እውቀትና ስልጣን

ታላቁ ግሪካዊ ፈላስፋ ፕሌቶ «ፈላስፎች መምራት አለባቸው » ሲል እውቀት ስልጣንን ሊጨብጥ ይገባል ከሚል አስተሳሰብ ነው ። ስልጣን በእውቀት ስር መዋል አለበት እንጂ ፣ ስልጣን ከእውቀት ማፈንገጥ የለበትም ከሚል እሳቤ በመነሳት ነው ።

ብዙውን ጊዜ በአለም ላይ እውቀት ሳይኖር ስልጣንን መጨበጥ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ ነው ። ዝቅተኛው ደረጃ ላይ ያሉ ፣ በአመፅ ከፍተኛውን የእውቀትን ደረጃ በሚጨብጡበት ወቅት በርካታ ጥፋቶችን በተለያዩ አገራት ላይ እንዳደረሱ በታሪክ የተመዘገበ ነው ። ብዙውን በዘላቂ እውቀት ላይ ያልተመሰረተ ስልጣን ዘላቂ የማይሆን ሲሆን ፣ መምራት ራሱን የቻለ እውቀትን የሚጠይቅ ሲሆን ፣ ስልጣን ዘለቄታ አይኖረውም ። 

በአሁኑ ዘመን በአብዛኛው የፖለቲካ አመታራሮች በምእራባውያን አገራት ሳይቀር ውድቀትን አስከትሏል ። ለዚህም የፖለቲካ ሰዎች ስለ ህሊና ንቃት ፣ ስለ ሀይመኖት እና ስለ ሰብአዊነት በአጠቃላይም ስለ ሰው ዘር በአለም ላይ በጋራ ተባብሮ መኖር የተሻለ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ።

የምእራቡ አለም ሜሪቶክራሲ መሆኑ በተሻለ ፖለቲካቸው እንዲመራ አስችሏል ። ነገር ግን በጣም ችሎታና አቅም ያላቸው ሰዎችን ብዙው ጊዜ ወደ ፖለቲካው አለም እንደማይገቡ ግን የታወቀ ነው ። ያም ሆኖ ግን አንድ የአሜሪካ ፕወ ፕሬዝዳንት ተመርጦ ወደ ስልጣኑ ሲመጣ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው አማካሪዎች ዙሪያውን የሚከቡት ሲሆን የአካዳሚ ሰዎች በተለያየ ዘርፍ የሰለጠኑ ፣ በኢኮኖሚክስ በስነ- ልቦና ፣በጋዜጠኝነት ፣ በህዝብ ግንኙነት፣ በህግ እንዲሁም በፖለቲካና በዲፕሎማሲው መስክ ልምድና ስልጠናው ያላቸው ፣ እንዲሁም አንድ ችግር በድንገት ቢፈጠር ሃሳብን ማመንጨት የሚችሉ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰዎች ሳይቀር ተፈልገው የቡድኑ አባል በመሆን አማካሪዎች ሆነው ይመደባሉ ። እነሱም ቢሆኑ ይህንን ሲያደርጉ የፖለቲካ ታማኝነትን አይተው መሆኑ የታወቀ ነው ፣ ነገር ግን ከዋና ዋናዎቹ ፓርቲዎች የሚውጣጡት ሰዎች ውስጥ የዚህ አይነትን ሰዎችን ማግኘት አስቸጋሪ አይደለም ። ይህ ብቻም ሳይሆን ምእራባውያን በተለይም አሜሪካኖች የፖለቲካ ድጋፋቸውን በመቀያየርም ይታወቃሉ ። በአንድ ወቅት የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል የነበረ በሌላ ወቅት ደግሞ የዲሞክራቲክ ፓርቲው አባል በመሆን የራሱን አባልነት መቀያየር የተመደ ነው ።

ዲሞክራሲ መኖሩ ሰዎች በችሎታቸው ወይም በሜሪታቸው ወደ ከፍተኛው ስልጣን እንዲመጡ ቢያስችልም በጣም የተካኑት ግን የራሳቸውን ስራ በመስራት ፣ የራሳቸውን ግዙፍ ኩባንያውን ዎችን በመመስረትና በፊልም ፣ በስነ-ጥበብ ዘርፍ ነው የሚሰማሩት ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s