የፖለቲካ ሳይንስ

ማን ይምራ ? ሲባል እንደ ጥንታዊ ግሪክ ታላላቅ ፈላስፎች አባባል አገርን መምራት የሚችለው ፣የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ፣ በልምድና በተሞክሮ የዳበሩ ሰዎች ናቸው አገርን ምመራት ያለባቸው ነው እሚሉት ጥንታዊ ግሪኮች ። ይህ ብቻ እንደ ጥንታዊ ግሪኮች አባባል ጥሩ መሪ ማለት መምራትን ብቻ ሳይሆን መመራትንም እሚያውቅ መሆን ይኖርበታል ይላሉ ። ይህም ማለት ሁልግዜም ብቸኛ መሪ ያልሆነ ፣ ባጠገቡ ካሉ ሰዎች ጋር የሚማከር ፣ የሌሎች ሰዎችን ሀሳብ እሚያዳምጥ ማለት ነው ። ይህ ህዝቡንም ይጨምራል ፣ ህዝቡን ፍላጎት ፣ ስሜትን መከተልም ሲኖርበት ፣ህዝቡ እማይፈልጋቸውን ወይም እማይስማማባቸውን ነገሮች በሚኖሩበት ወቅት የህዝቡን ፍላጎትን ጭምር ለመጠበቅ ፈቃደኝነትን ማሳየት አለበት የሚል አስተሳሰብ አላቸው ።

     ከጥንት ግሪካውያን ወዲህ በመካከለኛው ዘመን የነበረው የስዩመ – እግዝአብሄር የዘውዳዊ ስርአቶች በተለያዩ የአለም ክፍሎች የነበሩበት ሲሆን ። አንድ ፈላስፋ እንደገለፀው ስዩመ – እግዝአብሄር ማለት የእግዝአብሄርን ህግጋትንና ትእዛዛቱን በመፅሀፉ ውስጥ የተደነገጉትን ነገሮች በሙሉ ስዩመ – እግዝአብሄር መንግስት መከተል አለበት ። እዚህ ጋ ስዩመ – እግዝአብሄር ለማሳሳቻውም ተግባራዊ ሳያደርግ ለማስመሰል ሳይሆን ህግጋቱንናና ደንቦቹን ከልቡ የተቀበለ መሆን አለበት።

     ስዩመ – እግዝአብሄር ንጉስ ትልቅ ሀላፊነትን የተሸከመ እንደመሆኑ ትልቅ የሞራል ወይም የስነ – ምግባር ሸክም አለበት ። ሲነግስ ቤተሰቡ ከሰጠው ስም በተጨማሪ የንግስና ስምን ይሰጠዋል ። አሁን ሲነግሱ ስዩመ – እግዝአብሄር ስለሆነ ከሰው የተለየና ከሰዎች የበለጠ ፍርድንና ፍትህን መስጠት አለበት ።

     ወደ ዘመናዊ የመንግስት ስርአቶች ብንሄድ ስዩመ – ህዝብ ነው ። ይህም ፓርላማዊ ወይም ሪፐብሊክ ይሆናል ። ዲሞክራሲ የሚለው ቃል ዲሞክራቲያ ከተባለው ቃል የመጣ ሲሆን ዲሞክራሲ ከመልካም አስተዳደር የሰፋ ፅንሰ – ሀሳብ ነው ። መልካም አስተዳደር አንዱ የዲሞክራሲ መሰረት ነው ። መልካም አስተዳደር የአንድ ተቋም በትክክል መተዳደር ፣ ትክክለኛ አስተዳደር መኖር ማለት ነው ።  ዲሞክራሲ ከመልካም አስተዳደር ሰፋ ያለ ፅንሰ – ሀሳብ ሲሆን የዲሞክራሲም አንድ አካል ነው ።

ማክያቬሊ ዘመናዊ የፖለቲካ ሳይንስን መደላድል ፈጠረ ሰው ሲሆን ። እርሱም አዲስ የፖለቲካ አህጉርን ፈጠርኩ ነው እሚለው። ይሁን እንጂ የእርሱ ስራ ባለፉት 300 እና 400 በተለያዩ ሰዎች የተለያየ ትርጓሜ ሲሰጠው ኖሯል ። በዚህም ማክያቬሊዝም የሚባል የፍልስፍናና የአስተሳሰብ ዘውግ የተፈጠረ ሲሆን አልፎ አልፎም እርሱ ከራሱ አስተምህሮዎች የተለዩ ሀሳቦችንም ያያዘ ነው ።

ወደ ዋናው ሀሳብ ስንመጣ የራሱን አዲስ ሀሳብ ሲያዘጋጅ የቀደምት ግሪኮችን እንዲሁም በክርስትና ሀይማኖት ላይ የተመሰረተውን የመካከለኛውን ዘመን ፍልስፍናን በመተቸት ነው እሚነሳው ። እንደ እርሱ አስተሳሰብ ፈላስፋዎች የሰውን ልጅ ከጨለማ ወደ ብርሀን ለማውጣት ይፈልጋሉ ። ለምሳሌ የፕሌቶ የዋሻው ተምሳሌት ሀሳቡ የሰውን ልጅ ከጨለማው ዋሻ ወደ ብርሀኑ የማውጣት እና ብርሀነ – ህሊናን  (enlightenment) እንዲቀዳጅ የማድረግ አለማ ያለው ነው ። ይሁን እንጂ እንደ ማክያቬሊ አስተሳሰብ ደግሞ ወደ ብርጀኑ እምመራችሁ መሲህ ሳይሆን እንዴት የሰው ልጅ በዚህ ጨለማ በሆነ አለም ህልውናችሁን እንደምታስጠብቁ ፣ እና ይህንን የጨለማ አለም እንደምትቋቋሙት አሳያችኋለሁ ነው እሚለው ።   

ትልቁ የሱ ካበረከታቸው ሀሳቦች መሀከል ስነ – ምግባርን ወይም ሞራልን በተመለከተ ቀድሞ በነበረው አስተሳሰብ ላይ ያቀረበው ትችት ነው ። እንደ ማክያቬሊ አባባል ሁለት አይነት ስነ – ምግባሮች ወይም ሞራሎች ሲኖሩ አንደኛው በህዝብ ፊት የሚደረግ ስነ – ምግባር ሲሆን ይህም ፖለቲካዊ ስነ – ምግባርን ይጨምራል ። ሁለተኛው አይነት ስነ – ምግባር ደግሞ ግለሰባዊ የሆነ ስነ – ምግባር ሲሆን ፤ አንድ መሪ በስልጣን ላይ እሚመራው እሚዳኘው በፐብሊክ ሞራሊቲ ነው እንጂ በግለሰብ ሞራሊቲ አይደለም ።መሪው የሚጠየቅብበት ሞራሊቲና ግለሰብ የሚጠየቅበት ሞራላቲ ሉያያል ።

ሌላው ደግሞ ያለው የልሂቅ (elite) የሚባለው ህብረተሰብ ክፍል አስተሳሰብ ቀስ በቀስ ወደ ዋናው ህብረተሰብ እየሰረፀ በሄደ ቁጥር ያ መንግስት ሊናወጥ ወይም ሊፈራርስ ይችላል ። የዛን ሀሳብ ትክክለኛነት እየተረዳ በሚመጣው ተራው ህብረተሰብ ያ ሀሳብ ቦታን እያገኘ የበለጠ ጉልበት እየጨመረ ይሄዳል ። ይሄድና የዛ መንግስት ወይም ስረአት አደጋ ውስጥ ይወድቃል ።

የጥንቶቹ ግሪካውያን ፍልስፍና የሰው ልጅ ሄዶ ሄዶ የፖለቲካ ፀጋን (political virtue) ደረጃ ላይ ማድረስ ነው አላማው ወይም የመጨረሻው ግቡ ። በጥንት ግሪክ አባባል (man is a political animal) እናም ደስታውን ኑሮውን ሁሉንም ነገር እሚፈልገውም እሚያገኘውም (city state) ውስጥ ነው ። በነገራችን ላይ ይህ አስተሳሰብ ከምስራቃውያን የመንፈሳዊ እውቀት ጋራ በእጅጉ ይለያያል ። በምስራቃውያን አንድ ሰው ራሱን ማንቃት  በእውቀት መንጋቃት ደረጃ መድረስ ነው ዋናው አላማው መሆን ያለበት ። ቡድሂዝምን ብንወስድ ንቃት ከመንግስት ህልውና ጋር ምንም እሚያገናኘው ነገር የለም ።

በነገራችን ላይ የጥንቱን የግሪካውያንን ፍልስፍና በተለይም የፕሌቶን ፍልስፍና ከክርስትና ሀይማኖት ጋር ማስማማት ቀላል የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ የመጣውን የአሪስቲቶትልም ፍልስፍና ግን ከብዙ ጊዜያት በኋላ ነው ከክርስትና ሀይማኖት ጋራ ያስማሙት ። እሱ የሚለው እማይሆን አይነት ። (ideal) ላይ ትፈጥራላችሁ ሰውን በጎ (virtuous) ለማድረግ ትጥራላችሁ ነገር ግን ሰው ምን አይነት አስቸጋሪ እንደሆነ አልተረዳችሁም ፣ ሰው በትምህርት እና በምክር ብቻ ጥሩ አይሆንም የሀይል ዱላ ያስፈልጋል ነው እሚለው ።

ይህም (morality) ከ (immorality) ይመነጫል ፣ ፍትህም (Justice) ከኢ – ፍትሀዊነት (injustice) ይመነጫል ። አገር እሚመሰረተው ከወንጀል ነው ። ትልቅ ስልጣኔ የሚመሰረተው ትልቅ ወንጀል ተሰርቶ ነው ፣ በቀላሉ አይገኝም ፣ አልጋ ባልጋ አይሆንም የሚል ነው ።

Leave a comment