድሮ ከእነሱ የላቀ ጥበብ የነበራቸውን ህዝቦችን ለማስተዳደር ልምዱም ሆነ እውቀቱ ስላልነበራቸው አገዛዛቸው ሊወድቅ በቅቷል ።
እስራኤሎችን ብንወሰድ ፣ xesera
ቲቤቶችን ብንወሰድ
የስልጣኔዎች አወዳደቅና አነሳስ
የስልጣኔዎች መንፈስ
ያላቸው የስልጣኔ መንፈስ ይሸሻቸዋል ። ይህም ውድቀትን ያመጣል ። ማንኛውም ስልጣኔ የራሱ መንፈስ ያለው ሲሆን
ስልጣኔና አብዮት
አትላንቲስ
አሜሪካ እንደ ሮማ ኢምፓየር ?
ጦርነትና ስልጣኔ
የተፈጥሮ አደጋዎችና ስልጣኔ
ፊልማንሶሪ የተሰኘችው በካሪቢያን የምትገኝ ደሴት በእሳተ ገሞራ የወደመች ሲሆን በ 1902 ወድማለች ።
ቦብ ማርሌ
ምእራባውያን ከሶስተኛው ዓለም ተፈጥረዋል ብለው ከሚያምኗቸው ጥቂት ታላላቅ ሰዎች አንዱ ቦብ ማርሌ ነው ። በርካታ ዘፈኖቹም የቦብ ማርሊን ስለ አለም የነበረውን እውቀትና ግንዛቤን የሚያሳዩ ናቸው ።

Natural Mystique it if you listen carefully, it is in the air.
ስፖርት
ስፖርት እጅግ የበዛ ገንዘብ የሚንቀሳቀስበትና ለህብረሰቡንም አደንዛዥ የሆነ ነገር ነው ። ማስታወቂያን የሚሰሩት እንደ AIG እና Berclays ያሉት ለማስታወቂያ የበዛ ገንዘብን የሚያወጡ ሲሆን ለእንግሊዝ የቱሪስት መስህብ መፍጠሪያና ከፍተኛ የገቢ ምንጫቸው ነው ።
ሐዲስ አለማየሁ ወንጀለኛው ዳኛ በተሰኘው መፅሀፋቸው ውስጥ «የህዝብ ድምፅ ፣ የእግዝአብሄር ድምፅ ነው » ይላሉ ።
እየሱስ ክርስቶስ አንድ ደቀ መዝሙሩ አባቴ ሞቶብኛል ልቅበረው ሲል «ሙታንን ሙታን ይቅበሯቸው» የሚል ምላሽ ነበረ የሰጠው ።
ፍቅርና ወሲብ
ህሊናዊ ንቃት እና አእምሮ
ህሊናዊ ንቃት ደረጃ መድረስ የሚቻለው አእምሮን ማለፍ ሲችል ብቻ ነው ። ዓለምን የሚመራው አእምሮ ሲሆን ፣ የሳይንስ ፣ የቴክኖሎጂ እውቀቶች እያደጉ ሲሄዱ በአንፃሩ ደግሞ የሰው ልጅ ህሊናዊ ንቃት ግን ልክ እንደ እውቀት የሚያድግ አይደለም ። ከዚያ ይልቅ ግን ማንኛውም ሰው የራሱን ህሊናዊ ንቃት በራሱ መንገድ መሳደግና ኮትኩቶ ማሳደግ አለበት ። ማንኛውም ሰው በራሱ መንገድ ህሊናዊ እውቀቱን ማሳደግና ከፍተኛው ሰረ ደረጃ ላይ መድረስ የሚችለው በራሴ መንገድ ነው ።
እውቀት ግን በየትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ነገር ሲሆን ፣ እጅግ የተራቀቁ የሚባሉ እውቀቶች ሳይቀሩ በማስተማር ፣ በማንበብ ወደ ሌሎች ሊረዷቸው ወደ ሚችሏቸው ሰዎች በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ ።

ታላቁ መፅሀፍ
በዓለም ላይ ከተፃፉ ታላላቅ መፅሀፍት መፅሀፍ ቅዱስ ተወዳዳሪ የለውም ። መፅሀፍ ቅዱስ ህሊናዊ-ንቃት ደረጃ ው እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ፣ ማንም በቀላሉ በሚረዳው እንዲሁም እጅግ የረቀቁ እና ለመረዳት እጅግ ውስብስብ ሐሳቦችን አ ጣምሮ የያዘ ነው ።
መፅሀፍ ቅዱስ የሚጀምረው ከአዳም ሲሆን ፣ አዳም ተምሳሌታዊ ነው ። አዳም ራሱ የሰው ልጅ ነው ። የሰው ልጅ የገባበትንና የሚጠብቀውን ኑሮ የሚያሳይ ነው ። ለምሳሌ አዳም «በላብህና በወዝህ፣ እንጀራን ትበላለህ» የተባለው የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ የሚጠብቀውንና የሚኖረውን ኑሮ የሚያሳይ ነው ።
«ለፍጥረታዊው ሰው የእግዝአብሄር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም ፣ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም ። መንፈሳዊው ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ፣ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም » ቆሮ 2፣14
ቀጥሎም ጳውሎስ «የስጋ እንመሆናችሁ በከርስቶስም ህፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም ። ገና ፅኑ መብል መብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ ፣ ገና ስጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁም ? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱም ? » ቆሮ ምእራፍ ።፣3፡1-4
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አምላክነቱን እንኳን ትተን እንደ ሰው እንኳን ቢታይ እየሱስ ክርስቶስን እሚወዳደር የለም ። በአሁኑ ወቅት ምእራባውያን ፀሀፍት የእየሱስ ክርስቶስን ስብእናና ማንነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባትና ማቃለል ጀምረዋል ። አይሁዳውያን አሁንም ድረስ ለእየሱስ ክርስቶስ ይቅርታን እንዳላደረጉለት ይታወቃል ።
እስራኤል እና አረቦች
«ጨዋታ ቀያሪ» ያሏቸውን የጦር መሳሪያዎችን በአረቦች እጅ መግባቱን ኢሁድ ኦልመርት የተባሉ የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ገልፀውታል ። የባሽር አሳድ መንግስት እየተዳከመ በሄደበት ወቅት ያሉትን ሚሳይሎችንና ምናልባትም የኬሚካል የጦር መሳሪያዎቹን ለሂዝቦላ ለማቀበል ደርሸበታለሁ ያለችው እስራኤል ከሶሪያ ወደ ሊባኖስ ሊላኩ የነበሩትን ተጓዥ መኪኖችን ሶርያ ውስጥ ገብታ በተደጋጋሚ በአየር በመደብደብ ለሂዝቦላ እንዳይደርስ ማድረግ ችያለሁ ብላለች ። ይህ ብቻም ሳይሆን እስራኤል በጦርነት እየተዳከመ የነበረውን የአሳድን መንግስት ሶርያ ውስጥ በመግባት የጦር መሳሪያ ማከማቻ ናቸው ያለቻቸውን የጦር መጋዘነኖችን በተደጋጋሚ በአውሮፕላን ደብድባለች ።
አሜሪካኖች በበኩላቸው በበሽር አል-አሳድ የሚመራው የሶሪያ መንግስት የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተጠቅማች የሚል ማስረጃን አግኝተናል በማለት ወታደራዊ እርምጃን በሶሪያ ላይ ለመውሰድ መዛታቸው አልቀረም ። በአንፃሩ ሩስያ አሜሪካ ሶርያ ላይ ወታደራዊ እርምጃን ለመውስድ እያጤነችበት ባለችበት ወቅት ፣ ለባሽር አል አሳድ መንግስት የጦር መሳሪያ ድጋፍን ያደርጉ ነበረ ።
ራስን ማወቅ
ራስንና ሌሎችን የመረዳት አስተውሎት

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s