ሰውና ተፈጥሮው

‹‹ ማንም ሰው በሁሉም ጊዜ ጥሩ ለመሆን የሚሞክር ቁጥራቸው በርካታ በሆኑት ጥሩ ባልሆኑ ሰዎች ይገፈተራል ፤ ስለዚህ አንድ ስልጣኑን መጠበቅ የሚፈልግ መስፍን ጥሩ አለመሆንን መማር አለበት ፣ ይህንንም እውቀቱን ሁኔታው እንደሚጠይቀው መጠቀም ወይም አለመጠቀም ይኖርበታል ›› ፤
ይህ የማክያቬሊ አባባል በአጭሩ ሲገለፅ ‹‹ሁልግዜ ጥሩ የምትሆን ከሆነ የመጥፎ ሰዎች መጫወቻ ትሆናለህ ›› ማለቱ ነው ፡፡
ኒኮሎ ማክያቬሊ (መስፍኑ)
‹‹በእግራቸውም እንዳይረጋግጡት ፣ ተመልሰውም እንዳይነክሷችሁ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ፣ እንቁዎቻችሁንም በእርያዎች ፊት አትጣሉ፡፡ ››
(እየሱስ ክርስቶስ የማቲዎስ ወንጌል ም፣7፡ ቁጥር 6)
ከላይ በተቀመጡት በሁለቱ አባባል መሀከል ተመሳሳይነት እንዳለ ልብ ማለት ይቻላል ፡፡ የማክያቬሊ ፅንሰ ሃሳብ ቀድሞ ሰዎች ሁሉንም ነገር እግዝአብሄር እንዳለ ይሉ የነበረ ቢሆንም ይህን ከላይ ወደ ታች ማለትም ከእዝአብሄር ወደ ሰዎች የነበረን ግንኙነት በመለወጥ ሰዎች የራሳቸውን እጣ ፈንታ ራሳቸው መወሰን ወይንም ቅርፅ ማስያዝ ይችላሉ ፡፡ ከላይ ወደ ተች ታች (Vertical) የነበረውን ግንኙነት ማክያቬሊ ወደ ጎን (Horizontal) ዘረጋው ፡፡ ከእርሱ ቀድሞ ፖለቲካና ቤተክርስትያን በእጅጉ የተቆራኙና አንዱን ከአንዱ መለየት የማይቻልበትና ፖለቲካ ሃይማኖታዊ በሆኑ አስተሳሰቦች የሚመራና የሚቃኝ ነበረ ፡፡ ይህም ይህ ማ ዓለም ባለቤትና ሁሉን ያደረገ አንድ ላእላይ መንፈሳዊ ህላዌ (Being) አለው የተቀመጠ ህግና ስርአት አለው የሚለውን የፕሌቶን በኋላም የክርስትናን የሌሎችን ሃይማኖቶችን አስተሳሰብ የሚገዳደር ነው ፡፡
በማክያቬሊ አስተሳሰብ ግን ሀይማኖትና የተለያዩ ሲሆኑ ምድራዊ የሆነው ፖለቲካ ራሱን ከሀይማኖት መለየት አለበት የሚል አቋም አለው ፡፡ ሰው ራሱ በሚያርገው ማንኛውም ነገር የራሱን እጣ ፈንታ መወሰንና ቅርፅ ማስያዝ ይችላል የሚል ነው የማክያቬሊ ፍልስፍናዊ መርሁ ራሳቸው የኢጣሊያ ምሁራን የፖለቲካ ሳይንስ አባት ተደርጎ የሚቆጠረው ማክያቬሊ በታሪክ በፖለቲካው መስክ ያበረከተው ፍልስፍና ይሄው መሆኑን ይገልፃሉ ፡፡
ነገር ግን ማክያቬሊ በታሪክ እጅግ አወዛጋቢ ከሆነ ሰዎች አንዱ ሲሆን ፣ ዘ ካውንት ኦፍ ሞንቴ ክሪስቴ (The Count of Monte Cristie) በአማርኛ ‹‹እፎይታ›› ተብሎ የተተረጎመው አበጀ ጎሹ ያሳተመውና የተረጎመው መፅሀፍ ደራሲ ማለትም አሌክሳንደር ዱማስ በፃፈው ፅሁፍ ላይ ማክያቬሊ ዋና ገፀ ባህሪ አድርጎታል ተብሎ እሚታመነውን ቄሳር ቦርጂያን ‹‹ከአባቱ የባሰ እጅግ ስግብግብና ጨካን ነበረ›› ሲለው ህመም ባይጥለው ኖሮ እጅግ ስኬታማ ይሆን ነበረ ብሎ ማክያቬሊ የሚቆጭለት ይኸው በወጣትነቱ የሞተው መስፍን በዛን ዘመን ተበታትና የነበረችውን ጣሊያንን አንድ ያደርግ ነበረ የሚል ስሜት ስለነበረው ለመስፍኑ የበዛ አድናቆት እንደነበረው መገመት ይቻላል ፡፡ ነገር ግን ይህን ሰው ማክቬሊ የመስፍኑ መፅፍ ዋና ገጸ ባህሪ ማድረጉ ግን ማክያቬሊን ክፉኛ ያስተቸውንና በታሪክ አወዛጋቢ አድርጎት አልፏል ፡፡
መስፍኑ የተባለው መጽሀፍም የመጨረሻ ምእራፉ ጣሊያንን አንድ ሊያደርግ የሚመጣ ማንኛውም መስፍ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚመክር ነው ፡፡ ስለዚህ ማክያቬሊ ይህን መፅሀፍ የፃፈው የጣሊያንን አንድነት ለማስከበር ሊመጣ ይችላል ብሎ ለሚያምነው መሪ እንደ ምክር እንዲሆን ነው እንጂ ለወደፊቱ ዘመን ለሚመጣው የፖለቲካ ሳይንስን አዲስ አስተሳብን ፈር ለመቅደድ አይመስልም ፣ ነገር ግን በፃፈው በዚህ ወጣ ባለና ከዘመኑ እጅግ የቀደመና ያፈነገጠ መፅሀፍ ሰበብ ከሰው ተገልሎ፣ ከስራው ተባሮና ተግዞ በብቸኝነት በገጠር ርስቱ ቁጭ ብሎ የፃፈው ይሄው አስተሳሰቡ የዘመናዊው የፖለቲካ አስተዳደር መሰረታዊ ፍልስፍናን የሚወክል መፅሀፍ ሊወጣው በቅቷል፡፡
መፅሀፉ የአርትኦት ስራ ያልተሰራበትና በአንድ ሰው በመገለል ለብቻ ሁኖ ተጽፎ የተሰራጨ ነው ፡፡ ከጨረሰውም በኋላ አንዱን መታሰቢ ላደረገለት ሎሬንዞ ለተባለው ለሜዲቺ መስፍን የተቀሩትንም ጥቂት ኮፒዎችን ለጓደኞቹ ከበተነ በኋላ ሽልማትንና ወደ ስራው መመለስንና ምስጋናን የጠበቀው ማክያቬሊ ያልጠበቀውን ስድብንና ነቀፋን ሲያስተናግድ ከመገለልና ወደ የልኡላኑን ፊት ለማግኘት ሳይታደል በዚያው ብዙም ሳይቆይ ህይወቱ አልፏል ፡፡ የካቶሊኩ ፖፕ በተለይም አንድ አዲስ መስፍን የቀድሞውን መስፍን ቤተሰቡን ጭምር አብሮ ነው ማጥፋት ያለበት ማለቱን ክፉኛ ሲተቹት ፣ በዘመኑ የነበሩ የጣሊያን የፖለቲካ መሪዎችም መታሰቢያ የተደረገለት ሎሬንዞም ጭምር እምብዛም አልወደዱትም ፡፡
ከዚያ በኋላ የእርሱ ስራ በእንግሊዝና በፈረንሳይ ፀሀፍት እየተተረጎመ ለተቀረው አለም ሊተዋወቅ በቅቷል ፡፡ አሁን ከአለማችን አንድ መቶ ተፅእኖ አሳዳሪ ከሚባሉ መፅሀፍት ይሄው ‹‹መስፍኑ›› የተባለው መፅሀፍ ነው ፡፡
ለነገሩ እርሱ ሌሎች በርካታ ስራዎችንም የሰራ ሰው ሲሆን ለምሳሌ የፍሎሬንስን ሪፐብሊክ በተመለከተ ምን መምሰል እንዳለበት ፣ እንዲሁም ስለ ጦርነት ጥበብ የፃፋቸው ፅሁፎች በታሪክ ሁነኛ ስፍራ የሚሰጣቸው ናቸው ፡፡ በተለይም ስለ ፍሎሬንስ ሪፐብሊክ ፅሁፉ ለዘመናዊ የመንግስት አስተዳደርና ፣ ለህገመንግስት ቅርፅ ተፅእኖ አሳዳሪ ስራው ነው ፡፡ በኋላ ላይ ወደ አውሮፓ የመጡትና የፈላጭ ቆራጭ የዘውዳዊ ስርአትን በሪፐብሊካዊ አስተዳደር ለመተካት ለሚፈልኩ ወጣት ፖለቲከኞች የእርሱ ሪፐብሊክ ስራው መሰረት ተደርጎ ይቆጠራል በኋላ ላይም የሩስያ አብዮተኞች የእርሱን የሪፐብሊክ ፍልስፍና ወስደው ስራ ላይ አውለውታል ፡፡
በአሁኑ ዘመን ውድድር የከፋበት ዘመን የሆነው ነገር ግን ይህንን ዘመን ሊገልፅ የሚችለው የዝግመተ – ለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ነው ፡፡ አንድ አዞን ብንወስድ አድርጎ ትልቅ እስሚሆን ድረስ ትላልቆቹ አዞዎች በሚኖሩበት አካባቢ የማይገኝ ሲሆን ጥልቀት ወደ ሌላውና ትላልቆቹ ወደ ማያዘወትሩት አካባቢ ራሱን ያሸሻል ፡፡
በአሁኑ ወቅት በዝርያዎች መሀከል ያለው ውድድር ከፍተኛ ሲሆን በዝግመተ ለውጥ ንድፈ – ሃሳብ መሰረት አንድ ዝርያ በጣም ከተባዛ በኋላ እርስ በእርሱ የከፋ ውድድርን ማደግ ይጀምራል ፡፡ ቀድሞ ለምሳሌ የኒያንደርጋትታልና የሆሞ ሳፒያንስ (Neandertal Homo Sapians) ዝርያዎች የነበሩ ቢሆንም ኒያንደርታል በወረርሽኝ በሽታ ወይንም ከሆሞ ሳፒያንስ በመጣ ተፅእኖ እንደጠፋ ወይንም ምንነቱ በማይታወቅ ምክንያት እንደጠፋ ሳይንቲስቶች ይገምታሉ ፡፡ የአንጎላቸው መጠን ከአሁኑ የሰው ዘር ወይንም ከሆሞ ሳፒያንስ ያንስ የነበረውና ነገር ግን እንደ ሰው ቆመው ይራመዱ የነበሩትና በራሳቸው ቋንቋ ይግባቡ የነበሩትና ተወዳዳሪ የነበሩት የኒያንድርታል ዝርያዎች ጠፍተው በምትካቸው በሳይንሳዊ ስሙ ሆሞ ሳፒያን ወይንም ዘመነኛው የሰው ልጅ የዚህ ምድር ወራሽና ባለቤት ሊሆን በቅቷል ፡፡
በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ የአየር ንብረት ለውጥ በአገራት በተለይም በታዳጊ አገራት ላይ ከባድ ጉዳትን እያደረሰ የሚገኝበት ፣ ለክፍለ ዘመናት ህዝቦችንና ማህበረሰቦችን በሰላም አስተሳስሮ ያኖረው የሃይማኖት መፋለስ የሚታይት ፣ የእርሻ መሬት ወደ ከተማነት እየተቀየረ ያለበት ፣ ለምግብ ሰብል አመቺ የነበረ መሬት ወደ ጠፍ መሬትነት እየተቀየረ ያለበት እንዲሁም ወንዞችን ጨምሮ የውሀ አካላትና ውቅያኖሶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተበከሉ ያሉበትና ፣ የአለም ሙቀት መጨመር ለሰው ልጅ ካንሰርን ጨምሮ የበሽታ ስጋት የደቀነበት ፣ የአለም ሰሜናዊና ደቡባዊ ንቀፍ ክበባት በረዶ እየቀለጠ የሚገኝበትና የውሀ አካላትና ደሴቶች እየሰመጡ የሚገኙበት ዘመን ነው ፡፡
ስፒኖዛ መልካም እጅግ በጣም ጥቂት ስለሆነ መልካም ያልሆኑ ነገሮች ይበዛሉ ሲል ፣ መፅሀፍ ቅዱስም ‹‹የሰው ልብ እጅግ ክፉ ነው›› ይላል ፡፡
None of you is a believer, until what you love for yourself loves for your brother. Prophet Mohamed
በራስህ እንዲደረግ የማትፈልገውን በሌሎች ላይ እንዲደረግ አታድርግ የሚለው አባባል በበርካታ ሃይማኖቶችና ፍልስፍናዎች ውስጥ ያለ ነው ፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን ስለ ሰው ልጅ ሲናገር መፅሃፈ መክብብ ምእራፍ 6፣15 ላይ ‹‹ጻድቅ በጽድቁ ሲጠፋ ሃጥእም በክፋቱ እጅግ ዘመን ሲኖር ፣ ይህን ሁሉ ከንቱ በሆነ ዘመኔ አየሁ ፡፡ እጅግ ጻድቅ አትሁን ፣እጅግ ጠቢብም አትሁን ፣ እንዳትጠፋ ፡፡ እጅግ ክፉ አትሁን፣እልከኛም አትሁን ጊዜህ ሳይደርስ እንዳትሞት›› ላይ ይላል ፡፡ ብዙ ሰዎች አውነት ሊሆን የማይችለውን ነገር እውነት ነው ብለው ያምናሉ ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s