ራስን ማወቅ

ራስን ማወቅ

ራስን ስለማወቅ ብዙ ብዙ ተብሏል ።  ለአንድ ሰው ህይወቱን በአግባብ ለመምራት  ራሱን ማወቅ ወሳኝ ነው ። ራስን   ማወቅ የህይወት ግብን ለማስቀመጥ ፣ የወደፊት የህይወት አቅጣጫን ለመምራት አስፈላጊ ነው ። ራሰን ማወቅ በጣም ቀላል ከሆኑ ነገሮች ይጀምራል ። ለምሳሌ የጤንነት ሁኔታን ማወቅ ፣ ከተለያዩ ህመሞች ተመርምሮ ራስን ማወቅ የመሳሰሉት ሁሉ ራሷን ስን የማወቂያ ቀላል መንገዶች ናቸው ። እነኚህ በሀኪም አማካይነት ፣ እና በላብራቶሪ ምርመራ በቀላሉ የሚታወቁ ሲሆን አንድ ሰው ስለ ራሱ ለማወቅ ከእነኚህ ሊጀምር ይችላል ።

ነገር ግን ራስን ማወቅ ከዚህ ያለፈ ሲሆን ራስን ማወቅ ማለት የራስን ፍላጎትን ፣ አስተሳሰብን ፣ አንድ ሰው ከሌሎች ሰዎች ጋር ሲቀላቀል በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያሳድረውን በጎም ይሁን አሉታዊ ተፅእኖ ሁሉ መረዳት ራስን ማወቅ ማለት ነው ። ለምሳሌ አንድ ሰው ስራ ተቀጥሮ የራሱ ባህሪ ፣ አስተሳሰብ፣ አለባበስም ፣ አነጋገር ወይም ስብእናውም ጭምር አወቀውም አላወቀውም በሌሎቸው ላይ አሉታዊም ፣ ሆነ አዎንታዊ ተፅእኖን ያስርፋል ። ሰውየው በሌሎች ሰዎች ላይ የፈጠረውን ተፅእኖ መረዳት ካልቻለ ፣ ችግር ቢገጥመው ለምን ያ ችገር ግር እንደገጠመው ሊገባው አይችልም ።

ራስን ማወቅ አንድ ሰው ልጅ ለህይወቱ ከሚሰጠው ትርጉም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው ። ራሱን በትክክል የሚያውቅ ሰው ለህይወቱ የሚሰጠውም ትርጉም ትክክለኛ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ለህይወቱ ትርጉምን ስላገኘ የሚሰራውን ስራ በትክክል ለመምረጥ ፣ በስራው ስኬታማ ለመሆን ያስችለዋል ። በዓለም ላይ በብዙ ዘርፎች እጅግ ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ራሳቸውን በአግባቡ ያወቁ ሰዎች ናቸው ። እነሱም እንኳን ራሳቸውን ጨርሰው እንዳላወቁ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰለማሉ ።     

የሀይማኖት መፋቀር

«አራዊት ከአንድ ወንዝ ይጠጣሉ» የተባሉት በአለም ላይ ያሉ የተለያዩ ሀይማኖቶች ናቸው ። በሀይማኖቶች መሐከል ስምምነት ደርሶ እርስ በእርስ መፋቀርና መወዳጀት ይከተላል ማለት ነው ።

የነፍስያ ሚስጥር

በሂንዱዎች እምነት የሰው ዘር መደቦች አራት ናቸው ። እነርሱም ብራህማን («ምርጥ የእግዝአብሄር ፍጥረት » የሚባሉት ) ፣ ሻትርያ (ጦረኛ ተዋጊ እና ለዚሁ ብቻ የተፈጠሩ) ፣ ቫዝያ (በግብርናና በከብት ርባታ የሚኖሩ ተራ ሰዎች ) እና ሲድራ ወይም አይነኬ (እንዲያገለግሉ ብቻ የተፈጠሩ) ናቸው ። የመጨረሻዎቹ የሰው አይነቶች መንካት ቀርቶ እነርሱ በተጠቀሙበት ዕቃ እንኳ መጠቀም እንደ ትልቅ ርኩሰት ይወሰዳል [1] ።    

መፅሀፍ ቅዱስም በበኩሉ «ካህን መሆን የሚችለው ሌዋዊ ብቻ ነው» ይላል ። ይህም ካህን የመሆን መብት ለሌዋዊ ብቻ የተሰጠ ሲሆን ለሌሎች የአይሁድ ጎሳዎች ግን አልተፈቀደም ማለት ነው ። የእየሱስ ክርስቶስ የዠር ሀረግም ከዳዊትና ከሰለሞን የሚመዘዝ ሲሆን ።

መፅሀፍ ቅዱስ ወደ ሮሜ ሰዎች  ምእራፍ 8 ፡ ቁጥር 28 ሁሌ ነገር ስለ ሰው ልጅ አስቀድሞ እንደታወቀ ይናገራል ። አስቀድሞ አወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ ወስኗል ።

 


[1] ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ ፣ ማህበረ ቅዱሳን ፣ 1997

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s