ዲሞክራሲ በአብዮት ?

ዲሞክራሲ በአብዮት ሊመጣ ይችላል ወይንስ አይችልም ? በታሪክ እንደታየው ከፈረንሳይ አብዮት ብንጀምር የመጀመሪያው የምእራቡ አለም አብዮት በመባል የሚታወቀው የፈረንሳይ አብዮት ከአብዮቱ ማግስት የታዩት ጃካባውያንና በሮስፒየር የተመሩት ብዙ ደምን በማፍሰሳቸው እና በርካታ የንጉሳውያንና መሳፍንቶችን በጊሎቲን ያለ ፍርድ በመጨፍጨፍ ይታወቃል ። ከዚህ በኋላም ቢሆን ፈረንሳይ ሪፐብሊክ አልሆነችም ከዚያ ይልቅ ናፖሌዎን ቦናፓርቴ በአምባገነንነት ወደ ስልጣን ሲመጣ ፈረንሳይን ወደ ዘውዳዊ ስርአት ሲመልሳት በአውሮፓም እንደ ወታደራዊ ጂኒየስ በሚቆጠረው በናፖሌዎን ዘመን ማለቂያ የሌለው ጦርነት ሰበብም ሆኗል ። በሩስያም በዛሩ መንግስተ መጨረሻ ላይ ከኬረንስኪ መውደቅ በኋላ  ስልጣን ላይ የወጡት እነ ሌኒንና ትሮትስኪ በኋላ ላይም ስታሊን ሚሊዮኖችን ጭዳ ያደረገ የሶቭየት ህብረት ስርአትን ሊያጠናክረው በቅቷል ።

እንዲህና እንዲያ እያልን እስከ በሀያኛው ክፍለ ዘመን በሶሻሊዝም ስም የተካሄዱት አብዮቶች አላማቸውን በማሳካት ፈንታ የአምባገነኖች ወደ ስልጣን መምጫ ጥሩ ሰበብ ነው የሆኑት ። በቻይና በማኦ የተመሩት አብዮተኞች የኮሚኒስት ስርአትን ሲመሰርቱ ፣ የቀድሞው የሊቢያው መሪ ሙሀመድ ጋዳፊ ሳይቀሩ ወደ ስልጣን የመጣሁት በአብዮት ነው የሚል መከራከሪያን ሲያቀርቡ ይሰማሉ ። በሀገራችንም እንዲሁ የ66 ቱ አብዮት ለብዙዎች ህይወት መጥፋትና ለወታደራዊ መንግስት ወደ ስልጣን መምጣት ሰበብ ሆኗል – ዋነኛው ግቡንም በመሳት ሀገሪቱ በእርስ በእርስ ጦርንተ ውስጥ ስትዘፈቅ ወታደሩ ስልጣኑን አጠናክሮ ቁጭ ሊል በቅቷል ፣ እርሱንም ለማስወገድ አገሪቱ በእርስ እርስ ጦርነት ልትዘፈቅ በቅታለች ። አብዮቶች አስፈላጊ ቢሆኑም በጥቂት መጠለፋቸውና አላማቸውን መሳታቸው በታሪክ በተደጋጋሚ የታየ ክስተት ነው ። የአረቦችም አብዮት የሚፈለገውን የዲሞክራሲ ስርአት ማምጣት መቻሉ አጠራጣሪ ነው ። 

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s