የአፍሪካ ህዳሴ

በዓለም ላይ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘመኑ ወደ አፍሪካ ያዘመመ ሆኖ መታየት ጀምሯል ። ለአንዱ ሲዘንብ ለሌላው ያካፋል እንዲሉ ለቻይናና ለሌሎች የደቡብ መስራቅ እስያ ያካፈው የስልጣኔና የምጣኔ-ሐብት ብልፅግና ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካም ማካ ፋት ጀምሯል ።

      ለአፍሪካ አህጉር ድህነት ብቸኛው ዋና ምክንያት ባይሆንም አንዱ ምክንያት በርካታ የአፍሪካ አገራት በባርነት ፣ ከዚያም በቅኝ ግዛት አገዛዝ ስር መውደቃቸው ለአህጉሩ መደህየት አንዱ ምክንያት መሆኑ አያጠራጥርም ። አፍሪካ ነፃነቷን ካገኘች በኋላም ቢሆን በአብዛኛው ስለ ፖለቲካ ፣ አስተዳደርና ስለ ምጣኔ-ሀብት ስለ መሳሰለው ጉዳይ እውቀት ባልነበራቸው ወታደራዊ መሪዎች እጅ ስልጣኑ በመግባቱ ምክንያት ከ1960ዎቹ ጀምሮ እስከ 2000ዎቹ ጅማሮ ድረስ ብዙዎቹ አፍሪካ አገራት ጉዞ የኋሊት ሆኖ ቆይቷል ።

      ነገር ግን የደቡብ ምስራቅ እስያ ሀገራት ማንሰራራት ከጀመሩ ወዲህ ከእድገቱ ፀበል ለአፍሪካ አገራት መድረስ ጀምሯል ። የምጣኔ-ሐብት እድገት ለአንድ አገር ጅማሮ ሲሆን ለዛ ሀገር ወደፊት በሌሎች ዘርፍ ለሚያስመዘግበው እድገት መደላድሉ የምጣኔ-ሐብት እድገቱ ነው ። ለአንድ ስልጣኔ ኢኮኖሚ መሰረት ሲሆን ከኢኮኖሚ እድገት ብቻ ግን እድገት ያበቃል ማለት አይደለም ።  በብዙዎቹ የአፍሪካ አገራት መሪዎች ካለፉት ስህተቶቻቸው በመማር ከመቼውም ጊዜ በተሻለ አመራርን መስጠታቸው መታዘብ ይቻላል ።

      የአፍሪካ አገራት ለዚህ አስፈጊውን ስልጣኔ መሰረት በመጣል ላይ መሆናቸው መልካም  ዜና ነው ። ነገር ግን እንደሚታወቀው አንድ ስልጣኔ በኢኮኖሚ እድገት ብቻ አያበቃም ከዚያ ይልቅ አንድ ጊዜ የሰዎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ከተሟሉ በኋላ ግን መንፈሳዊ ፣ ስነ-ልቦናዊ ባህላዊ ሀይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ እና ሀሳብን የመግለፅ ነፃነቶቻቸውን የመሳሰሉ ከፍ ያሉ ፍላጎቶቻችቸውን ወደ ማሟላት መሄዳቸው አይቀርም ።

ለዚህ አይነተኛ ምሳሌ የምትሆነው ቻይና ስትሆን ይህቺ ሀገር ምጣኔ ሀብቷን በአስደናቂ ፍጥነት በሀያና ሰላሳ አመታት ውስጥ ወደ ግዙፉ ምጣኔ ሀብት ስትቀይር በአንፃሩ የፖለቲካ አድተዳደሯ ግን በአንድ ፓርቲ ላይ የተመሰረተ ሆኖ መቀጠሉ ለወደፊት መረጋጋቷ ስጋትን መደቀኑ አይቀርም ። ነገር ግን በርካታ ተመልካቾች እንደሚገምቱት የመካከለኛው መደብ በቁጥና ፣በሀብት እየበረከተ ሲሄድ ተጨማሪ የፖለቲካ መብቱን መጠየቁ አይቀርም ። ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆን ወጣት ትውልዷን እ.አ.አ. በ1989 ዓ.ም. በታይናሚን አደባባይ ባደረጉት የተቃውሞ አመፅ የፈጀችው ቻይና እየበለፀገ ያለው ወጣት ህዝቧ የበለጠ የመናገር ነፃነትን ፣ የመምረጥ ሀሳብን የመግለፅ የመሳሰሉ ዲሞክራሲያዊ መብቶቹ በበለጠ እንዲከበሩለት መጠየቁ አይቀርም ።  

      ምእራባውያን ከላይ ከላይ ሲታይ ስልጣኔአቸው በቁሳዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት ላይ የተመሰረተ ቢመስልንም ወደ ውስጡ ሲገባ ግን ስልጣኔቸው የተመሰረተው በጣም መሰረታዊ በሆኑ ፍልስፍናዎች አስተሳሰቦችና አስተምህሮቶች ላይ ነው ። ከእነኚህ መሰረታዊ ከሆኑ የፖለቲካን ሆነ የህግ የምጣኔ ሀብት አስተምህሮዎቻቸው ዝንፍ የማይሉ ሲሆን ችግር ቢያጋጥማቸው እንኳን ጊዜ ሰጥተው መልሰው ነገሮችን ወደ ነበሩበት ያስተካክሉታል ።

      ምንም አስንኳን በ20ኛው ክፍል ዘመን ላይ የአለም ሀያሏ አገር አሜሪካ ብትሆንም አሜሪካንን የመሰረቱ መስራች አባቶቿ ግን ያቺን አገር መሰረት የጣሉት በአውሮፓውያን ፈላስፎች አስተረምህሮና ፍልስፍና ላይ ነው ። እንደ ጆን ሎኬና ፣ሩሶን በመሳሰሉ የእንግሊዝና ፈረንሳይ ፈላስፎች አስተምህሮዎች ላይ ነው ። በአብርሆት ዘመን ከአውሮፓ እንደ ዋና አሳብያንና ፈላስፎች ይቆጠሩ የነበሩት በተለይም የፈረንሳይ እንግሊዝ ፈላስፎችና ፀሀፍት ነበሩ ። አሜሪካ በምትመሰረትበት ወቅት በአለም ላይ ተሰሚነት የነበራቸው የአውሮፓውያን አሳብያን ነበሩ ። በመሆኑም አሜሪካ የእነሱን አስተምህሮ በመውስድ ራሷን እንደ አገር በሁለት እግሯ መቆም ችላለች ።

Advertisements

ዲሞክራሲ በአብዮት ?

ዲሞክራሲ በአብዮት ሊመጣ ይችላል ወይንስ አይችልም ? በታሪክ እንደታየው ከፈረንሳይ አብዮት ብንጀምር የመጀመሪያው የምእራቡ አለም አብዮት በመባል የሚታወቀው የፈረንሳይ አብዮት ከአብዮቱ ማግስት የታዩት ጃካባውያንና በሮስፒየር የተመሩት ብዙ ደምን በማፍሰሳቸው እና በርካታ የንጉሳውያንና መሳፍንቶችን በጊሎቲን ያለ ፍርድ በመጨፍጨፍ ይታወቃል ። ከዚህ በኋላም ቢሆን ፈረንሳይ ሪፐብሊክ አልሆነችም ከዚያ ይልቅ ናፖሌዎን ቦናፓርቴ በአምባገነንነት ወደ ስልጣን ሲመጣ ፈረንሳይን ወደ ዘውዳዊ ስርአት ሲመልሳት በአውሮፓም እንደ ወታደራዊ ጂኒየስ በሚቆጠረው በናፖሌዎን ዘመን ማለቂያ የሌለው ጦርነት ሰበብም ሆኗል ። በሩስያም በዛሩ መንግስተ መጨረሻ ላይ ከኬረንስኪ መውደቅ በኋላ  ስልጣን ላይ የወጡት እነ ሌኒንና ትሮትስኪ በኋላ ላይም ስታሊን ሚሊዮኖችን ጭዳ ያደረገ የሶቭየት ህብረት ስርአትን ሊያጠናክረው በቅቷል ።

እንዲህና እንዲያ እያልን እስከ በሀያኛው ክፍለ ዘመን በሶሻሊዝም ስም የተካሄዱት አብዮቶች አላማቸውን በማሳካት ፈንታ የአምባገነኖች ወደ ስልጣን መምጫ ጥሩ ሰበብ ነው የሆኑት ። በቻይና በማኦ የተመሩት አብዮተኞች የኮሚኒስት ስርአትን ሲመሰርቱ ፣ የቀድሞው የሊቢያው መሪ ሙሀመድ ጋዳፊ ሳይቀሩ ወደ ስልጣን የመጣሁት በአብዮት ነው የሚል መከራከሪያን ሲያቀርቡ ይሰማሉ ። በሀገራችንም እንዲሁ የ66 ቱ አብዮት ለብዙዎች ህይወት መጥፋትና ለወታደራዊ መንግስት ወደ ስልጣን መምጣት ሰበብ ሆኗል – ዋነኛው ግቡንም በመሳት ሀገሪቱ በእርስ በእርስ ጦርንተ ውስጥ ስትዘፈቅ ወታደሩ ስልጣኑን አጠናክሮ ቁጭ ሊል በቅቷል ፣ እርሱንም ለማስወገድ አገሪቱ በእርስ እርስ ጦርነት ልትዘፈቅ በቅታለች ። አብዮቶች አስፈላጊ ቢሆኑም በጥቂት መጠለፋቸውና አላማቸውን መሳታቸው በታሪክ በተደጋጋሚ የታየ ክስተት ነው ። የአረቦችም አብዮት የሚፈለገውን የዲሞክራሲ ስርአት ማምጣት መቻሉ አጠራጣሪ ነው ። 

ገናናነትና ስም

ስሙን የማይጠብቅ የኋላ ኋላ ገናናነቱን ማጣቱ አይቀሬ ነው ። በጣም ስልታዊ የሆኑ ተቀናቃኞች የተቀናቃኛቸውን ሰው ስም የዛን ሰው በማጥፋት ይጀምራሉ ። ምናልባት ገናናነት የቀድሞዎቹ በነገስታት ታሪክ ሊመስላቸው ይችላል ። ከቅርቡ እንኳን ስማቸውን ያጡ ወዲያውም የነበራቸውን ማንኛውንም ነገር ያጡ ሰዎች በርካታ ናቸው ። በተለይ በምእራቡ አለም የአንድ ሰው ተሰሚነቱ ፣ ገናናነቱ ወይንም ተወዳጅነቱ ጭምር በስሙ ላይ የተመሰረተ ሆኖ ይታያል ።

ገናና የሆኑ ሰዎች ሌላው ሰው እሚያከብራቸውን ህግጋት ለምንድነው እንደሌላው ሰው እማያከብሩት ? በነገራችን ላይ አንድ ሰው ትልቅ ስልጣንን ወይንም ሀይልን ወይንም ስምን ሲይዝ የሚኖርበትም ሀላፊነት እንደዛው ከባድ ነው ። 

በእርግጥ በዘመናችን በልሂቃኑና በተቀረው ህብረተሰብ መሐከል ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በሐብት ፣ በእውቀት በአኗኗር የጎሉ ልዩነቶችም በመታየት ላይ ይገኛሉ ። ልሂቃኑ ሀብታቸው ፣ ዝናቸው የሚያስገኝላቸው የአኗኗር ደረጃ በጣም ከመስፋቱ የተነሳ ቀድሞ ከነበረው ሰፍቶ ይታያል ።

የፖለቲካ ሳይንስ

ማን ይምራ ? ሲባል እንደ ጥንታዊ ግሪክ ታላላቅ ፈላስፎች አባባል አገርን መምራት የሚችለው ፣የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ፣ በልምድና በተሞክሮ የዳበሩ ሰዎች ናቸው አገርን ምመራት ያለባቸው ነው እሚሉት ጥንታዊ ግሪኮች ። ይህ ብቻ እንደ ጥንታዊ ግሪኮች አባባል ጥሩ መሪ ማለት መምራትን ብቻ ሳይሆን መመራትንም እሚያውቅ መሆን ይኖርበታል ይላሉ ። ይህም ማለት ሁልግዜም ብቸኛ መሪ ያልሆነ ፣ ባጠገቡ ካሉ ሰዎች ጋር የሚማከር ፣ የሌሎች ሰዎችን ሀሳብ እሚያዳምጥ ማለት ነው ። ይህ ህዝቡንም ይጨምራል ፣ ህዝቡን ፍላጎት ፣ ስሜትን መከተልም ሲኖርበት ፣ህዝቡ እማይፈልጋቸውን ወይም እማይስማማባቸውን ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት የህዝቡን ፍላጎትን ጭምር ለመጠበቅ ፈቃደኝነትን ማሳየት አለበት የሚል አስተሳሰብ አላቸው ።

     ከጥንት ግሪካውያን ወዲህ በመካከለኛው ዘመን የነበረው የስዩመ – እግዝአብሄር የዘውዳዊ ስርአቶች በተለያዩ የአለም ክፍሎች የነበሩበት ሲሆን ። አንድ ፈላስፋ እንደገለፀው ስዩመ – እግዝአብሄር ማለት የእግዝአብሄርን ህግጋትንና ትእዛዛቱን በመፅሀፉ ውስጥ የተደነገጉትን ነገሮች በሙሉ ስዩመ – እግዝአብሄር መንግስት መከተል አለበት ። እዚህ ጋ ስዩመ – እግዝአብሄር ለማሳሳቻውም ተግባራዊ ሳያደርግ ለማስመሰል ሳይሆን ህግጋቱንናና ደንቦቹን ከልቡ የተቀበለ መሆን አለበት።

     ስዩመ – እግዝአብሄር ንጉስ ትልቅ ሀላፊነትን የተሸከመ እንደመሆኑ ትልቅ የሞራል ወይም የስነ – ምግባር ሸክም አለበት ። ሲነግስ ቤተሰቡ ከሰጠው ስም በተጨማሪ የንግስና ስምን ይሰጠዋል ። አሁን ሲነግሱ ስዩመ – እግዝአብሄር ስለሆነ ከሰው የተለየና ከሰዎች የበለጠ ፍርድንና ፍትህን መስጠት አለበት ።

     ወደ ዘመናዊ የመንግስት ስርአቶች ብንሄድ ስዩመ – ህዝብ ነው ። ይህም ፓርላማዊ ወይም ሪፐብሊክ ይሆናል ። ዲሞክራሲ የሚለው ቃል ዲሞክራቲያ ከተባለው ቃል የመጣ ሲሆን ዲሞክራሲ ከመልካም አስተዳደር የሰፋ ፅንሰ – ሀሳብ ነው ። መልካም አስተዳደር አንዱ የዲሞክራሲ መሰረት ነው ። መልካም አስተዳደር የአንድ ተቋም በትክክል መተዳደር ፣ ትክክለኛ አስተዳደር መኖር ማለት ነው ።  ዲሞክራሲ ከመልካም አስተዳደር ሰፋ ያለ ፅንሰ – ሀሳብ ሲሆን የዲሞክራሲም አንድ አካል ነው ።

ማክያቬሊ ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስን መደላድል ፈጠረ ሰው ሲሆን ። እርሱም አዲስ የፖለቲካ አህጉርን ፈጠርኩ ነው እሚለው። ይሁን እንጂ የእርሱ ስራ ባለፉት 300 እና 400 በተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጓሜ ሲሰጠው ኖሯል ። በዚህም ማክያቬሊዝም የሚባል የፍልስፍናና የአስተሳሰብ ዘውግ የተፈጠረ ሲሆን አልፎ አልፎም እርሱ ከራሱ አስተምህሮዎች የተለዩ ሀሳቦችንም ያያዘ ነው ።

ወደ ዋናው ሀሳብ ስንመጣ የራሱን አዲስ ሀሳብ ሲያዘጋጅ የቀደምት ግሪኮችን እንዲሁም በክርስትና ሀይማኖት ላይ የተመሰረተውን የመካከለኛውን ዘመን ፍልስፍናን በመተቸት ነው እሚነሳው ። እንደ እርሱ አስተሳሰብ ፈላስፋዎች የሰውን ልጅ ከጨለማ ወደ ብርሀን ለማውጣት ይፈልጋሉ ። ለምሳሌ የፕሌቶ የዋሻው ተምሳሌት ሀሳቡ የሰውን ልጅ ከጨለማው ዋሻ ወደ ብርሀኑ የማውጣት እና ብርሀነ – ህሊናን  (enlightenment) እንዲቀዳጅ የማድረግ አለማ ያለው ነው ። ይሁን እንጂ እንደ ማክያቬሊ አስተሳሰብ ደግሞ ወደ ብርጀኑ እምመራችሁ መሲህ ሳይሆን እንዴት የሰው ልጅ በዚህ ጨለማ በሆነ አለም ህልውናችሁን እንደምታስጠብቁ ፣ እና ይህንን የጨለማ አለም እንደምትቋቋሙት አሳያችኋለሁ ነው እሚለው ።   

ትልቁ የሱ ካበረከታቸው ሀሳቦች መሀከል ስነ – ምግባርን ወይም ሞራልን በተመለከተ ቀድሞ በነበረው አስተሳሰብ ላይ ያቀረበው ትችት ነው ። እንደ ማክያቬሊ አባባል ሁለት አይነት ስነ – ምግባሮች ወይም ሞራሎች ሲኖሩ አንደኛው በህዝብ ፊት የሚደረግ ስነ – ምግባር ሲሆን ይህም ፖለቲካዊ ስነ – ምግባርን ይጨምራል ። ሁለተኛው አይነት ስነ – ምግባር ደግሞ ግለሰባዊ የሆነ ስነ – ምግባር ሲሆን ፤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ እሚመራው እሚዳኘው በፐብሊክ ሞራሊቲ ነው እንጂ በግለሰብ ሞራሊቲ አይደለም ።መሪው የሚጠየቅብበት ሞራሊቲና ግለሰብ የሚጠየቅበት ሞራላቲ ሉያያል ።

ሌላው ደግሞ ያለው የልሂቅ (elite) የሚባለው ህብረተሰብ ክፍል አስተሳሰብ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ህብረተሰብ እየሰረፀ በሄደ ቁጥር ያ መንግስት ሊናወጥ ወይም ሊፈራርስ ይችላል ። የዛን ሀሳብ ትክክለኛነት እየተረዳ በሚመጣው ተራው ህብረተሰብ ያ ሀሳብ ቦታን እያገኘ የበለጠ ጉልበት እየጨመረ ይሄዳል ። ይሄድና የዛ መንግስት ወይም ስረአት አደጋ ውስጥ ይወድቃል ።

የጥንቶቹ ግሪካውያን ፍልስፍና የሰው ልጅ ሄዶ ሄዶ የፖለቲካ ፀጋን (political virtue) ደረጃ ላይ ማድረስ ነው አላማው ወይም የመጨረሻው ግቡ ። በጥንት ግሪክ አባባል (man is a political animal) እናም ደስታውን ኑሮውን ሁሉንም ነገር እሚፈልገውም እሚያገኘውም (city state) ውስጥ ነው ። በነገራችን ላይ ይህ አስተሳሰብ ከምስራቃውያን የመንፈሳዊ እውቀት ጋራ በእጅጉ ይለያያል ። በምስራቃውያን አንድ ሰው ራሱን ማንቃት  በእውቀት መንጋቃት ደረጃ መድረስ ነው ዋናው አላማው መሆን ያለበት ። ቡድሂዝምን ብንወስድ ንቃት ከመንግስት ህልውና ጋር ምንም እሚያገናኘው ነገር የለም ።

በነገራችን ላይ የጥንቱን የግሪካውያንን ፍልስፍና በተለይም የፕሌቶን ፍልስፍና ከክርስትና ሀይማኖት ጋር ማስማማት ቀላል የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ የመጣውን የአሪስቲቶትልም ፍልስፍና ግን ከብዙ ጊዜያት በኋላ ነው ከክርስትና ሀይማኖት ጋራ ያስማሙት ። እሱ የሚለው እማይሆን አይነት ። (ideal) ላይ ትፈጥራላችሁ ሰውን በጎ (virtuous) ለማድረግ ትጥራላችሁ ነገር ግን ሰው ምን አይነት አስቸጋሪ እንደሆነ አልተረዳችሁም ፣ ሰው በትምህርት እና በምክር ብቻ ጥሩ አይሆንም የሀይል ዱላ ያስፈልጋል ነው እሚለው ።

ይህም (morality) ከ (immorality) ይመነጫል ፣ ፍትህም (Justice) ከኢ – ፍትሀዊነት (injustice) ይመነጫል ። አገር እሚመሰረተው ከወንጀል ነው ። ትልቅ ስልጣኔ የሚመሰረተው ትልቅ ወንጀል ተሰርቶ ነው ፣ በቀላሉ አይገኝም ፣ አልጋ ባልጋ አይሆንም የሚል ነው ።

MYSTICISM

በመሀከላችን የረቂቅ መንፈሳዊ እውቀት ባለቤቶች «ሚስቲክስ» ይገኛሉ ። ረቂቅ መንፈሳዊነት ወይም «ሚስቲዝም» ይባላል ። ይህ እውቀት ጥቂቶች ይዘውት የሚወለዱት ለብዙሀኑ ህብረተሰብ ግን ስውር ነው ። የመንፈስ ሚስጥራት ለረቂቅ መንፈሳውያን ግልጥ ሲሆኑ ፣ ይህ እውቀት ጥቂቶች ይዘውት የሚወለ  ዱት ለብዙሀኑ ህብረተሰብ ግን ስውር ነው ። የመንፈስ ሚስጥራት ለረቂቅ መንፈሳውያን ገሀድ ሲሆን ፣ ስለ ረቂቅ መንፈሳዊነት ምንም ለማያውቅ ሰው ግን እንግዳ  ነው ።

ጳውሎስ በመልእክቱ ላይ እናንተ በመንፈስ ህፃናት ናችሁ ይላል ። ቡድሀ በበኩሉ በርካታ «የተጨናነቁ ነፍሳትን » መመልከቱን ይናገራል ።

የአለማችን ታላላቅ ሀይማኖቶች በግለሰብ ደረጃ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት ሚስቲሲዝምን አጥብው ይከለክላሉ ። ይህም በአንድ በኩል ሰዎችን ከሀይማኖት የበለጡ ያደርጋቸዋል ፣ እንዲሁም በዚህ ደረጃ ሰዎች የተሸሸገ ሚስጥርን ማወቅ ከቻሉ ለሀይማኖቱ ስጋት ነው በማለት ፣ እንዲሁም የዚህ እይነቱ እውቀት ለአንድ ሰው ሊሰጠው የሚችለውን የሀይልና የተሰሚነትን ብቃት በመስጋት ሊሆን ይችላል ።  በአንፃሩ የአዲሱ ዘመን ፍልስፍና በመባል የሚታወቀው ፍልስፍና ረቂቅ መንፈሳዊነትንና ተመስጦን «ሜዲቴሽንን» ያበረታታል ።

በነገራችን ላይ ረቂቅ መንፈሳዊነትን የአለማችን ታላላቅ ሀይማኖቶች የማያበረታቱበት ዋነኛው ምክንያት አንድን ሰው ከመናፍስት ጋር በራሱ በቀጥታ እንዲገናኝ ያደርገዋል በሚል ነው ። በመካከለኛው ዘመን አውሮፓ በካቶሊክ እምነት ሀያልነት በሰፈነበት ዘመን እንደ ጠንቋይና አስማተኛ ሲታዩ የነበሩ በርካታ ሰዎች በግፍ መገደላቸው ይታወቃል ።

መንፈስ

መንፈስን በተመለከተ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ ጳውሎስ እጅግ ብዙ ፅፏል ፤ «በመንፈስ ያለ ሰው ሌሎችን ይመረምራል እንጂ ሌሎች እርሱን አይመረምሩትም» ይላል ። እያንዳንዱ ሰው አንድ አይነት መንገስፈስን ይወክላል ። ሁላችንም አንድ አይነት መንፈስን ይዘን የየተወከድን ሲሆን ፣ ስቴንሰር የተባለው የረቂቅ መንፈሳዊ ሊቅ እንደሚለው «ማንኛውም መንፈስ መጥፎ የለውም » ይላል ። መጥፎ ወይም ጥሩ ከመሆን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ። መንፈስ በራሱ መጥፎም ፣ ጥሩም አይደለም – በሚይዘው ሰውና ለሚጠቀምበት አላማ ነው የመንፈስ አካሄድ የሚገለጠው ።

ለምሳሌ የክርስትና ሀይማኖትን ብንወስድ ሰይጣን ከሌሎች መላእክት የበለጠ ስልጣንና እው  ቀት የነበረው መልአክ እንደነበረ ነገር ግን የተሰጠውን ስልጣን በፈጠረው በእግዝአብሄር ላይ በመቅናትና ለክፋት ስላዋለው ከሰማይ ቤት እንደተባረረ በክርስትና ሀይማኖት ሊቃውንት ይገለፃል ። ይህም ትልቅ ስልጣንና እውቀትን የያዙ ፣ ነገር ግን የተሰጣቸውን መንፈስ ለክፋት እና አለአግባብ የተጠቀሙ ግን ከስልጣኑ ወንበር እንደሚወድቁ የሚያሳውቅ ነው ።

በነገራችን ላይ ከማንኛውም ምድራዊ የፖለቲካ ስልጣን ወይም ሀብት በበለጠ የመንፈስ ስልጣን እጅግ የላቀ ነው ። በሠው ልጅ ታሪክ የተፈጠሩ ታላላቅ የጥበብ ስራዎች ፣ ስእሎች ፣ ስነ-ፅሁፎች  ፣ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች ስራቸውን ያከናወኑት በመንፈስ እየተመሩ መሆኑ ይታወቃል ። በእውቀቱ ስዩም መግባትና መውጣት በተሰኘው መፅሀፉ መግቢያ ላይ ይህንን እውነት ከትቦት እናገኘዋለን ።

«……..»

መንፈስ የራሱ እርከን ያለው ሲሆን ፣ በውስጡም በርካታ እርከኖችን ይዟል ። ከታላቁ የክርስቶስ መንፈስ ጀምሮ እስከ መጨረሻው እርኩስ መንፈስ ድረስ መንፈስ ድረስ ማለትም በመፅሀፍ ቅዱስ ላይ «ለምን ያለጊዜው መጣህብን» እስካሉት ወደ እርያው እስከ ገቡት ድረስ ማለት ነው ።

በልሳን መናገር የአንድ ሰውን በመንፈስ መገለጥን የሚያመለክት ሳይሆን ያ ሰው የተጠናወተውን መንፈስ አይነት የሚያመለክት ነው ። ያንን ሰው የያዘው መንፈስ ጥሩም ሊሆን ይችላል ወይም መጥፎ መንፈስ ሊሆን ይችላል ። ነገር ግን ሰዎች በመንፈስ በሚያዙበት ወቀት በልሳን መናገርና ሌላ ሰው ሊረዳው የማይችለውን ነገር ሊያነበንቡ ይችላሉ ። እየሱስ ክርስቶስም ባስተማረበት ወቅትም «በልሳን ይናገራሉ ፣ እባብን ይይዛሉ» ብሎ ስለ እነሱ ትንቢትን ተናግሯል ።

መንፈስ በእንሰሳት አያድርም ።  አንዳንድ እንሰሳት አደጋ ሲመጣ ለሰው  ከሰው ልጅ አስቀድመው የሚረዱ አሉ ። ለምሳሌ እንደ አህያ ፣ ፈረስና ሌሎችም እንደሰሳት በአካባቢያቸው የተፈጥሮ አደጋ ሊመጣ ባለበት ወቅት የተለየ ድምፅና መጨነቅን ያሳያሉ ። አንዳንድ ነፍሳት ከብዙ መቶዎች  ኪሎ ሜትር ያሉ እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ ሲል አስቀድመው እንደሚያውቁ የጃፓን ሳይንቲስቶች ደርሰውበታል ።

የሰው ልጅ በአዝጋሚ ለውጥ የመጣ ከሆነ መንፈስ የሚባለው ነገር ከየት መጣ ታዲያ ?

እኛና ስሜቶቻችን

ዋና ዋና የሚባሉት ስሜቶች በአንዳንድ ሰዎች ለምሳሌ ዎለሽ እንደሚለው የሰው ልጅ ዋና ዋና ስሜት የሚባሉት ፍርሀትና ፍቅር ሲሆኑ ፣ ደግሞ ዋና ዋና የሚባሉት የሰው ልጅ ስሜቶች ሶስት ናቸው እነሱም ናቸው ።

የአንድ ሰው ስሜቶች ከዝቅተኛ ስሜቶች ይጀምራል ። ስሜቶች አንድ ሰው ለመኖር ከሚያስፈልጉት መራብ ፣መጠማት ፣ የመሳሰሉት አንድ ሰው በደመ-ነፍስተ ለመኖር ህልውና እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ።

ሶስቱ ጠንካራ ስሜቶች በመባል በዶ/ር ሄለን ፊቨር በተሰኙ የሰው ዘር አጥኚ ወይም አንትሮፖሎጂስት የተገለፁት ጠንካራ የጉጉትና አንድን ነገር የመሻት ወይም ጥማት ስሜት «lust» ፣ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ የመነቃቃት ስሜት «infatuation» እና በፍቅር የመጣመር ስሜት «attachment » ናቸው ። እንደ ዶክተሯ ገለፃ እያንዳንዱ ጥልቅ ስሜት በአእምሮ ውስጥ የራሱ የሆነ ባዮ ኬሚስትሪ እንቅስቃሴ አለው ። ይሄውም ግለሰቡ ከአንድ ሰው ጋር በሚጣመርበት ጊዜ አእምሮውን የማንቃትና የማብራት ሚናውን ይወጣል የሚል አመለካከት አላቸው [1]

ንዴትን ብንወሰድ አንድ ሰው በትክክለኛ ምክንያቶች ሊናደድና ስሜቱን ሊያሳይ ይችላል ። ስሜቶች በቅዱሳን መፅሀፍትን ብንወስድ እየሱስ ክርስቶስን የአባቴን ቤተ-መቅደስ የገበያ ቦታ አደረጋችሁት የሚለው ቁጣና ንዴት አግባብነት ያለው ሲሆን ፣ በአንፃሩ ደግሞ ቃየል በወንድሙ ላይ በቅናት መነሳሳቱ ደግሞ በክፋት የተነሳሳ የቁጣና የንዴት ስሜት ነው ።


[1] ሳይኮ ላቭ ፣ ኤልያስ ገብሩ – ገፅ 2 ፣ ታህሳስ 2005

እውቀትና ስልጣን

ታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ፕሌቶ «ፈላስፎች መምራት አለባቸው » ሲል እውቀት ስልጣንን ሊጨብጥ ይገባል ከሚል አስተሳሰብ ነው ። ስልጣን በእውቀት ስር መዋል አለበት እንጂ ፣ ስልጣን ከእውቀት ማፈንገጥ የለበትም ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው ።

ብዙውን ጊዜ በአለም ላይ እውቀት ሳይኖር ስልጣንን መጨበጥ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ ነው ። ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ያሉ ፣ በአመፅ ከፍተኛውን የእውቀትን ደረጃ በሚጨብጡበት ወቅት በርካታ ጥፋቶችን በተለያዩ አገራት ላይ እንዳደረሱ በታሪክ የተመዘገበ ነው ። ብዙውን በዘላቂ እውቀት ላይ ያልተመሰረተ ስልጣን ዘላቂ የማይሆን ሲሆን ፣ መምራት ራሱን የቻለ እውቀትን የሚጠይቅ ሲሆን ፣ ስልጣን ዘለቄታ አይኖረውም ። 

በአሁኑ ዘመን በአብዛኛው የፖለቲካ አመታራሮች በምእራባውያን አገራት ሳይቀር ውድቀትን አስከትሏል ። ለዚህም የፖለቲካ ሰዎች ስለ ህሊና ንቃት ፣ ስለ ሀይመኖት እና ስለ ሰብአዊነት በአጠቃላይም ስለ ሰው ዘር በአለም ላይ በጋራ ተባብሮ መኖር የተሻለ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ።

የምእራቡ አለም ሜሪቶክራሲ መሆኑ በተሻለ ፖለቲካቸው እንዲመራ አስችሏል ። ነገር ግን በጣም ችሎታና አቅም ያላቸው ሰዎችን ብዙው ጊዜ ወደ ፖለቲካው አለም እንደማይገቡ ግን የታወቀ ነው ። ያም ሆኖ ግን አንድ የአሜሪካ ፕወ ፕሬዝዳንት ተመርጦ ወደ ስልጣኑ ሲመጣ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው አማካሪዎች ዙሪያውን የሚከቡት ሲሆን የአካዳሚ ሰዎች በተለያየ ዘርፍ የሰለጠኑ ፣ በኢኮኖሚክስ በስነ- ልቦና ፣በጋዜጠኝነት ፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በህግ እንዲሁም በፖለቲካና በዲፕሎማሲው መስክ ልምድና ስልጠናው ያላቸው ፣ እንዲሁም አንድ ችግር በድንገት ቢፈጠር ሃሳብን ማመንጨት የሚችሉ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሳይቀር ተፈልገው የቡድኑ አባል በመሆን አማካሪዎች ሆነው ይመደባሉ ። እነሱም ቢሆኑ ይህንን ሲያደርጉ የፖለቲካ ታማኝነትን አይተው መሆኑ የታወቀ ነው ፣ ነገር ግን ከዋና ዋናዎቹ ፓርቲዎች የሚውጣጡት ሰዎች ውስጥ የዚህ አይነትን ሰዎችን ማግኘት አስቸጋሪ አይደለም ። ይህ ብቻም ሳይሆን ምእራባውያን በተለይም አሜሪካኖች የፖለቲካ ድጋፋቸውን በመቀያየርም ይታወቃሉ ። በአንድ ወቅት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የነበረ በሌላ ወቅት ደግሞ የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባል በመሆን የራሱን አባልነት መቀያየር የተመደ ነው ።

ዲሞክራሲ መኖሩ ሰዎች በችሎታቸው ወይም በሜሪታቸው ወደ ከፍተኛው ስልጣን እንዲመጡ ቢያስችልም በጣም የተካኑት ግን የራሳቸውን ስራ በመስራት ፣ የራሳቸውን ግዙፍ ኩባንያውን ዎችን በመመስረትና በፊልም ፣ በስነ-ጥበብ ዘርፍ ነው የሚሰማሩት ።

ታላቁ መፅሀፍ

በዓለም ላይ ከተፃፉ ታላላቅ መፅሀፍት መፅሀፍ ቅዱስ ተወዳዳሪ የለውም ። መፅሀፍ ቅዱስ ህሊናዊ-ንቃት ደረጃ ው እጅግ ከፍተኛ ሲሆን ፣ ማንም በቀላሉ በሚረዳው እንዲሁም እጅግ የረቀቁ እና ለመረዳት እጅግ ውስብስብ ሐሳቦችን አ ጣምሮ የያዘ ነው ።

መፅሀፍ ቅዱስ የሚጀምረው ከአዳም ሲሆን ፣ አዳም ተምሳሌታዊ ነው ። አዳም ራሱ የሰው ልጅ ነው ። የሰው ልጅ የገባበትንና የሚጠብቀውን ኑሮ የሚያሳይ ነው ። ለምሳሌ አዳም «በላብህና በወዝህ፣ እንጀራን ትበላለህ» የተባለው የሰው ልጅ በዚህች ምድር ላይ የሚጠብቀውንና የሚኖረውን ኑሮ የሚያሳይ ነው ።

«ለፍጥረታዊው ሰው የእግዝአብሄር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም ፣ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም ። መንፈሳዊው ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ፣ ራሱ ግን በማንም አይመረመርም » ቆሮ 2፣14

ቀጥሎም ጳውሎስ «የስጋ እንመሆናችሁ በከርስቶስም ህፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም ። ገና ፅኑ መብል መብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ ፣ ገና ስጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁም ? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱም ? » ቆሮ ምእራፍ ።፣3፡1-4

በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ አምላክነቱን እንኳን ትተን እንደ ሰው እንኳን ቢታይ እየሱስ ክርስቶስን እሚወዳደር የለም ። በአሁኑ ወቅት ምእራባውያን ፀሀፍት የእየሱስ ክርስቶስን ስብእናና ማንነት ጥያቄ ውስጥ ማስገባትና ማቃለል ጀምረዋል ። አይሁዳውያን አሁንም ድረስ ለእየሱስ ክርስቶስ ይቅርታን እንዳላደረጉለት ይታወቃል ።

ህሊናዊ ንቃት እና አእምሮ

ህሊናዊ ንቃት ደረጃ መድረስ የሚቻለው አእምሮን ማለፍ ሲችል ብቻ ነው ። ዓለምን የሚመራው አእምሮ ሲሆን ፣ የሳይንስ ፣ የቴክኖሎጂ እውቀቶች እያደጉ ሲሄዱ በአንፃሩ ደግሞ የሰው ልጅ ህሊናዊ ንቃት ግን ልክ እንደ እውቀት የሚያድግ አይደለም ። ከዚያ ይልቅ ግን ማንኛውም ሰው የራሱን ህሊናዊ ንቃት በራሱ መንገድ መሳደግና ኮትኩቶ ማሳደግ አለበት ። ማንኛውም ሰው በራሱ መንገድ ህሊናዊ እውቀቱን ማሳደግና ከፍተኛው ሰረ ደረጃ ላይ መድረስ የሚችለው በራሴ መንገድ ነው ።

እውቀት ግን በየትምህርት ቤቶች የሚሰጥ ነገር ሲሆን ፣ እጅግ የተራቀቁ የሚባሉ እውቀቶች ሳይቀሩ በማስተማር ፣ በማንበብ ወደ ሌሎች ሊረዷቸው ወደ ሚችሏቸው ሰዎች በቀላሉ ሊተላለፉ ይችላሉ ። 

ማንኛውም መንፈሳዊ አስተማሪ እንደሚያውቀው አእምሮን ማለፍ ሲችል ነው አንድ ሰው ፣ መንፈሳዊ መፀገለጥ ደረጃ ሊደርስ የሚችለው ።