እስራኤል እና አረቦች

«ጨዋታ ቀያሪ» ያሏቸውን የጦር መሳሪያዎችን በአረቦች እጅ ከገባ የመካከለኛው ምስራቅ የሀይል ሚዛን እንደሚለወጥ ኢሁድ ኦልመርት የተባሉ የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ወቅት አስታውቀው ነበረ ። የባሽር አሳድ መንግስት እየተዳከመ በሄደበት ወቅት ያሉትን ሚሳይሎችንና ምናልባትም የኬሚካል የጦር መሳሪያዎቹን ለሂዝቦላ ለማቀበል ደርሸበታለሁ ያለችው እስራኤል ከሶሪያ ወደ ሊባኖስ ሊላኩ የነበሩትን ተጓዥ መኪኖችን ሶርያ ውስጥ ገብታ በተደጋጋሚ በአየር በመደብደብ ለሂዝቦላህ እንዳይደርስ ማድረግ ችያለሁ ብላለች ። ሂዝቦላህ በበኩሉ ሶርያ ውስጥ ተዋጊዎቹን በማስገባት ለሶርያ መንግስት በማገዝ ውጊያ መግጠሙም ይታወቃል ። ሊባኖስ ውስጥ ያሉ ሌሎች ታጠቃ ሀይሎችም በሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ወገን በመለየት ውጊያው ውስጥ መሳተፋቸው ይታወቃል ። በእርግጥ እኚህ የሶርያ ሀይሎች ሰላማዊዋን ሊባኖስን ወደ ሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ መጨመራቸውን አልተገነዙቡት ይሆናል ፣ ነገር ግን በአደገኛው የሶርያ የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ የእነኚህ የሊባኖስ ሀይሎች መነከራቸው ለሊባኖስ ሰላም ሊያናጋ የሚችል መሆኑ የታወቀ ነው ።  

 ይህ ብቻም ሳይሆን እስራኤል በጦርነት እየተዳከመ የነበረውን የአሳድን መንግስት ሶርያ ውስጥ በመግባት የጦር መሳሪያ ማከማቻ ናቸው ያለቻቸውን የጦር መጋዘኖችን በተደጋጋሚ በአውሮፕላን ደብድባለች ።  

አሜሪካኖች በበኩላቸው በበሽር አል-አሳድ የሚመራው የሶሪያ መንግስት የኬሚካል የጦር መሳሪያ ተጠቅማች የሚል ማስረጃን አግኝተናል በማለት ወታደራዊ እርምጃን በሶሪያ ላይ ለመውሰድ መዛታቸው አልቀረም ። በአንፃሩ ሩስያ አሜሪካ ሶርያ ላይ ወታደራዊ እርምጃን ለመውስድ እያጤነችበት ባለችበት ወቅት ፣ ለባሽር አል አሳድ መንግስት የጦር መሳሪያ ድጋፍን ያደርጉ ነበረ ። ሩስያውያን በዚህ ብቻ ሳይወሰኑ ሰ-300 የተሰኘውንና እጅግ ዘመናዊ የሆነ ፀረ-አውሮፕላን  ሚሳይልን ለሶሪያ ማስታጠቃቸውንም ገልፀዋል ። ይህ ሚሳይል በሶርያም ሆነ በእስራኤል ድንበር ውስጥ ያለን አውሮፕላን በ200 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ማውደም የሚችል ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s