Christianity in history

ክርስትያኖች ስነ – ፅሁፍን ፣ ሳይንስን ሂሳብን በመሳሰለው ክርስትያኖች አረቦችን አግዘዋል ፡፡ ማንኛውም ስልጣኔ ከእርሱ ቀደም ከነበረ ስልጣኔ ላይ ተመስርቶ ነው እንጂ እንደ አዲስ መስሎ የሚቆመው ከእርሱ በፊት በነበረ ስልጣኔ ላይ በመመስረት ነው የሚመሰረተው፡፡ ክመንት አሌክሳንደር (Clement Alexander) በበኩሉ የግሪክ ፍልስፍና ግሪካውያንን ወደ ክርስትና ለማድረስ አግዟል:: የግሪክ ፈላስፎች እንደ ሀይማኖት የለሽ አይደሉም ፡፡ እነ ፕሌቶ በመንፈስ ቅዱስ መንፈስ ተመርቶ የተፈላሰፈው የተገለፀበት ነው እስከመባል ተደርሷል፡፡
አካላዊና ዝቅ አድርጎ ማየትና መንፈሳዊውን እጅግ አግዝፎ ማየት አሁን ላለንበት ግዴለሽ እንድትሆን ፣ በዚህም ምክንያት ከምርምርና ከጥናትና ከሳይንስ እንድትርቅ ሲያደርግ ከዚህ አንፃር በጣም የጨለማ ዘመን ከሮማውያን ስልጣኔ መውደቅ በኋላ እስከ 11ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ነበረ ፡፡ የነበረውም ትምህርት እጅግ አነስተኛ ነው ፡፡ በዚህ ግዜ በአንፃሩ የእስልምናው ዘርፍ ሊነሳ በቅቷል አረቦች በፍልስፍና ፣ በሳይንስ ፣ በሀሳብ ለአረቡ ዓለም እሚታወቅበት ዘመን ሊሆን በቅቷል፡፡ አውሮፓ በጭለማው ዘመን በሚገኝበት ዘመን መሆኑ ነው ፡፡ ከ11ኛው ክፍል ዘመን በኋላ ግን አውሮፓ መረጋጋትና የትምህርት ተቋማት መቋቋም ሲጀምሩ የመፅሀፍ ቅዱስ ምሁራን መፈጠር ሲጀምሩ በስነ – መለኮት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጣቸው ምሁራን ሊፈጠሩ በቅተዋል ፡፡
አውሮፓውያን በስፔን አማካይነት ከአረቦች ጋር መገናኘት መጀመራቸው ጠፍተው የነበሩና የት እንደገቡ የማይታወቁ የነበሩ በተለይም የጥንታዊ ግሪክ ፈላስፋ ስራዎችን ከአረቦች ማግኘት ችለዋል ፡፡ በሰሜን አውሮፓ ተደብቀው የነበሩ የግሪክ ፈላስፎች ስራዎችም ተገኝተው በቅተዋል ፡፡ በ12ኛው ክፍለ ዘመን የአሪስቶትል ስራ መገኘት ፡፡ አሪስቶትል እውነትን በመመርመር በማጥናት የሚገኝ ነው ማለቱ ከፕሌቶ በተቃራኒው ፕሌቶ ዋናው ሰማያዊው ነው የሚለውን የፕሌቶን አቋም ፈትኗል ፡፡ ቶማስ አኳዬንስ የአሪስቶትልን ስራዎችን በመውሰድ አዳብሮታል፡፡ አመክንዮ ስለ ፍጥረታዊው ዓለም ፡፡
ኮንሲታንቶንፕል በኦቶማን እጅ መውደቅ የግሪክ ወደ ፈላስፎች ወደ ምእራብ አውሮፓ እንዲፈልሱና እውቀታቸውን ይዘው ወደ አውሮፓ እንዲፈልሱ አግዟል ፡፡ ኤራስመስ ኦፍ ሮተርዳም የተባለው የግሪክ መፅሀፍ ቅዱስ መተርጎም እና የአውሮፓ ወደ ሬኔሳንስ ዘመን ማበብና መፍለቅ ነው ፡፡
በዚህም ግን ስነ መለኮት አል ተብሎ መሄድም ነበረ በተለይም ሂውማኒዝም የሚባለው አስተሳሰብ ከስነ – መለኮት ጋር የተፋታ ነበረ ይሄም አንድ የሀይማኖት ፈተና ሆኖ ከዚያን ዘመን ጀምሮ ቀጥሏል ፡፡
ከተሃድሶ ወይንም ‹‹ከሪፎርሜሽን›› ጋር ተያይዞ የመጣው በሰሜን አውሮፓ የመጣውና ነፃነትና ለምርምር ሰፊ ነፃትን በመስጠቱ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ግስጋሴ በርን ከፍተዋል ፡፡ ነገር ግን ሂውማዝም በሳይንስና በአዳዲስ ግኝቶቹ አማካይነት በመደገፍ ጉልበት እያገኘ ሲሄድ ስነ – መለኮትን መዋጥና መገዳደር ከጀመረ ወዲህ በአውሮፓውያን አእምሮ ውስጥ እግዝአብሄር ምንም ጣልቃ የማይገባት ዝግ የሆነ ዓለም አድርጎ ወደ ማሰብ እንዲሄድ አድርጓል ፡፡
ኢማኑኤል ካንት ያሉት በአመክንዮ መመራት አለብን አመክንዮ ፊት ተፈትሾ ያላለቀ ነገር ተቀባይነት እንዳይኖረው አመክንዮ ፊት ቀዳሚ የሆነበትና እግዝአብሄርን አንፈልግም እስከማለት ተደርሷል ፡፡ በ17ኛው እና በ18ኛው ክፍል ዘመናት ተአምራትና ፈውሶች ሁሉ ተቀባይታቸውን እዲያጡና ፡፡
ብሎም ከትምህርት ሰርአቱም ጭምር በመገፋት የትምህርት ሁሉ ንግስት ነው የሚባለው የስነ – መለኮት ትምህርት አንድ ፀሀፊ የስነ – መለኮት ትምህርት በስደት ላይ ነች እስኪል ድረስ ስነ – ለመለኮት እጅጉን እየተገፋ መጣ ፡፡ በስደት ላይ ያለውን ስነ – መለኮት ትምህርት ሊሆን በቅቷል ፡፡
የዳርዊን ዝግመተ ለውጥ ፅንሰ – ሃሳብ ደግሞ እግዝአብሄር የለም እስከመባል የተደረሰበት ነው፡፡ ስነ መለኮት በዘመናዊው ትምህርት ውስጥ በዘመናዊው ትምህርት ምንም ቦታ የሌለውና ተደርጎ ተወስዷል ፡፡
መፅሀፍ ቅዱስ ከአይሁዳውያን ለአለም ካላቸው እይታ አንፃር መፃፉ እርግጥ ነው ለምሳሌ በዮሀንስ ራእይ ላይ አረቦች ሩስያን በማሰለፍ ከቻይና ጋር ሆነው እየሩሳሌምን ለመያዝ እስራኤል ላይ ወረራን ያደርጋሉ የሚለው ትንታኑ ይን አይሁን ለማወቅ አወዛጋቢ ነው ፡፡ ይሁን እንጂ በዋነኝነት መፅሀፍ ቅዱስ የመንፈሳዊ መፅሀፍ መሆኑና የታሪክ መፅሀፍነቱ ሁለተኛ እንጂ መጀመሪያ አለመሆኑ ግልፅ ነው ፣ አንዳንድ አይሁዳውያን ራሳቸው መፅሀፍ ቅዱስን ጊዜ ያለፈበትና እንደ ታሪክ መፅሀፍ ሊቆጠር ይችላል ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን መንፈሳዊ መፅሀፍ እንደመሆኑ መጠን ግን መንፈሳዊ መፅሀፍነቱን ሊያጣ እንደማይችል ግልፅ ነው ፡፡
በብሉይ ኪዳን መፅሀፍ ‹‹ሙሴ በቤተመንግስት የግብፃያውያንን ጥበብ እየተማረ አደገ›› የሚል ሲሆን ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ግን ሁሉንም የእግዝአብሄርን ጥበብ አይሁዳውያን በእንዳፈለቁትና እንደደረሱበት አድርገው ፅፈውታል ፡፡
ብሌይዝ ፓስካል በበኩሉ መፅሀፍ ቅዱስን አትናቁት ይላል ፡፡
እግዝአብሄር ዋናው ማእከሉ ነው ፡፡ እንጂ የሰው ተግባር እግርዝአብሄርን ማሞገስና ማወደስ ነው ፡፡ የግል ፣ ሃገራዊ፣ አለምአቀፋዊ ፣ ማህበረሰባዊ እና የቤተሰብ ችግሮች ማንም ሰው በህይወቱ ውስጥ የሚያጋጥሙት የችግር አይነቶች ናቸው ፡፡ እግዝአብሄር እስረኤላውያንን ከግብጽ ባርነት ቀንበር እንዳዳናቸው ለሚምኑት ለፍጥረቶቹ መድህን አዳኝ ነው ፡፡
እግዝአብሄር የእስራኤላውያንን አዳኝ ነው ፡፡ ባርያን ከቀንበሩ ማላቀቅ የማዳን ስራ ነው፡፡ ክርስቶስ ከሰይጣን ፣ ከሀጢአት ያዳነን ነው ፡፡ ድህነት የእግዝአብሄር ስራ ነው ፡፡ እግዝአብሄር ዓለሙን የወደደ እንደመሆኑ ድህነትን ለፍጡራኑ ያበረክታል ፡፡
‹‹ሀብትህ ባለበት ገንዘብህ ባለበት ልብህ አለ›› ክርስቶስ ‹‹ልብህ የሚሆነው መዝገብጀህ ባለበት ጥሪትህ ባለበት በዚያ ነው››

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s