Advertisements

የወሲብ ስሜትን «በማፈን» የተገኘው ስልጣኔ

ሲግመን ፍሮይድ ይህ የሠው ልጅ ስልጣኔ የሰው ልጅ «የወሲብ ስሜቱን በማፈን ያገኘው ነው» ሲል እንዲሁም ፍሬደሪክ ኒችም ይህ ስልጣኔ «ራስን በማሰቃየት የተገኘ ነው» ሲል ገልጿል ። ለዚህ የኒች አባባል ማስረጃ የሚሆነው ማርክስ «ዳዝ ካፒታል» በተሰኘው መፅሀፉ በዝርዝር እንደገለፀው ካፒታሊዝም ስርአት በመጀመሪያው የእድገት ዘመኑ እጅግ አነስተኛ ደሞዝ እና በጣም አስቸጋሪ በሆነ የስራ ሁኔታ የሰራተኞችን ብሎም የህፃናትን ጉልበት ጭምር ያለ ምህረት ይበዘብዝ ፣ እንደነበረ ይገልፃል ።

የወሲብ ስሜት ልክ እንደ ማንኛውም እንሰሰሳ ለሰው ልጅም ራሱን እንዲራባና ዘሩን ተክቶ እንዲያልፍ የሚያስችል ነው ። ብዙውን ግዜ ታላላቅ ሀይማኖቶች ሰው ራሱን እንዲገዛ ከሚያስተምሩባቸው ምክንያቶች በአንድ በኩል የሰው ልጅ የወሲብ ስሜቱን ካልተቆጣጠረ ወደ ሌላ አላማ ሊውል የሚችል እምቅ ሀይሉን ያዳክማል ፣ በሌላ በኩል ግብረ-ገባዊ የሆነና ስርአትና ወግን የተከተለ ማህበረሰብን ለመፍጠር አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል ። በምእራቡ አለም አንድ የፖለቲካ ሰው ከሚስቱ ውጪ ከማገጠ እና በማስረጃ ከተረጋገጠ የፖለቲካ ህይወቱ ያበቃለታል ። የወሲብ ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው ለከፍተኛ የሀላፊነት ደረጃ አይታጭም ማለት ይሆን ?

የወሲብ ስሜት በሁለት እርስ በራሳቸው ተቃራኒ በሆኑ አቅጣጫዎች የሚመራ ነው፣ አንደኛው የወሲብ ስሜት ሀይል ሲሆን ፣ በአለም ላይ ከፍተኛ ስኬትን የሚቀዳጁ ሰዎች ከፍተኛ የወሲብ ስሜት ያላቸው ሰዎች ናቸው ። አንዳንዶቹ እንደ ኒውተን ያሉት ደግሞ በድንግልና ኖረው የሞቱ ናቸው ። በተቃራኒው የወሲብ ሰሜት ካልተገራና ወደ ሌላ ጠቃሚ ወደ ሆነ ነገር ካልተለወጠ በስተቀር ፣ የሕይወት ብክነትን ይፈጥራል ።

የወሲብ ስሜት እንደ ማንኛውም እንሰሳ ለሰው ልጅ የተሰጠው ራሱን እንዲያራባበት ነው ። ይህም ማለት የወሲብ ስሜት አንድ እምቅ ሀይል ነው ። ይህ ሀይል አለልክ ሲባክን የዛን ሰው የህይወት ግብ ያመክናል ። ሲታፈን ደግሞ እንዲሁ የተቆጣና የተናደደ ሰውን ይፈጥራል ። ናፖሌዎቸን ሂል የተባለው ፀሀፊ እንዳስቀመጠው «አንድ ሰው ከአርባ አመቱ በፊት ስኬታማ አይሆንም» ፣ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ እድሜው በፊት የወሲብ ስሜቱን መቆጣጠር ስለማይችል ነው ።

በዝግመተ-ለውጥ አስተሳሰብ መሰረት አንድ ሰው ወጣትና ለተቃራኒ ፆታ መስህብ የሚኖረው በወጣትነቱ ዘመን ብቻ ነው – ይህም ለመራባት አንዲያስችለው ነው ። የወጣትነቱ ዘመን ሲያልፍ ተፈጥሮ እንሰሳው ወይም ተክሉ ራሱን አንደተካ በማመን ለእርሱ እምትሰጠውን እንክብካቤ ማለትም ወጣትነቱንና ሀይሉን ውበ አማላይ አካላዊ ገፅታውንና ጥንካሬውን በአጠቃላይ የአንድ ሰው ትልቁ ፀጋ እሚባለውን ወጣትነቱን ቀስ በቀስ ትወስድበታለች ። ከዚያም እያረጀ ፣ እያረጀ ይሄድና ወደ ተፍፃሜ-ህይወቱ ማለትም ወደ ሞት ያዘግማል ።

የህይወት ሚስጥር ?

ብዙ ሰዎች የህይወትን ሚስጥር ለማወቅ ይጥራሉ ። ህይወት የተገለጠች መፅሀፍ ነች «Life is an Open Secret » ። ህይወት «የተገለጠች» መፅሀፍ ብትሆንም ሊያነቧትና ሊደረዷት የሚችሉት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው ። በዚህች ምድር ከተፈጠሩ እጅግ ታላላቅ ሰዎች አንዱ የሆነው ቡድሀ ፣ የደረሰበትን እውቀት ለሰዎች እንዲያስተምር ተከታዮቹ ሲገፋፉት የሰጠው መልስ ባስተምርስ ማን ይረዳኛል የሚል ነበረ ። ተከታዮቹም መልሰው ጥቂት ሰዎችም ቢሆኑ የሚረዱህ ጥቂቶች አሉ ብለው ነበረ እንዲያስተምር ሊያሳምኑት የበቁት ።

ከቅዱሳን አስተምህሮዎች የምንረዳው ይሄን ነው ። ምንም እንኳን የህይወት ሚስጥራት ሁሉ በቅዱሳን መፅሀፍ ውስጥ ሰፍረው እሚገኙ ቢሆንም ፣ ቅዱሳን መፅሀፍን በትክክል መረዳት እሚችሉ ጥቂቶች ናቸው ። በዚህች ምድር ከተፈጠሩ ታላላቆች የደረሱበትን እውቀት አስተላልፈው አልፈዋል ። ነገር ግን የሰው ልጅ ሁኔታ እነሱ ሲመጡ ከነበረው ፈቀቅ አላለም ። ይህ የሆነበት የራሱ ምክንያት አለው ።

ሰዎች የታላላቆቹን አስተምህሮ አለመረዳትና አለማወቅ ብቻ ሳይሆን እውነትን ለመከተል ድፈረትንና የውስጥ ንፅህናንና ፍቅርን ይፈልጋል ። ሌሎች ሰዎችን መውድድን ፣ የራስን ጥቅምን ከማስቀደም ይልቅ ለሰዎች ደህንነት ማሰብንና መጨነቅን ይጠይቃል ። የውስጥ ንፅህና የሌለው ፣ ውስጡ ንፁህ ያልሆነ ፣ ክፋትን በውስጡ ያዘለ ከእውነት ጋር ትውውቅ የለውም ፣ ሊኖረውም አይችልም ።

የካባላህን ሚስጥር ካወቁ መሀል ፣ ላኦ ዙም እንደዛው ሲሆን፣ ቡድሀም እንደዛው ነው ። ጥቂቶች ይረዱሀል ብለው ነው ። የሊቁን ፎስት ታሪክ እዚህ ላይ መጥቀስ ተገቢነት አለው ። ሊቁ ፎስት እውቀትን ከሰይጣን ጋር የተለዋወጠ ሰው ነበረ ። የአለምን ሚስጥር ሁሉ እንዲገልጥነትና በልዋጩም ነፍሱን ሰይጣን እንዲወስዳት ነፍሱን ለሰይጣን ለመስጠት  ከሰይጣን ጋር የተዋዋለ ሰው ነበረ ።

ኦከልትንም ብንወሰድ እንደዛው ነው ። ለብዙሀኑ ቢታወቅ አደገኛ ነው ተብሎ ስለ ሚታሰብ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ግን አንድ ሰው ፓሪስ ወይንም ለንደን ሳይሄድ እዚሁ አዲስ አበባ ተቀምጦ ማወቅ ይችላል ። በድረ-ገፅ ላይ መመልከት ይችላል ። ለምሳሌ ፕሌቶ ለጥቂት ፈላስፋዎች ብቻ ይሰጥ የነበረውን እውቀት በመፅሀፍ መልክ በመፃፉ በዘመኑ በነበሩት ልሂቅ ፈላስፎች ተተችቶበታል ። በየትኛውም የታሪክ ዘመን ልሂቃኖች እውቀታቸውን ለብዙሀኑ ለማካፈል ፈቃደኛ ሆነው አያውቁም ። ለዚህም ምክንያቱ በርካታ ነው ፣ በአንድ በኩል ልሂቃኑ የተቀረው ህብረተሰብ ሊረዳው አይችልም ብሎ በማሰብ ወይም ፣ እውቀት የሀይል ፣ የስልጣንና የሀብት ምንጭ ስለሆነ ሚስጥርነቱን ለመጠበቅ በሚል ነው ።