Gorfu Contra Nietzsche

ኒች ዛርቱስትራን የፃፈው በዘረኝነት በመሳሳት መሆኑ አጠያያቂ ነው በእርግጥ ሶቅራጥስን አፍንጫው ደፍጣጣ ፣ መላጣ እና ከአውሮፓዊነት ይልቅ አፍሪካዊ መልክ እንዳለው ታሪኩ የተፃፈ ሲሆን ይህም ዘረኝነትን ማለትም ኒች ሶቅራጥስን ሲያቃልለው መልኩን በመመልከት ይህ ሰው አውሮፓዊ ወይንም ግሪካዊ ሳይሆን አፍሪካዊ ነው በሚል ነው ፡፡ ለዚህም የኒቼን ታሪክ የፃፉ ሰዎች እንደሚስማሙበት ኒች ዘረኝት የሚነካካው ሰው እንዳልነበረና ከራ ጀርመናዊያንን ይልቅ ፈረንሳውያንን ይበልጥ ያደንቅ የነበረ ሰው እንደነበረና በዘመኑ በጀርመን አገር ተንሰራፍቶ ከነበረው የፀረ – ሴማዊነትንም ፈፅሞ የማይካካው ሰው እንደነበረ ስለ እርሱ የተፃፉ ድርሳናት ያመለክታሉ ፡፡ በራሱ ወገኖች በሆኑ ጀርመናዊውያን ፀረ – ሴማዊነት ከት ብሎ ይስቅ እንደበረ ባገሩ ሰዎች ከንቱ ዘረንነኝነት የሚስቅ ሰው ችአ እንደነበረ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት ፡፡
የኒችን ስራ ከሳይንስ አንፃር ለመመርመር መነሳት ወደ መስመሩን ወደ መሳት ሊያመራ ሲችል ፣ ምክንያቱም ይሄ ዛርቱስትራ (Thus Spoke Zarathustra) ይናገራል የሚለው የኒች ስራ ላይ ዛርቱስትራ እንደ እየሱስ ክርስቶስ በአዲስ ኪዳን እንደሚናገረው ቃና ነው የሚናገረው ፡፡ ይህ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው እንጂ ሳይንስን ወይንም የምናልባት ንድፈ – ሓሳብን (Probability Theory) ፣ የአቶሚክ ፊዚክስን በመጠቀም ለማብራራት ፣መነሳት ሀይማኖትን በሳይንስ አመክንዮ ለመርታት እንደ መነሳት እና ወደ ግዙፉና መሰረታዊ ወደ ሆነው የሳይንስና የሀይማኖት ክርክር የሚመራ ነው ፡፡ በሳይንስና ሀይማኖት ክፍለ ዘመናትን ባስቆጠረው ክርክር ውስጥ አንዱ የአንዱን አመክንዮ እንደማይቀበለው የታወቀ ሲሆን ሳይንስ ሀይማኖት የሚያምንበትን ራእይ ፣ መገለጥን ፣ ተአምራትና ገድሎችንና ፈውስን ሳይንስ ፈፅሞ የማይቀበላቸው ሲሆን በአንፃሩም ሀይማኖት በበኩሉ የኢ – አማንያን (Atheists) መሰረታዊ ንድፈ ሃሳብ የሆነውን የሳይንስን ዝግመተ – ለውጥ ወይንም (Evolution) ‹ኢቮሉሽን›ን ፣ ወይንም የቁስ አካላዊ ፍልስፍናንና ንፅርዮተ – ዓለምን ‹‹World View›› ወይም ‹‹ወርልድ ቪው› ፈፅሞ እንደማይቀበላቸው የታወቀ ነው ፡፡ ስለዚህ ሁለቱ ማለትም ሀይማኖትን ሳይንስ የሚጠቀሙባቸው መሰረታዊ አስተሳሰቦች ሃራምባና ቆቦ ስለሆኑ ሁለቱን ማስታረቅ አስቸጋሪ ሲሆን በዘመናትም መራራቃቸው እየሰፋ ነው የሄደው ፡፡
በእርግጥ ሀይማትኖት የሳይንስን አንዳንድ የተቀበላቸው አስተሳሰቦች አሉ ፣ ለምሳሌ ጋሊሊዮ ጋሊሊን በዘመኑ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ብታወግዘውም ከብዙ ክፍለ ዘመናት በኋላ ግን ከቤተርስትያን አስተምህሮ ጋር ግጭትን እንደማይፈጥር በመረዳት ለጋሊሊዮ ስራ እውቅናን ሰጥታዋለች ፡፡ በኋላም ላይ ስለ ጠፈር ምርምር እንዲሁ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እውቅናን ስትሰጥ ሃይማኖት በተወሰነ መልኩ ሳይንስ ከሀይማኖት አስተምህሮ ጋር ግጭት እንደሌለው በመረዳት የሀይማኖት ሰዎች ለሳይንስ ክርክር ማድመጥና ምላሽን መስጠት ጀምረዋል ፡፡ ይሁን እንጂ ሀይማኖት እና ሳይንስ ተቀራርበዋል ፣ ታርቀዋል ማለት አይደለም ፡፡ በመሰረቱ ሳይንስ ከሀይማኖት አንፃር በጣም እንጭጭና ጨቅላ ነው ፣ ነገር ግን ብዙዎቹ ሳይንቲስቶች ይህንን ለማመንም ሆነ ለማወቅ ዝግጁ አይደሉም ፡፡
የአንፃራዊ ንድፈ ሃሳብን አልበርት አንስታይን ሲያቀርብ አንዷ የዚህን ንድፈ ሀሳብ ተቃዋሚ የነበረችው የካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ስትሆን ፖፑም አንስታይንን ተችተውታል ታላቁ ፈላስፋ ኒቼ ከአልበርት አንስታይን የአንፃራዊነትን ንድፈ ሃሳብ ከማግኘቱ በፊት በፃፋቸው ፅሁፍ ላይ ‹‹No Truths ፣Only Interpretations›› የሚል አባባልን የተጠቀመ ሲሆን ይህም ‹‹እውነት የሚባል ነገር የለም ፣ የእውነት ትርጓሜዎች እንጂ›› ሲል ይህም እውነት በተለያየ መንገድ ከተለያየ ማእዘን በአንፃራዊነት በበርካታ እርስ በእርሳቸው በማይመሳሰሉ ትርጓሜዎች ሊሰጣት ይችላል – እዚህ ላይ ኒችና አንስታይን ይስማማሉ ማለት ነው ፡፡

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s