ኦከልት

ከማንኛውም እውቀት በስተጀርባ የተደበቀ ሚስጥር አለው ። ለምሳሌ ኒውተን በኦከልት እስከ ህይወቱ መጨረሻ ድረስ በዚህ ተለክፎ  እንደነበረ የታወቀ ነው ። ማንኛውም በአለም ላይ ያለ እውቀት ሳይንስ ፣ ፍልስፍና እና ሀይማኖትም ጭምር ከጀርባቸው ያለው የተመሰጠረው እውቀት ኦከልት ነው ። ነገር ግን ይፋዊ የሆነው እውቀት ለኦከልት እውቅና አይሰጠውም ።

አሊስተር ክራውሊ የተሰኘው እንግሊዛዊ በዚህ እውቀት እጅግ የረቀቀ ደረጃ ላይ ደርሶ የነበረ ነው ። እንዲሁም ኤሊፈስ ሌቪ የተሰኘው ፈረንሳዊም እንዲሁ በዚሁ በኦከልት እውቀት የነበረው ሰው ነበረ ። ለምሳሌ የማንኛውም ሀይማኖት ከጀርባው የራሱ የሆኑ አእማደ-ሚስጥራት ሲኖሩት እነኚህም ኦከልት ዘውግ የሚመደቡ ናቸው ። በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ ሆሊውድ እሚሰራቸው ፊልሞች በኦከልት ጥበብ ላይ የተመሰረቱ ናቸው ።

ስለ ሰው ልጅ የስልጣኔ ታሪክ በሳይንሳዊ ምርምር የተረጋገጠው የአስር ሺህ አመታት ብቻ ነው ። በስነ- ሰብ «አንትሮፖሎጂስቶች» ምርምር ሳይንስ የተቀበለው የሰው ልጅ በአጠቃላይ የግብፅ ፣ ቻይናም ይሁን የህንድ ፣ የአዝቴክሶችም ይሁን የማያዎች ስልጣኔ ከአስር ሺህ አመታት የተበለጠ ታሪክ የለውም የሚል ነው ። ነገር ግን የሠው ልጅ ስልጣኔ በርካታ አስር ሺዎች ብ ሎም የመቶ ሺህ ዎች አመታት ታሪክ ሊኖረው እንደሚችል መገመት ይቻላል ።

ኦከልት የሰው ልጅ በዘአዝጋሚ ለውጥ ተፈጠረ የሚለውን አስተሳሰብ አይቀበልም ። ለዚህም ምክንያቱ የመንፈስ ህልውና በጣም ረጅም መሆኑን በመረዳት ነው ።

«ልዩ ችሎታ ባላቸው ሰዎች ጥናት መሰረት እኛ የምንኖርበት አፅናፈዓለም አካል የተሰራው ከዘጠኝ ጊዜ ፍንዳታዎች በኋላ ነው የምንኖርበትም ፕላኔት ለብዙ ጊዜ ጠፍቶ ነበር ፕላኔቱ እንደገና በተሰራበት ጊዜ የሰው ልጅ እንደገና መባዛት ይጀምራል በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የነኛን የአሁን ጊዜ ስልጣኔም ከአስር ሺህ አመት በፍ ፊት በላይ እድሜ እንደሌለው ነው ሆኖም የአርኪዎሎጂ ግኝቶች እንደሚያመለክቱት በአውሮፓውያን አልፕስ ዋሻዎች ውስጥ 250 ሺህ አመት እድሜ በላይ ያላቸው የቀለም ስራዎች በጣም ከፍተኛ የስነጥበባዊነት የሚያሳዩ ሆነውናከዘመናዊው ሰው ችሎታዎች የበለጡ ነው ተገኝተዋል በፔሩ ብሄራዊ ዩንቨርስቲ ሙዚየም ውስጥም በትልቅ ድንጋይ ላይ የተቀረፀና ተቴሌስኮፕ ይዞ ክዋክብትን የሚያጤን የሰው ምስል እድሜ ከሰላሳ ሺህ አመት በላይ ነው ። እንደምናውቀው ጋሊሊዮ 30 × የሆነ የአስትሮኖሚያዊ ቴሌስኮፕ የፈለሰፈው ከሶስት መቶ አመታት በፊት ፣ በ1609 ዓ.ም . ነው ። ከሰላሳ ሺህ አመታት በፊት ቴሌስኮፕ እንዴት ሊኖር  ቻለ ? በህንድ ውስጥ የብረት መጠኑ ከዘጠና ዘጠን ፐርሰንት በላይ የሆነ የብረት ቴክኖሎጂ የብረት ምሰሶ ተገኝቷል ። ዘመናዊው የብረት ማቅለጫ ቴክኖሎጂ ደረጃ በልጦ የተገነኘ ነው ። እነዚህን ስልጣኔዎች ማን ፈጠረ? እንዱዴት የሰው ልጅ …በዚያን ጊዜ ፣ ረቂቅ ነፍሳት የነበሩበት .. እነዚህን ነገሮች ሊፈጥሩት ቻሉ ? እነዚህ ግኝቶች በአለም አቀፍ ደረጃ የሳይንቲስቶችን ትኩረት በጣም ስበዋል። ስለ እነዚህም ማብራራት ስላልተቻለ የቅድመ-ታሪክ ባህል እንደሆኑ ተደርገው ተወስደዋል።[1]»

በኦከልት ዓለም በአዝጋሚ ለውጥ ነው የተፈጠረችው የሚለውን አይቀበልም ። ከዚያ ይልቅ ግን የመንፈስን ህልውና አጉልቶ የሚያሳይ ነው ።

 


[1] ፋሉን ጎንግ ፣ የአማርኛ ትርጉነም ፣ ሊ ሁጂ ፤ ትርጉም ፣ በአብርሀም ተመስገን ፣ ታህሳስ 1999 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s