የከሸፈው የአረቡ ዓለም አብዮት

      እ.ኤ.አ በ 2011 ዓ.ም. በተቀጣጠለው የአረቡ ዓለም አብዮት ማለትም በአረብ ስፕሪንግ አማካይነት ለበርካታ አስርት አመታት በላይ ተጨቁነው የኖሩትን አምባገነኖችን በማስወገድ ምንም እንኳን የተሳካ አብዮትን ቢያካሂድም እንዲሁም በአካባቢው ለክፍለ ዘመናት በብልሹ አሰራርና በዝምድናና በሙስና የሚገባውን ያህል ሳያድግ የኖርው የአረቡ አለም ህዝብ የኢኮኖሚው ችግር ፈጦ መውጣቱ ለመካከለኛው ምስራቅ ብቻ ሳይሆን ለተቀረውም አለም ጭምር ስጋት ላይ የጣለ ክስተት ሊሆን በቅቷል ።

አብዮቱ በትክክለኛው ሰአት መደረጉ ተገቢ ቢሆንም አብዮቱን ተከትሎ በአረቡ አለም የተከሰቱት ያልተጠበቁ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ፣ ስልጣኑ በምርጫ አማካይነት በእስላማዊ ፓርቲዎች እጅ በቀላሉ መግባቱና እስከላማዊ አጥባቂዎቹም በቱኒዝያ አለማዊ የፖለቲካ አቋምን ሲያራምዱ የነበሩ የፖለቲካ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በሊቢያና በግብፅም እንዲሁ ስልጣንን በጨበጡ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደተፈራው ስልጣናቸውን ማጠናከራቸው ፣ በግብፅ በሙሀመድ ሙርሲ የተመሩት እስላማዊ ወንድማማች ፓርቲ መሪዎች ህዝቡን በአግባቡ ሳያማክሩ ህገ-መንግስት ማውጣታቸው ለሙሀመድ ሙርሲ ከስልጣን መወገድና ለግብፅ መረጋጋትን ለማጣት ሰበብ ሆኗል ።  

በሶርያ የተከሰተው ሁኔታ ግን ከሁሉም የከፋ ሲሆን ተቃውሞው ወደ እርስ በእርስ ጦርነት በመለወጥ ከአንድ መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ሶርያውያን ህይወታቸውን ሲያጡ ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ከአገር ሲሰደዱ ፣ አገሪቷ ከተሞቿ ሲፈራርሱ በርካታ ህፃናቶቿ ሲያልቁ እንዲሁም በአለም ቅርስነት የተመዘገቡ በአሌፖና በሌሎች ከተሞቿ የሚገኙ እጅግ ጥንታዊ የሆኑ መስጊዶችና ቅርሶችንም ጭምር እንዳልነበሩ ሆነዋል ። ይህ  ዘግናኝ ጦርነት ከዚህ በፊት ታይተው የማይታወቁ የሀይል እርምጃዎች የተወሰዱበት ነው ። ከተሞች በአዳፍኔ የተደበደቡበት ፣ ሲቪሎች ያለቁበትና የኬሚካል የጦር መሳሪያም ጭምር ስራ ላይ የዋለበት ሆኗል ።  

የእርስ በእርስ ጦርነቱ መራዘሙም ከጎረቤት በሽምቅ ውጊያ ልምድ ያለው ሂዝቦላህ ለሶሪያው የአሳድ መንግስት አግዞ ጦርነት ውስጥ ሲገባና በተቃዋሚዎች የተያዙ ከተሞችን ሲያስለቅቅ ፣ እንዲሁም ከኢራንም የአሳድ መንግስት የዲፕሎማሲያዊና ወታደራዊ ድጋፍን ማግኘቱም ይታወቃል ።

ምእራባውያንና እንደ ሳኡዲ አረቢያና ኳታር ያሉት የመካከለኛው ምስራቅ አገራትም በበኩላቸው ለተቃዋሚዎቹ ጦር የጦር መሳሪያንና የገንዘብ ድጋፍን በማድረግ ጦርነቱን አቀጣጥለውታል ። በአለዋይት ሺአዎች የሚመራው የአሳድ ቤተሰቦች መንግስት በቀላሉ የሚወድቅ አልሆነም በዚህም ምእራባውያን ራሳቸው መሳሪያ ከማቀበል አልፈው ጦር ለማዝመትም እስከማሰብ ደርሰዋል ።

 በሊቢያም እንዲሁ በእስላማዊ ታጣቂዎች መሀከል መግባባት ሊሰፍን አለመቻሉና መንግስት ሁሉንም ታጣቂዎች ወደ አንድ ተቋም ስር ማምጣት አለመቻሉ በየጊዜው በሊቢያ ከተሞች ውስጥ ቦምቦች ሲፈነዱ ፣ በግብፅም ምንም ሰእንኳን ሙሀመድ ሙርሲ ተመርጠው ስልጣን ቢጨብጡምና ህጋዊ የስልጣን ባለቤት ቢሆኑም በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ የተፈለገውን ውጤት ማምጣት ባለመቻላቸው ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍን ባደረገበት ወቅት የግብፅ ወታደራዊ ሀይል ለሙሀመድ መርሲ ሁኔታውን እንዲያስተካክሉ 48 ሰአታትን ብቻ በመስጠት ከስልጣን ሊያወርዳቸውና ለእስር ሊዳርጋቸው በቅቷል ። ይህን ተከትሎ በተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችም ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፣ በርካቶችንም የአካል ጉዳት ተዳርገዋል ።

በእርግጥ ዲሞክራሲ በጨቅላ ደረጃ ባለበት ወቅት ህዝቡ በአንድ አመት ውስጥ ካልተሻሻለልኝ ብሎ ትእግስትን ማጣቱ የዲሞክራሲ ልምድ አለመኖርን ያሳያል ። ዲሞክራሲ የዳበረበት አገር ቢሆን ኖሮ ግን አንድ አመት በጣም አጭር ጊዜ በመሆኑ ለውጡን በትእግስት መጠበቅ ይኖርበት ነበረ ። ሙርሲ የቀራቸውን ሶስት አመት ጨርሰው ከስልጣን ማስወገድ በርካታ ብጥብጦችንና አለመረጋጋቶችን ማሰወ ስወገድ ይቻል ነበረ፣ ነገር ግን በዋነኛነት የሙርሲን የእስልምና ፖሊሲዎችን ባለመደገፍ ወይም በመፍራት ወታደሩም ሆነ ምእራባውያን ሀይሎች በሙርሲ ፖሊሲዎች ደህንነት ሊሰማቸው እንዳልቻል ግልፅ ነው ።

በአሜሪካን አገር ፕሬዝዳንት ቡሽ በኢራቅ ባካሄዱት ጦርነት ወቅት የአሜሪካን ወታደሮች ከባድ መስዋእትነትን እየከፈሉ በነበረበት ወቅት በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ከኢራቅ የእንውጣ ጥያቄ በተደጋጋሚ ከህዝቡም ሆነ ከአሜሪካ ኮንግሬስ ተደጋጋሚ ቢቀርብላቸውም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ጦራቸውን ከኢራቅ አላስወጣም በማለታቸው ዲሞክ ራሲ ያደገበት አገር ስለሆነ ህዝቡ ልክ የስልጣን ዘመናቸው ሲያልቅ በመጠበቅ ኦባማን በመምርጥ አሜሪካንን ከኢራቅ የጦርነት ሊያላቅቁ ችለዋል ። ዲሞክራሲ በዳበረበት አገር ምንም እንኳን የተመረጠው ፕሬዝድዳንት ህዝቡ የማይፈልገውን ፖሊሲን ቢከተልም ፣ ወይም የተሰጠውን ከባድ ሀላፊነት ለመወጣት አቅም ቢያንሰው በአንድ ጊዜ ከስልጣንህ ተነስ አይባልም ከዚያ ይልቅ ግን የስልጣን ዘመኒ እስከሚያልቅ ድረስ ጠብቆ ልክ የስልጣን ዘመኑ ሲያልቅ የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት የበለጠ ለመረጋጋትና ለዲሞክራሲው እድገት ወሳኝ ነው ።  በግብፅ የሆነው ግን ስልጣን ዘመኑን ያልጨረሰውን ፕሬዝዳንት ከስልጣን በማስወገድ የባሰ ቀውስንና ግርግርን ማምጣት ሆኗል ።

እንጭጩ የግብፅ ዲሞክራሲ በዚህ አይነት መንገድ ሀዲዱን ሲስት ወታደሩ ተመልሶ ወደ ስልጣን ሊመጣና የተወሰኑ ሲቪሎችን ፕሬዝዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ በመሾም ሀገሪቱን ስልጣን በመጨበጥ ድጋሚ ምርጫ መደረግ አለበት ብሎ ወስኗል ። ይህንንም በመመቃወም በርካታ ግብፃውያን ሰልፍ ሲወጡ በመቶዎች የሚቆጠሩትም ህይወታቸውን ሊያጡ በቅተዋል ። ግብፅ በአለመረጋጋት ስትታመስ በርካታ የመካከለኛው መደብ አባላትም ቤተሰባቸውን በመያዝ ከግብፅ መውጣት ቀጥለዋል ።

በነገራችን ላይ ግብፅ ካላት እጅግ ስልታዊ ከሆነ መልከአ-ምድራዊ አቀማመጧ አንፃርና እንዲሁም የስዊዝ ካናል ባለቤት እንደመሆኗ በግብፅ የሚፈጠር ረብሻንም ሆነ ብጥብጥ በአካባቢው የሚተላለፈውን የአለም ንግድን እንደሚያውክ ግልፅ ነው ። በተለይ አውሮፓውያን ዋነኛው የንግድ መተላለፊያ በሆነውና በመካከለኛው ምስራቅ የሚመረተው የዓለም ነዳጅ በሚጓጓዝበት ዋነኛ በሆነው በስዊዝ ካናል ላይ የሚደርስ መዘጋትም ሆነ የባህር መጓጓዣ መስመር መስተጓጎል በኢኮኖሚያቸው ላይ የከፋ ጉዳትን እንደሚያስከትል የታወቀ ነው ። የግብፅን ብጥብጥ በስጋት መመልከት ይዘዋል ። አውሮፓውያን የውጭ ጉዳይ ሀላፊያቸውን ካትሪን አሽተንን ወደ ግብፅ በመላክም ከሙሀመድ ሙርሲ ጋር የመጀመሪያውን ውይይት አድርገዋል ።

በግብፅ ያለው ሁኔታ ከቁጥጥር ውጪ ቢወጣ የአለም ዋነኛው የንግድ መስመር ሲዘጋ ዝም ብለው ያያሉ ማለት አስቸጋሪ ነው ። እንደ ሶርያ አይነት የተጋጋለ የእርስ በእርስ ጦርነት በግብፅ ቢካሄድ ምእራባውያን እጃቸውን ማስገባታቸው የማይቀር ነው ። ግብፅን መውረራቸው ወይንም ብግብፅ ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት በማንኛውም መንገድ ጣልቃ መግባታቸው የማይቀር ጉዳይ ነው ። የአሜሪካ አስተዳደሮች አስተዳደር መፈንቅለ መንግስት በተደረገበት አገር ማንኛውንም አይነት እርዳታንም ሆነ ድጋፍን ማድረግ እንደሌለባቸው የአሜሪካ ኮንግሬስ ያወጣው አዋጅ በጥብቅ እንደሚከለክል ይታወቃል ። የኦባማ አስተዳደር  የግብፅ ወታደራዊ ሀይል በህዝብ በተመረጡት ሙሀመድ ሙርሲ ላይ የወሰደውን ከስልጣን የማስወገድን ድርጊት «መፈንቅለ መንግስት» ነው ወይስ አይደለም  ብዬ ለመፈረጅ አልገደድም በማለት ከግብፅ ጋር ያለውን ግንኙነት አላሻከረም ። ለግብፅ ይተላለፉ የነበሩ F-16 የተሰኙ እጅግ ዘመናዊ የሆኑ በአየር ላይ ነዳጅ መሙላት የሚችሉ እንዲሁም ከራዳር እይታ ተሰውረው ረጅም ርቀትን መጓዝ የሚችሉ የጦር ጀቶችን እንዳይተላለፉ ለጊዜው ከማገድ በስተቀር ሌላ ተፅእኖን አላሳረፈም ።

እ.ኤ.አ. በ1956 ዓ.ም. የወቅቱ የግብፅ ፕሬዝዳትንት ገማል አብደል ናስር የስዊዝ ካናልን ብሄራዊ ሀብት አድርገው ውርስ ባደረጉበት ወቅት አውሮፓውያን እንግሊዝና ፈረንሳይ ግብፅን መውረራቸው ይታወቃል። በወቅቱ በአይዘንሀወር ትመራ የነበረችው አሜሪካ ሁለቱን አውሮፓውያን ሀይሎችን በመቃወም ግብፅን ለቀው እንዲወጡ በመጠየቅ ጦርነቱን ማስቆማቸው ይታወቃል ።

የምእራባውያን መሪዎች ግብፅን እጅግ ስልታዊ ከመሆኗ አንፃርና የእስራኤል ጎረቤት በመሆኗና ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነትን የተፈራረመች ብቸኛዋ የአረብ አገር እንደመሆኗ በመካከለኛው ምስራቅ እንደ ዋነኛው አጋራቸው እንደሚመለከቷት ይታወቃል በመሆኑም በግብፅ ማኝም ይሁን ማ በስልጣን ላይ ያለው ከፋ ጫናን ለማሳረፍ የማይፈቅዱት በዚህ ምክንያት ነው ። ኤፍ 16 የጦር ጀቶች ለጊዜው ቢያዘገየውም የኦባማ አስተዳደር ለግብፅ በየአመቱ የሚሰጠውን የ1 ነጥብ አምስት ቢሊየን ዶላር በአብዛኛው ለወታደሩ የሚሰጠውን እርዳታ ማገዱን ግን ይፋ አላደረገም ።

በ2011 እና በ2012 የተቀጣጠለው (Arab Spring) የአረቡ አብዮት የሚፈለገውን ውጤት ማምጣቱን ለማየት ገና በርካታ አመታትን ይፈጃል ። በአረቡ አለም ዲሞክራሲ ሊሰፍን አይችልም የሚል ጨለምተኛ አስተሳሰብ ባይኖርም ከእስላሙ ዓለም ቱርክን ብንወስድ የተሻለ የዲሞክራሲ ደረጃ ላይ የደረሰች ሲሆን በዚህ አብዮት ከአምባገነን መሪዎቻቸው ገና መላቀቅ የጀመሩት ዓረቦች ቱርክ የደረሰችበት የዲሞክራሲ ደረጃ ላይ እንኳን ለመድረስ በርካታ አመታት ይፈጅባቸዋል ።

የአረብና የእስራአቼል የሰላም ድ3ርድር

እስራአቼ በክልሉ የ240 ቢሊየን ዶላር ኢኮኖሚን ስትገበቫ በሀገሪቱ ያለው የስራ አጥቀ ቂጥርትም ከ7 በመቶ በታችነብ ነው ። ከዚህ አየጠቃላይ አገራዎ ምርቷ ውስጥ 40 በመቶ የሚሆነው በቴጅኖሎጂ የፈጠራ ምርቶቿ የምታገኘው ገቢ ሲሆን ፣ የመካከለኛው ምስራቅ በከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር በሚታመስበት ወቅት እስራኤል በሶስተኛው አገር ያለች ያደገች አገር ያሰኛታል ። በጠላት በተከበበችበትና አብሯት ጎረቤቶቿ ለመነገድ ፈቃፈኛ ባልሆኑበት እን ዲሁም አብዛኞቹ እስራኤላውያን ገንዘባቸውን በሀገራቸው ይልቅ በውጭ ሀገራት ኢንቨስት በሚያደርጉብት ሁኔታ እስራኤል የዚህ አይነት ኢኮኖሚ መገንባቷ አስገራሚ እና አገሪቱ ያላትን እምቅ አቅም የሚያሳይ ነው ።

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s