ሃሳባዊነትና ቁስ-አካላዊነት

ካርል ማርክስ የሀሳብን ሚና ዝቅ በማድግ የቁስ አካልን ሚና ከፍ በማድረጉ ምክንያት ታላቁ የፍልስፍና ክህደት በመባል ይታወቃል ፡፡ ከአለማችን ፈላስፎች ለምሳሌ ታላቁን ፕሌቶን ብንወስድ የሀሳብን ቀዳነሚነትን ያስቀደመ ሲሆን በዚህም እጅግ የሚደነቅበትና የክርትና ሀይማኖት ሳይቀር ከፕሌቶ ብዙ ሀሳቦችን ወስዷል እስከ መባል ደርሷል ፡፡ የማርክስ ፍልስፍና የወደቀበት ምክንያት የሰው ልጅን የራስ ወዳድነት ተፈጥሯዊ ባህሪን (Individualism) ባለመቀበሉ ፣
የካርል ማርክስ ሀሳብን የፍራንሲስ ፉኩያማ የታሪክ ፍፃሜ (The End of History) የሚለው አስተሳሰብ ሁለቱ ፅንፍና ፅንፍ ያሉ ሓሳቦች ናቸው ፡፡ በፉኩማያ አስተሳሰብ መሰረት የታሪክ ፍፃሜው የሚሆነውና ዓለም የምታመራው ወደ ሊበራል ዲሞክራሲ ስርአት ነው በአንፃሩ ለካርል ማርክስ ግን የታሪክ ሂደቱ ገና ያላበቃ ሲሆን የሚሄደውም ወደ ኮሚኒዝም ነው ፡፡ የሁለቱም አስተሳሰብ ግን የየራሱ ድክመቶች አሉበት ፍራንሲስ ፉኩያማ መጀመሪያ ያፈለቀውን ሃሳቡን ከዚያ በኋላ እያሻሻለ የመጣ ሲሆን በእርሱ አስተሳሰብ መሰረት የዓለም ታሪክ የሚያመራው ወደ ሊበራል ዲሞክራሲ ስርአት ሲሆን ይህም በርካታ የምእራባውያን የሚዲያ ጋዜጠኞች የሊበራሊዝም ስርአት ትክክለኛ ነው ለማለት የሚጠቅሱት ነው ፡፡
የሰው ልጅ እንደ አንድ ብቸኛ ዝርያ የሚቃለል አይደለም በአለም ላይ በርካታ አጥቢዎች ወፎች ፣ አሶች ፣ ተሳቢዎች ሳቢዎች ወዘተ… ቢሞሉም የሰው ልጅ ህሊና ስላለውና ህሊናዊ – ንቃትን ስለሚጎናፀፍ የተለየ ፍጡር ነው ፡፡ እንደ አንድ ተራ ዝርያ ወይ እንሰሳ የሚታይ አይደለም ሰው ፡፡
የካርል ማርክስ ኮሚኒዝም እጅግ የበዛ ተምኔታዊ ወይም ሃሳባዊነት (Utopia) ‹‹ዩቶፒያ›› የሚጎላበት እና ተግባራዊ ለመሆንም ከሰው ልጅ ባህሪና ተፈጥሮ አንፃር ብዙ መቃኘትን የሚሻ አስተሳሰብ ነው ፡፡ የመንፈስንም ሆነ የሃሳብን መሪነት ጨርሶ የማይቀበለው ማርክሲዝም ውድቀቱ ይሄው ቁስ አካልን ከሃሳብና ከመንፈስ ማስቀደሙ ሲሆን ሊበራሊዝምም ቢሆን ከላይ እንደሚታየው ሁሉንም ሰው ነፃነትን የሚያጎናፅፍ ይምሰል እንጂ ፣ በነፃነትና በሊበራሊዝም ስም ከልክ ያለፈ ነፃነትን በመስጠት የሰው ልጅ ተፈጥሮን አስከመገዳደር የሚደርሰው ይሄው የሊበራል ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው ፡፡
ማንም ሰው እንደሚረዳው ሁለት አይነት አለሞች እንዳሉ ነው እነሱም ፣ መንፈሳዊውና ቁሳዊው እንዲሁም የሚታየውና የማይታየው በመባል ይታወቃሉ ፡፡ ብዙውን ግዜ ሰዎች የሚታየውን ወይንም ቁሳዊው የሆነውን ዓለም በቀላሉ ሲረዱትን በዚህም ዓለም ውስጥ ስኬታማ ለመሆንና የሚያስፈልገን የሚሉትን ቁሳዊም ሆነ የገንዘብ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሲጥሩ ማየት የተለመደ ሲሆን ነገር ግን ከዚያም ባለፈ ሚስት ከማግባትና ልጅ ከመውለድ ፣ መኪና ከመግዛት ፣ ሀብት ከማፍራት ፣ ገንዘብ ከማከማቸት ፣ በስልጣን ላይ ስልጣን መደራረብ ፣ በትምህርትና በስራ ከመግፋት ባለፈ ስላለው ስለማይታየው ዓለም ለብዙ ሰዎች ግልፅ አይደለም ፡፡
ጠቢቡ ሰለሞን የመንፈስን ሃያልነትንና ምንም ነገር እንደማይገድበው ሲገልፅ በመፅሀፈ መክብብ ምእራፍ 8 ፣ቁጥር 8 ላይ ‹‹መንፈስን ለማስቀረት በመንፈስ ላይ ስልጣን ያለው ሰው የለም›› ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለወገኖቹ ለእብራውያን ባስተላለፈው መልእክት እብራውያን ምእራፍ 14 ፣ ቁ 1-3 ‹‹አለሞች በእግዝአብሄር ቃል እንደተዘጋጁ ፣ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታየው እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን›› የማይታየውን ነገር የተረዱ በእምነት 1 ቆሮ ምእራፍ 2 ፣ ቁጥር 14 ላይ ‹‹ለፍጥረታዊው ሰው የእግዝአብሄር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም ፣ በመንፈስም የሚመረምር ስለ ሆነ ሊያውቀው አይችልም ፡፡ መንፈሳዊው ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል ራሱ ግን በማንም አይመረመርም ››
ከሳይንሱም አንፃር ብንመለከት ማንኛውም ቁሳዊ የሆነ ነገር በጊዜና በቦታ የተገደበ ሲሆን ጊዜና ቦታ (ታይም ስፔስ) አጥረው የማይገድቡት ምንም አይነት ቁሳዊ የሆነ ነገር የለም ፡፡ ጊዜን ብንወስድ ቁሳዊ የሆነ ነገር እንዲያረጅና እንዲሰባበርና አንዲሞት ያደርገዋል ፣ ቦታንም ብንወስድ አንድ ቁሳዊ የሆነ ነገር ህልውና የሚኖረው በቦታ ውስጥ ሲሆን ቦታ ከሌለው ግን ነገርየው በየትኛው ቦታ መኖር ስለማይችል ህልውናው ይጠፋል ፡፡ይሁንና መንፈስ ቁሳዊ ከመሆን ጋር ግንኙነት የሌለው ነገር በመሆኑ በጊዜም ሆነ በቦታ አይገደብም ፡፡ ለዚህም ነው አንድ መንፈስ አማኞችና ተከታዮች ካሉት ሺህዎችን አመታት ለሚጠሩት ሰዎች እየተገለጠ የሚኖረው ፡፡
የዓለማችን ታላላቅ ሀይማኖት መስራቾች ራሳቸውን ከዓለም አግልለው ስለ ዓለም ብዙ ብዙ አስበዋል፣ ተጨንቀዋል ፡፡ ለዚህም አይነተኛ ምሳሌ የሚሆኑት እየሱስ ክርስቶስና ነቢዩ መሀመድ ሲሆኑ እየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከፆመና ከፀለየ በኋላ በዚያውም ሰይጣን ሲፈታተነውም ስለ ዓለም ነገስታት ክብርንና በማሳየት ሲሆን የዓለም ነገስታትን እሰጥሀለሁ ያለው ሲሆን ክርስቶስም ባለመቀበል መልሶለታል ይህም የሚያሳየው ሀይማኖት ዓላማው ከዚህ ምድር ካለው ማንኛውም ክብርና ሀብት በላይ መሆኑን ሲሆን ቡድሀንም ብንወስድ የንጉስ ልጅ የነበረና ልኡል የነበረ ሲሆን ያን ሁሉ ክብርንና ሀብትን ትቶ እንደመነነና ለ49 ቀናት እንደ በተመስጦ ውስጥ እንደቆየ ኒርቫናን (Nirvana) ወይንም አብርሆትን በመጎናፀፍ ዛሬ የዓለማችን አንዱና ታላቅ የሚባለውን ሀይማኖት እንደመሰረተ የታወቀ ነው ፡፡
ከሃገራችን ፈላስፎች ይህንን አብዝተው ያሰቡበት እጓላ ዮሃንስ ሳሆኑ አይቀሩም ፡፡
የሃሳብን ወይም የመንፈስን ቀዳሚነት መካድ ትልቁ ክህደት ሆኖ ተመዝግቧል ፡፡ የመንፈስን ቀዳሚነት መካድ የመንፈስን መሪነትን ማጣትን ያስከትላል የመንፈስንና የሃሳብን ቀዳሚነት አለመቀበል ፣ ይህም ክህደት ትልቅ ሽንፈትን አስከትሏል በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ፡፡ ለዚህ አይነተኛው ምሳሌ የሚሆነው ማርክሲዝም ሲሆን የመንፈስን ህልውናም ሆነ ከቁስ አካል በፊት የሀሳብን ቀዳሚነትን የካደው ማርክሲዝም አይሸነፉ ሽንፈትን ተሸንፎ በታሪክ አብቅቶለት ከመድረኩ ተወግዷል ፡፡ ይሁን እንጂ በአለም ታሪክ የአሁኑን ዘመንን ያህል መንፈሳዊነት ወይንም ሃይማኖታዊነት አስፈላጊ የሆነበት ዘመን የለም ይቻላል፡፡ ነገር ግን በአንፃሩ ወቅቱ ቁሳዊ ዘመን በመሆኑ ምክንያት መንፈሳዊነት የተዘነጋበትና ቦታ የማይሰጠው ዘመን ነው ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s