ግብፅ ወታደራዊ እርምጃ ዛቻ

ግብፅ ኢትዮጲያ የአባይ ወንዝ ላይ የራላ ታላቁን የህዳሴ ግድብን እሰራለሁ ብላ ከተነሳች ወዲህ ለግብፅ ጤና የሚሰጥ አልሆነም ። ግብፅ ኢትዮጲያ ግድቡን ለመስራት ያስችላት ዘንድ የአባይን ወንዝ አቅጣጫ ባስቀየረችበት ወቅት በሙሀመድ ሙርሲ የሚመራው የግብፅ መንግስት ከተቃዋሞ ፓርቲ መሪዎች ጋር በቀጥታ ባደረገው በቀጥታ ስርጭት በተላለፈው ስርጭት ላይ ተቃዋሚዎቹ ኢትዮጲያ ላይ ወታደራዊ እርምጃን እንውሰድ እስከ ማለት ደርሰዋል ። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች የግብፅ መንግስት ስብሰባቸውን በቀጥታ ስርጭት ያስተላለፈው ሆነ ብሎ ለኢትዮጲያ የማስፈራሪያ መልእክትን ለማስተላለፍ ነው የሚሉ አሉ ። በስብሰባቸው የተሳተፉ አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በበኩላቸው ደግሞ በስብሰባቸው ሳናውቅ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ሳናውቅ ነው አንድንሳተፍ የተደገረው ፣ ስብሰባቸው በቀጥታ እንደሚተላለፍ አናውቅም ነበረ ሲሉም ተደምጠዋል ። ያም ሆነ ይህነ ግን የግብፅ መንግስት ስብሰባቸውን ሆነ ብሎ ለኢትዮጲያ መረር ያለ መልእክት ለማስተላለፍ ያደረገው መሆኑ ግልፅ ነው ።
ይህም ኢትዮጲያን ማስቆጣቱ የታወቀ ነው ። ኢትዮጲያም ምላሿን በቁጣ የገለፀች ሲሆን የግብፅ መንግስትም በነገሩን ለማለዘብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ወደ አዲስ አበባ ልኳል ። ግብፅ ለማስፈራራት ካልሆነ በበስተቀረ ኢትዮጲያ ላይ ወታደራዊ እርምጃን ለመውሰድ የሚያስችላት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለችው ። ምንም እንኳን ግብፅ ለአመታት በተለይም ባለፉት የሆሲኑ ሙባረክ አገዛዝ ዘመን ለአሜሪካ ታማኝ ሆና በመቆየቷ መጠኑ የበዛ ወታደራዊ እርዳታን ስታገኝ ቆይታለች ።

Leave a comment