ሰይጣንንና ሃጢአት

ሰዎችን የሚሳስተው ሁለት ነው አንደኛው ራሱ ሰይጣን መንፈሱ ሲሆን ፣ ሌላኛው ግን መፈታተን ወይም ስጋ የሚባለው ነገር ነው ፡፡ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ሄዋን የተከለከለውን ፍሬ የበላችው እርቧት ወይም የሚበላ ሞልቶ በተረፈበት ገነት ውስጥ የምትበላው አጥታ ሳይሆን የሰይጣን መንፈስ ስላሳሳታት ነው፡፡ አለምነህ ፍልስፍን በሚለው መፅሀፉ ላይ የኢ – አማንያንን (Atheists) ሓሳብ በመውሰድ ሰይጣን የሚባል ነገር እንደሌለና የሰው ልጅ ውስጡ መሆኑን ይገልፃል ፡፡
‹‹ሰኮናህን ይነክስሃል አንተም ራስ ራሱን ትቀጠቅጣለህ››፤ተብሎ እግዝአብሄር እንደረገመው ሁሉ ፡፡
ሰዎች ሀጢአትን የሚሰሩበት ሁለት ምክንያቶች አሉ ፣ አንደኛው ለስጋው በማድላታቸው ወይንም ያንን ነገር ለማድረግ ሲፈታተናቸው ሲሆን ሌላኛው ግን በቀጥታ በራሱ በሰይጣን መንፈስ በመነዳት ወይንም በሰይጣን መንፈስ ቁጥጥር ስር በመሆን ነው ፡፡ ሰይጣን ራሱ የመፈታተን ውጤት ሲሆን ከእግዝአብሄር ጋር በስልጣንና በመፎካከሩና የበለጠ ሀይልንና ገናናነትን ለማግኘት በመሞከሩ ከሰማየ ሰማያት እንደተባረረ በቅዱሳን መፅሀፍት የተገለጸ ነው ፡፡
ሰይጣን እንደ መንፈስ ህልውና የለውም ብሎ መካድ በተዘዋዋሪ መንገድ እግዝአብሄርም የለም እንደማለት ነው ፡፡ ምክንያቱንም የእግዝአብሄር ተቃራኒና በተፃራሪው የቆመ ሰይጣን በመሆኑ ማንኛውም ነገር ተቃራኒ እንዳለው ሁሉ የእግዝአብሄርም ተቃራኒ ሰይጣን ነው ፣ የመልካም ተቃራኒ ክፉ ፣ የወንድ ተቃራኒ ሴት፣ የጥቁር ተቃራኒ ነጭ ወዘተ … እያለ መሄድ ማንኛውንም ነገር የምንመለከትበት ነው ፡፡ ነገር ግን የዚህ ክርክር ድክመት ምንድነው ቢባል አንድ ነው ይሄውም የአንድ ነገር ተመጣጣኝ ተቃራኒ ነገር ካለው ሰይጣንና እግዝአብሄር ተቃራኒ መሆናቸው አከራካሪ ባይሆንም ፣ ነገር ግን ሀይላቸው ግን ተመጣጣኝ ሊሆን አይችልም ፣ምክንያቱም አሸናፊው እና ሀያሉ እግዝአብሄር ስለሆነ ነው ፡፡ ስለዚህ ሰይጣንና እግዝአብሄር ተቃራኒ መሆናቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ተመጣጣኝ ሀይል እንደሌላቸው ግን አከራካሪ አይደለም ፡፡
እየሱስ ክስርቶስ ሲናገር ‹‹ገሀነም ለሰይጣንና ለመናፍስቱ ተዘጋጅቷል›› ሲኦል እንደሚባለው በእሳት የተሞላ አይደለም ለዚያም ምክንያቱ ሰይጣንም ሆነ አጃቢዎቹ መናፍስቶች ናቸው እንጂ የሚቃጠል ቁስ አካል አይደሉም ይልቅ ግን ሰይጣንና መናፍስቱ መንፈሶች እንደመሆናቸው ቁሳዊ ነገር ማጥፋት የሚችለው እሳት መንፈስን ሊያጠፋ አይችልም ፡፡ በዮሀንስ ራእይ ላይ ‹‹ይህም የእሳት ባህር ሁለተኛ ሞት ነው ፣ በህይወት መፅሀፍ ተፅፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባህር ውስጥ ተጣለ ›› ራእይ 20፣15 ‹‹መላእክት መጥተው ሃጢአተኞችን ከፃቃንም መሀከል ይለዩአቸዋል ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል ፣ በዚያ ጥርስ ማፋጨትና ልቅሶ ይሆናል ›› ማቴ 13፣49-50
ሃጢአት በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ‹‹ሀጢአት የምትሰራ ነፍስ ሁሉ እርስዋ ትሞታለች›› ህዝ 18፣4 ላይ ሲል ሮሜ 3፣23 ላይ ደግሞ ‹‹ሁሉ ሀጢአትን ሰርተዋል የእግዝአብሄር ክብር ጎድሎቸአቸዋል›› ፣ ‹‹የሀጢአት ደሞዝ የዘላለም ሞት
(በገሀነም መቃጠል) ነው›› ሮሜ 6፣23 ይላል ፡፡ ‹‹በሃጢአታችን ብንናዘዝ ሃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከአመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ፃድቅ ነው››
‹‹ከዓለም እንድታወጣቸው አለምንህንም ፣ እንድትጠብቃቸው እንጂ›› የዚህ አለም ገዢ በሆነው በሰይጣን በሚገዛ አለም ውስጥ የሰው ልጅ በዚህ ምድርር ላይ እስካለ ድረስ ማውጣት አይቻልም ፣ነገር ግን ጠብቃቸው ነው ያለው ፡፡
ዜኖ የጠርጣራዎች አባት በጥንት ግሪካውያን ‹‹ብልህ ሰዎች ከስሜት ነፃ መሆን አለባቸው ፣ ስሜት ማሳየት የለባቸውም የደስታም ሆነ የሀዘን ከደስታም ሆነ ከሀዘን አሳዛኙ ነገር ግን ፣ የዚህ አይነት ሰዎችም ቢሆኑ ራሳቸውን ለተፈጥሮ ህግ ማስገዛት ግዴታ አለባቸው – ያም እጣ ፈንታ ነው፡፡›› አለ ግን ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል ፡፡ የሃይማኖት ሰዎች እየሱስ ክርሰቶ በውሀ ላይ ሲራመድ እንዴት ለተፈጥሮ ህግ አልተገዛም ፣ በውሀ ላይ ሲሄድ ተኝቶ ነበረ ማእበል ጀልባዋን ሲያናጋት ፣ እረ ጌታ ሆይ እረ ጠፋን ሲሉት ለምን እምነት የላችሁም ብሎ ጠየቃቸው ፡፡ በመንፈስ ግን ሰዎች ምንም ገደብ የለባቸውም ነፃ ናቸው፡፡ ክርስቶስ ነፃነትን ከህመም ፣ ከማንኛውም እስራት ነፃ አውጥቶናል ፣ እረኛችን ነው አንፈራም ፡፡
እየሱስ ለድሆች ነው የመጣሁት ሲል በሃጢአት ለተዘፈቁና በሃጢአት ቀንበር ውስጥ ለታሰሩ እንጂ ለገንዘብ ድሆች ማለቱ ወይንም ሃብታሞችን በሚመለከት አልመጣሁም ማለቱ አይደለም ፡፡ ክርስትስ ወደዚህ ምድር በመጣበት ወቅት በርካታ ከስነ – ፣ምግባር ያፈነገጢ ድርጊቶች በዘመኑ በሮማውያን ቄሳሮች በምትገዛው እየሩሳሎምም ሆነ በሌች ግዛቶች የተንሰራፋ ነበረ ፡፡ በጎችን ያለጠባቂ ስለተመለከተ ነው ለእነኚህ በጎች የመጣው ፡፡ የድሆች ሰቆቃ ከምንድነው የመጣው ቢባል ከሰይጣን ፣ ከማህበረሰበና ከሃጢአት ነው ፡፡ አደንዛዥ እፅና አልኮሆል የሃጢአት ሰዎችን በባርነት የሚሰብር ሲሆን የሰዎችም ህይወቶችም ይበላሻሉ ፡፡
በምእራቡ አለም ሰዎች የሚያረጋጋ ስነ – ልቦናን የሚረጋጉ ፣ ድብርነትን የሚያባርሩ በሚልና በሌሎችም ስም በርካታ የመድሀኒቶች አይነቶች በሀኪሞች ለህመምተኞች ይታዘዛሉ ነገር ግን ዋናው የዚህ ሰበቡ የሰዎች መነጠል ይህም መነጠል መንፈሳዊ መነጠል (Spritual Alination) ሲሆን ይህም ከሃጢአትና ሰዎች በሃጢአት ከመዘፈቃቸው የሚመነጭ ነው ፡፡
ሰይጣን አንድ ራሱን የቻለ ሰው ነው ፡፡ ሰዎችን የሚማርክ እንደ ጦር እስረኛ ማርኮ የሚያስቀር ነው ፡፡ ሰይጣን በማታለል ፣ በዝሙት ፣ በመተት በመማረክ ሰዎችን ከፍትህ እንዲያፈነግጡ ሰብአዊነታቸውን ረስተው የውሸት ስብእናን እንዲላበሱ ያደርጋል ፤የጤና ፣የገንዘብ ችግሮች የማህረሰቡ መገለል ፣ ስነ – ልቦናዊ ቀውስ ፣ የምግብ እጥረት ፣ የጤና መቃወስ እንዲከተልና ከቤተሰብ ጀምሮ የማህበረሰብ መፈራረስንና ህልውናው አደጋ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል ፡፡
የዚህ ዓለም ገዢ ብሎ እየሱስ ክርስቶስ የጠራው ሰይጣን እየሡስ ክርቶስን ለማሳሳት በአንድ ገደል ጫፍ ላይ ወስዶ የዓለም ነገስታትን ክብር በማሳየት ‹‹ለኔ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› ሲል ፈትኖታል ፡፡ ሰይጣን የጋለ ምኞቱ በምድር ላይ ብቻም የተወሰነ አይደለም በኢያሳያስ 16፣ ቁጥር 12 ላይ
‹‹አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮኮብ ሆይ ፤እንዴት ከሰማይ ወደቅህ ! አህዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ ፣ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቆረጥህ ! አንተም በልብህ ፡-ወደ ሰማይ አርጋለሁ ፣ ዙፋኔንም ከእግዝአብሄር ክዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ፣ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ ፤ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ ፣በልኡልም እመሰላለሁ አልህ ፡፡ ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጉድጓድ ጥልቅ ትወርዳለህ ››
ነገር ግን ማንም ሰው ሁሉንም ክፋትንና መከራን በሰይጣን ማላከክ እንደማይችል መፅሃፍ ቅዱስ ራሱ ይናገራል ፡፡ ያእቆብ 1፣13 ላይ ‹‹በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው ፣ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የህይወትን አክሊል ይቀበላልና ፡፡ ማንም ሲፈተን ፡-በእግዝአብሄር እፈተናለሁ አይበል፡፡ እግዝአብሄር በክፉ አይፈትንምና እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል፡፡ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ሃጢአትን ትወልዳለች፣ሃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች ›› ይላል፡፡
የዪሀንስ ወንጌል ምእራፍ 8 ላይ ‹‹እናንተ ከአባታችሁ ከዲያቦሎስ ናችሁ እርሱ ያደረገውን ማድረግ ትፈልጋላችሁ››

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s