Ethiopia & Climate Change

የአየር ንብረት ለውጥና መዘዙ (Climate Change)
የአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ የሆነ ዓለማአቀፋዊ ችግር ከሆነ ውሎ አድሯል ፡፡ በአርክቲክ እና በግሪንላንድ በአንታርቲክ አካባቢ የሚገኘው ግዙፍ የበርዶ ግርግር መቅለጥ ለባህር እና ለውቅያኖችሶች ቁመት ከፍታ መጨመርና ለትናንሽ ደሴቶች መዋጥ ፣ ለባህር ጠረፎች በውሀ መጥለቅለቅ ሰበብ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ ትናንሽ ደሴቶችና በባህር ዳር የሚገኙ የአፍሪካ አገራትና ደሃ ሀገራት ከባዱ ጉዳት የሚያገኛቸው ይሆናሉ ተብሎ ይሰጋል ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ በአገራት ምጣኔ ሀብት ላይ ጉልህና የሚታይ ጉዳትን ማስከተል ይጀምራል ፡፡ ደሃ ሀገራት በየአመቱ በአየር ንብረት ለውጥ መነሻ በየአመቱ በመቶዎች ቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር ኪሳራ ያጋጥማቸዋል ተብሎ ይሰጋል ፡፡
የአለም የምጣኔ ሀብት ስርአት በውድድር ላይ የተመሰረተ ነው ፡፡ ለተፈጥሮ ሀብት፣ ለገበያ ለመሳሰለው ውድድር የተሞላበት ስሆነ ለሆነ ለተወዳዳሪዬ የበላይትን ይሰጣል በሚል ነው ፡፡ ግዙፎቹ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በአጭር ጊዜ ብዙ ትርፍን ቢዝቁም ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ከመንግስታቱም ጭምር የበለጠ አቅም ቢኖራውም ከእነርሱ በኩል ግን የተሰማ ነገር የለም ፡፡
የተባበሩት መንግስታት በ2014 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ድርጅት የአየር ንብረትን በተመለከተ ምንም ካልተደረገ ጫፉ ላይ ደርሰናል ብሏል ፡፡ ቻይና ቀድሞ ከነበራት ግትርነት በመላቀቅ ታርጌቶችን በማስቀመጥ መንቀሳቀስ መጀመሯ አንድ ለውጥ ሲሆን ራሺያ፣ ብራዚል፣ ህንድና አውስትራሊያና ታርጌት ለማስቀመጥ ፈቃደኞች አይደሉም ፡፡ እኛ በቅርቡ ነው አየር ንብረትን በመከል የጀመርነው ስለዚህ አይመለከተንም የሚሉ የአሁኖቹ እነኚህ በጉልመሳ ላይ የሚገኙ (Emerging) አገራት በተወሰነ ደረጃ እውነት ቢኖራቸውም ፡፡
ለምሳሌ በቻይና ለአየር ንብረት ብክለት ግማሹ ምክንያት የድንጋይ ከሰል ጥቅም ላይ በመዋሉ ምክንያት ነው ፡፡ የድንጋይ ከሰል በወደፊቱ የኢኮኖሚ ዓለም ውስጥ ቦታ እስካለው ድረስ በአየር ንብረት ላይ በካይ መሆኑ ይቀጥላል ፡፡
እንደ ፔሩ ያሉ የላቲን አሜሪካ አገራት በዚህ የሚጎዱ ሲሆን ያላት የአማዞን ደን በከሰል ማክሰል ህገ ወጥ ደን ጭፍጨፋ ደኗን እያጣች ያለችው ይህችው አገር በአለም በሚሊየን ዶላር ህገ – ወጥ ደን ጭፍጨፋን ለመከላከል ወጪ የፔሩን ደን ከጭፍጨፋ ሊያድን አልቻለም ፡፡
በፔሩ በተደረገው ስነ ዓለም ዓቀፍ አየር ንብረትን በተመለከተ በተደረገው ስብሰባ ላይ ለአለም የአካባቢ ሙቀት መጨመር ተጠያቂዎቹ በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሃብታም አገራት ነው በሚለው ትችት የተማረሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንዳሉት ‹‹በአሁኑ ወቅት በአለም ላለው የአየር ንብረት ብክለት ከግማሽ በላይ ተጠያቂዎቹ ታዳጊ አገራት ናቸው›› ብለዋል፡፡
የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውክሊየር ሱናሚ የሰውን ልጅ የተራቀቀ ቴክሎጂ ባለቤት የመሆንን ተቃርኖአዊ ውጤትን ያሳየ ሆኖ አልፏል ፡፡ ምንም እንኳን የፉኩሺማ ዳይቺ የኒውከሊየር የሃይል ማመንጫ በጃፓናውያን የተሳራና እጅግ የተራቀቀ ቢሆንም የሰው ልጅ ሊረዳውም ሆነ ሊቋቋመው በማይችለው ሱናሚ ባልተጠበቀ ወቅት በሚመታበት ወቅት ምን ማድረግ እንዳለበት ሰው ሊያውቅና ሊዘጋጅም ባለመቻሉ የደረሰው ውድመት ከባድ ነው ፡፡ የዚህ አይነት ሰው ከሳው ከተራቀቀ ቴክኖሎጂ ጋር አደጋን የሚፈጥሩ ነገሪች ከኒውክሊየር ጦርነት ባልተናነሰ ሁኔታ በአየት ንብረት ሆነ በራ በሰው ልጅ ህልውና ላይ አደጋም ሊጋርጡ የሚችሉ ናቸው፡፡ የአየር ንብረት ለውጥም እንዲሁ በራሱ በሰው ልጅ በተራቀቀ ቴክኖሎጂ በሰራው ስራ ሲሆን ነገር ግን የሰውን ለጅም ሆነ የህይወት ያላቸውን ፍጥረታት ህልውና በመገዳደር ላይ ይገኛል ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s